2016-10-06 12:05:00

ቅዱስነታቸው ቮዳፎን ከተባለው የግል ኩባኒያ አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት "ገንቢዎች እንጂ አፍራሾች አትሁኑ" ማለታቸው ታወቀ


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመስከረም 25/2009 በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ በቴለኮሚንከሽን ሥራዎች ላይ ተሰማርቶ የሚገኜው ቮዳፎን ከተባለው ዓለማቀፍ የግል ድርጅት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው “ገንቢ መሆን አለባችሁ” ካሉ ቡኋላ መንፈሳዊ የሆኑ መልዕክቶችንም ለብዙኋኑ ተደራሽ ያደርጉ ዘንድም ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ቮዳፎን የተሰኘው ዓለማቀፍ የግል የቴሌኮምንከሽን ድርጅት “ፈጣን ትምህርት ቤቶች ለአፍሪካ” የተሰኘ እና online ወይም በቀጥታ የድዕረ ገጽ መስመር ትምህርት አዘል የሆኑ ፕሮግራሞችን በአፍሪካ አህጉር ለሚገኙ ወጣቶች ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑም በእለቱ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸውም ይህንን መልካም ተነሳሽነት አድንቀው  ይህ የተጀመረ ተነሳሽነት በመገለል አደጋ ላይ የሚገኙትን የማሕበርሰብ ክፍሎችን የማስተሳሰር እድል የሚከፍት እና የዓለምን ማሕበርሰብ እንደ አንድ ቤተሰብ በማስተሳሰር የልማት እድሎችን የሚከፍት መሆኑን በመግለጽ የተጀመረውን ጥረት እንደ ሚያደንቁም ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው አክለውም ይህ የተጀመረው ተነሳሽነት ከግንዛቤ ልያስገባው የሚገባው ጉዳይ “ይህ አገልግሎት በሚጀመርበት ወቅት ወጣቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ፣ መሳሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው መማር ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅባቸው ነገር ግን የሚጠቀሙበትን መሳሪያ እንደ ቁስ አካል አድርገው መጠቀም እንደ ሚገባችቸው እና በነጻነት እና በጥልቀት” መማር እንዲችሉ ማገዝ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ይህ በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው የቀጥታ መስመር የትምህርት አገልግሎት “መንፈሳዊ የሆኑ አስተምህሮች እና በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ ቅዱሳን መጻሕፍት ይካተቱበት ዘንድ” ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸው “ይህም በአፍሪካ ባሕል ውስጥ የሰረጸውን መንፈሳዊነት እና በሐይማኖት ተቋማት መካከል ግልጽ ውይይት ይካሄድ ዘንድ የሚያግዝ ለመንፍሳዊ ጉዳዮች የምትሰጡት መልካም ገጽታን” ልያሳይላችሁ ይችላል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማጠቃለያ ንግግራቸው “ይህ የተጀመረው የቀጥታ መስመር ፕሮግራም በጣም ገንቢ እንደ ሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፣ አሁን ባለንበት ወቅት ገንቢ ነገሮችን ማከናወን በጣም አስፈላጊ ነው፣ ቦንብ በሰው ልጆች ላይ ሲወድቅ የሚያሳየውንና የሰላማዊ ሰዎችን፣ የልጆችን፣ የታመሙ ሰዎችን እንዲሁም በአጠቃላይ በከተማው ላይ ቦንብ ሲወርድ የሚያሳየውን ምስል ብቻ ሳይሆን ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ የሰው ልጆችንን እድገት የሚያፋጥኑ ገንቢ ተግባራት ላይ ትኩረት ልትሰጡ ይገባል! ገንቢዎች ሁኑ እንጂ አፍራሾች አትሁኑ! ካሉ ቡኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.