2016-10-06 11:56:00

ቅዱስነታቸው በነሐሴ 18/2008 በርዕደ መሬት አደጋ ሰላባ የሆኑ ከተሞችን ጎበኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በጥቅምት 25/2009 በአሳለፍነው ዓመት በነሐሴ 18/2008 በከባድ ርዕደ መሬት የተመታችሁንና ከ298 በላይ ነዋሪዎቿን በሞት የተነጠቀችሁን አማትሪቼን ከተማን መጎብኘታቸውና በጥቃቱ ወዳጆቻቸውን እና ንብረታቸውን ካጡት የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተገናኝተው የግራ ጸሎት ማድረጋቸው እና ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ፊት እንዲጓዙም መምከራቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ከሪዬቲ ጳጳስ ጋር ሆነው ከተማይቷን ለመጎብኘት ያቀኑት በመኪና መሆኑ የታወቀ ሲሆን በእለቱም ከጥዋቱ 3:10 ላይ የአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎችን መጎብኘታቸውም ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው ጉብኝታቸውን የጀመሩት አዲስ የተሠራውን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጎብኘት እንደ ነበር የተገለጸ ሲሆን በጎብኝታቸው ወቅት ከሕጻናት ተማሪዎች ጋር በተገናኙበት ወቅት ሕጻናቱም በእጃቸው የሳልዋቸውን የተለያዩ ስዕሎችን ከአበርከቱላቸው ቡኋላ ሕጻናቱን አንድ በአንድ ተቀብለው ሰላምታን ሰጥተው እና በርዕደ መሬቱ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ሕጻናቱ እንደ ተረኩላቸውም ተገልጹኋል።

ቅዱስነታቸው ለማትሪቼ ነዋሪዎች እንደ ገለጹት “አደጋው ከደረሰ ቡኋላ በመጀመሪያዎቹ ቀናት ነበር ወደ እናንተ መጥቼ ሐዘናችሁን እና መከራችሁን ለመካፈል ያሰብኩት ነገር ግን በእለቱ የእኔ መምጣት እናንተን ከመርዳት እና ከማጽናናት ይልቅ መሰናክል ይሆናል ብዬ ስላሰብኩኝ ነው ትንሽ ጊዜያት እንዲያልፉ እና አንድ አንድ መሰረታዊ ችግሮቻችሁ ለምሳሌም እንደ መጠልያ፣ ትምህርት ቤት የመሳሰሉ ነገሮች እስኪሟሉ መጠበቅ የፈለኩትም በእነዚሁ ምክንያቶች ነው” ብለዋል።

“ነገር ግን አደጋው ከተከሰተበት የመጀመሪያ እለት አንስቶ ወደ እናንተ በመምጣት መንፈሳዊ አጋርነቴን መግለጽ እንዳለብኝ ወስኜ ነበር፣ ለእናንተም ጸሎት አድርጊያለሁኝ፣ አጋርነት እና ጸሎት ይህንን ነው ለእናንተ ያቀረብኩት” ካሉ ቡኋላ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ በእዚህ የሐዘን፣ የስቃይ እና የመስቀል ጎዞኋችሁ የእመቤታችን ፀጋ ይጸልልባችሁ” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የአማትርቼ ነዋሪዎች ከባረኩ ቡኋላ “ሁልጊዜም ቢሆን ነገን በማሰብ ወደ ፊት እንጓዝ፣ በእነዚህ ፍርስራሽ ስር የወደቁ ብዙ ተወዳጅ የሆኑ ወገኖቻችን ጥለውን ሄደዋል፣ ስለእነርሱ ለእመቤታችን ጸሎት እናቅርብ፣ ይህንንም አብረን እናድርግ። ሁልጊዜም መጭውን ጊዜ ተመልከቱ። በርቱ እርስ በእርሳችሁም ተጋገዙ። በጋራ ብዙ መጓዝ እንችላለን፣ ብቻችንን ግን የትም መድረስ አንችልም፣ ወደ ፊት ሂዱ! አመሰግናለሁ።” በማለት የማጽናኛ ምክራቸውን ቅዱስነታቸው በሕይወት ለተረፉ የአማትሪቼ ከተማ ነዋሪዎች ለግሰዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ከአማትሪቼ ከተማ ከንቲባ ሰርጆ ጲሮሲ ጋር በመሆን በርዕደ መሬቱ ክፉኛ ወደ ተጎዳውን የከተማይቷን ማዕከል መጎብኘታቸው እና ለብዙ ደቂቃዎች ያህል ቆመው የህሊና ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በቅድስት መንበር የህትመት ክፍል የተሰጠው መግለጫ እንደ ሚያሳየው “በአሳለፍነው ሳምንት እሁድ እለት በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ያደረጉትን ጉብኚት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አጠቃለው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ይህን ማለትም ዛሬ በአማትሪቼ ያደረጉት ጉብኚት ‘በግላቸው እንዲሁም ብቻቸውን ሆነው እንደ ካህን፣ ጳጳስ እንዲሁም እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን ብቻዬን አደርጋለሁ። እንደዚህም ነው ማድረግ የምፈልገው። ወደ ሕዝቡ መቅረብ እፈልጋለሁ” ቅዱስነታቸው ብለው እንደ ነበር መግለጫው አስታውሱኋል።

