2016-10-06 12:49:00

ቅዱስነታቸው "በ3ቱ የካውካሰስ ሀገራት ተገኚቼ በቁጥር አናሳ የሆኑ የካቶሊክ ምዕመናንን በመጎብኜቴ ደስ ብሎኛል" አሉ


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት ጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በመስከርም 25/2009 ያስተላለፉት አስተምህሮ በቅርቡ በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ያደረጉት ጉብኚት ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው እንደ ገለጹት “ባለፈው ሰኔ ወር በአርመኒያ ጉብኚት ባደረኩት ወቅት ሦስቱንም የካውካሰስ ሀገሮችን በመጎብኘት በእዚያው የሚገኙ በቁጥር አናሳ የሆኑ የካቶሊክ ማሕበርሰቦችን ለማበረታታት፣ ሁሉም ሰው ወደ ሰላም እንዲያመራ እና የወንድማማችነት ስሜት ይኖራቸው ዘንድ ለመጎብኘት የነበረኝን ምኞቴን እውን ያደረኩበት ጉብኚት” እንደ ነበር ገልጸው “እግዚኣብሔር አርሜንያን፣ ጆርጂያን እና አዘረበጃንን  ይባርካቸው ዘንድ እና የእሱን ቅዱስ ሕዝብም ይመራ ዘንድ ጸሎቴ ነው” ብለዋል።

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅዱስ ጴትሮስ አደባባይ ያስተላለፉትን ጠቅላላ አስተምህሮ እነደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ወድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

በቅርቡ በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ጉብኚት ባደረኩበት ወቅት በፀጋው የረዳኝን እግዚኣብሔርን እያመሰገንኩኝ በሁለቱ ሀገራት ለሚገኙ የመንግሥት እና የሐይማኖት ተቋማት መሪዎችም በተለይም የጆርጂያን ፓትሪያርክ ኤልያ ሁለተኛን እና የካውካሰስ ሙሲሊም ሼክ የሆኑትንም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይህ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በአርሜንያ ያደረኩትን ጉብኚት ተከትሎ ሦስቱንም የካውካሰስ ሀገራትን በመጎብኜት በእነዚህ ሀገራት የሚኖሩ በቁጥር አናሳ የሆኑ የካቶሊክ ማሕበረሰቦችን ለማበረታታት እንዲሁም ለሰላም እና ለወንድማማችነት የሚያደርጉትን ጎዞ ለመደገፍ  የነበረኝን ፍላጎት ያሳካ ጉብኚት ነው። ምንም እንኳን ጆርጂያ እና አዘረባጃን ጥንታዊ የሆነ ታሪክ፣ ባሕል እና መንፈሳዊ ሥር መሰረት የነበራቸው ሀገራት ቢሆኑም ነጻነታቸውን የተቀናጁት የዛሬ 25 ዓመት በመሆኑ ብዙ መሰናክሎች እየገጠሙኋቸው ይገኛል። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተጠራችሁ ለእነርሱ ቅርብ ለመሆን ነው፣ በተለይም የበጎ አድራጎት ተግባራትን በማከናወን እና የሰውን ልጅ ክቡርነትን በማስተዋወቅ ከሌሎች አብያተ-ክርስቲያናት እና ከክርስቲያን ማሕበረሰቦች ጋር በመሆን በሌሎች የሐይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ በመሥራት ላይ ተገኛለች። በጆርጂያ የምናከናውናቸው ተግባራት ከኦርቶዶክስ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በመሆን ሲሆን ጆርጂያን ለመጎብኘት በሄድኩበት ወቅት ፓትሪያርክ ኤሊያ ሁለተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ድረስ መጥተው አቀባባል ማድረጋቸው የግንኙነታችንን ጥልቀት ታላቅ ማሳያ ሊጠቀስ ይችላል በተጨማሪም ወደ ፓትሪያርካዊ ካቴድራላቸው በሄድንበት ወቅት ያደረግነው ስብሰባ አበረታች መሆኑም መልካም ገጽታውን ያመላክታል። ይህ ሕብረታችን መሰረቱን አድርጎ የነበረው በተለያዩ ጊዜያት ደማቸውን በማፍሰስ ክርስትናቸውን በመሰከሩት ስማዕታት ላ ሲሆን በተለይም የሲሪያ እና የቄልቄዶን ክርስቲያኖች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው በእነርሱ አማላጅነትም ለሶሪያ፣ ለኢራቅ እና ለመላው የመካከለኛ ምስራቅ ሰላም ጸሎት በማድረግም ተገቢ ነው። የእስልምና ማሕበረሰብ በሚበዛባት አዘረበጃን በሐይማኖቶች መካከል በሚደረገ ወይይት ላይ ተካፊዬ እና በእዚያው ለሚገኙ ጥቂት የካቶሊክ ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርጊያለሁ። በአንዱ እግዚኣብሔር ማመናችን እምነቶቻችንን የምያስተሳስር በመሆኑ ግንኙነታችንን የሚያጠናክር እና ለውይይቶች የሚጋብዝ አጋጣሚ በመኖሩ በጋራ ፍትህን እና ወንድማማችነት የሰፈነበት ዓለም ለመገንባት ያስችለናል። እግዚኣብሔር አርሜንያን፣ ጆርጂያን እና አዘረበጃንን ይባርክ፣ ቅድሱ ሕዝባቸውንም ይመራ ዘንድ እማጸናለሁ።

ቅዱስነታቸው ከላይ የተጠቀሰውን ንግግራቸውን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ካስተላለፉ ቡኋላ ለሕዝቡ ቡራኬን ሰጥተው ሕዝቡን ተሰናብተዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.