በአሁኑ ወቅት በአማትሪቼ ከተማ በርዕደ መሬት መለኪያ መሳሪያ ረክተር ስኬል 6.2 የተመዘገበው ርዕደ መሬት ቤታቸውን ሙሉ በሙሉ ያወደመባቸው ከ4000 በላይ ሰዎች በድንኳን ውስጥ ተጠልለው እንደ ሚኖሩ ታውቁኋል።

ቅዱስነታቸው በጉብኚታቸው ወቅት በቁጥር 60 ከሚሆኑ እና በቅዱስ ሩፋኤል የአረጋዊያን መጦሪያ ቤት ከሚገኙ አረጋዊያን ጋር ምሳ አብረው ከተቋደሱ ቡኋላ በቀጣይነትም በነሐሴ 18/2008 በእዚሁ የርዕደ መሬት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ወደ ደረሰባት ሌላዋ ከተማ አኩሞሊ ከተማ አቅንተው በእዚያም ለሕዝቡ ሰላምታን አቅርበው እና በአደጋው ሙሉ በሙሉ በወደመው የቅዱስ ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ቆመው ከሕዝቡ ጋር ጸሎት ማደርገቸውም ታወቁኋል።

ቅዱስነታቸው የአኩሞሊ ጉብኚታቸውን ካጠናቀቁ ቡኋላ ፔስካራ ደል ቶሮንቶ ወደ ተባለው ከተማ በሚያቀኑበት ወቅት ለሦስት ጊዜያት ያህል መኪናቸውን አስቁመው በህብረት በመንገድ ላይ ቆመው ለነበሩትን ሰዎች ሰላምታ ማቅረባቸውም በእለቱ ተገልጹኋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው አርኩዋታ ደል ቶሮንቶ የተባለውን የእዚሁ ርዕደ መሬት አደጋ ሰለባ የሆነውን ከተማ ለመጎብኘት ባቀኑበት ወቅት በቁጥር መቶ የሚሆኑ ሰዎች አቀባበል ካደርጉላቸው ቡኋላ ቅዱስነታቸው አጠር ያለ መልዕክት አስተላልፈው እና ‘ፀጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይ’ የሚለውን ጸሎት በጋር ደግመው በጊዚያዊነት የተሰራውን የሕጻናት ትምህርት ቤት መጎብኘታቸውም ታውቁኋል።

በእዚህቹ አርኩዋታ ደል ቶሮንቶ ከተማ ጉብኚታቸው ወቅት በአደጋው ሰላባ ለሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ከእነርሱ ጋር በቅርበት መሆን እንደሚፈልጉና በልባቸው ሐዘናቸውን እና ጭንቀታቸውን እንደ ሚጋሩ” ከገለጹ ቡኋላ “ሕይወታቸውን በእዚሁ አደጋ ያጡት ተወዳጅ የሆኑትን ወገኖቻችሁን አጥታችኋል፣ ለእዚህም ነው ዛሬ እኔ ከእናንተ ጋር መሆን የፈለኩት፣ በእዚህም ምክንያት ነው እዚህ የተገኘሁት. . . በርቱ በጽናትም ወደ ፊት ተጓዙ። ጊዜ ይቀየራል ወደ ፊትም በጓዝ ይቻላል። እኔ ለእናንተ ቅርብ ነኝ፣ ከእናንተ ጋርም ነኝ” ማለታቸው ታውቁኋል።

ቅዱስነታቸው ቀጣዩን እና የጉብኚታቸውን ማጠቃለያ ያደረጉት በእዚሁ በነሕሴ 18/2009 ዓ.ም ተከሰቶ በነበረው ርዕደ መሬት አደጋ ሰላባ የሆነችሁን የሳን ፔሌግሪኖ ዲ ኖርቺያ ጠቅላይ ግዛት በመጎብኘት ሲሆን በእዚያም በእዚሁ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ቆመው ጸሎት ማድረጋቸው እና አጠር ያለ መልዕክት ለከተማው ነዋሪ ካስተላለፉ ቡኋላ “በእዚህ የሐዘናችሁ ወቅት” ሁል ጊዜም ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ገልጸው እና ብራታትን ይጎናጸፉ ዘንድና ወደ ፊት በጽናት እንዲጓዙ እንደ ይጸለዩላቸው እንደ ነበር ከገለጹ ቡኋላ ጉብኚታቸውን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.