2016-10-05 16:49:00

የካቶሊካዊትና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ግኑኝነት ለዓቢይ አወንታዊ ለውጥ


እ.ኤ.አ. መጋቢት 23ና 24 ቀን 1966 ዓ.ም. በካቶሊካዊትና አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ግኑኝነት እንዲኖርና ግኑኝነቱም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የበቃ አቢይ አወንታዊ ለወጥ ያስጨበጠ መሆኑ የሚነገርለት ሲሆን በአገረ ቫቲካን በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛና የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ቀዳሜ ሚካኤል ራምሰይ የጋራ የስምምነት ሰነድ ፍርርም የተከናወነበት ይኽ ለሁሉምቀጣይ ግኑኝነቶች ፍኖት ያስያዘው ክሌኣዊ የአቢያተ ክርስትያናቱ ግኑኝነት እግብ ለማድረስ ያስቻለውም እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 1960 ዓ.ም. በወቅቱ ከቀዳሜ ራምሰይ በፊት የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ፊሸር በአገረ ቫቲካን ከዮሓንስ 23ኛ ጋር የተካሂደው ግኑኝነት መሆኑ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀም 2016 ዓ.ም. ባወጣው ህትመቱ አስነብቧል።

ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ከቀዳሜ ራምሰይ በአገረ ቫቲካን ያካሄዱት ግኑኝነት በበአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመለገስ ተገኝተው ይፋ በማድረግ፡ የአቢያተ ክርስቲያን መለያየት ለሮማ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ስቃይ ነው። ቢሆንም ዛሬም መለስ ብሎ ለውህደት ታልሞ ግኑኝነቱን ማነቃቃት የጌታ ፈቃድ ነው እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ በማስታወስ ሮማ በሚገኘው ፎሪ ለ ሙራ ጳጳሳዊ የቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ የሁለቱ ኣቢያተ ክርስትያን መሪዎች ተገናኝተው የእንግሊክዊት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሜ መንፈሳዊ መሪ የሮማ ጳጳስ እጅ ተንበርክከው ሰላም ሲሉ ጳውሎስ ስድስተኛም የሮማ ጳጳሳዊ ቀሌበታቸው ከጣታቸው በማውለቅ በቀዳሜ ራምሰይ ጣት ላይ አጥልቀው እንዲህ ባለ መልኩም ትልቅ መቀረራብ የተመሰከረበት ግኑኝነት በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል መቀራረብ ለውህደት ያለመ ውይይት ማካሄድ እጅግ እንዲበረታና ጥልቅ ዘርፈ ብዙ ግኑኝነት እንዲከወን በማድረጉም ምክንያት በ 1969 ዓ.ም. የዓለም አቀፋዊ የካቶሊካዊትን የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራ ድርገት እንዲቆም አድርጓል።

ይኽ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች መካከል የተካሄደው ግኑኝነት ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሜ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት ጁስቲን ወልባይ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ሮማ የገቡ ሲሆን እ.ኤ.አ. ዛሬ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጎርጎሪዮስ ዘቸሊዮ ቤተ ክርስቲያን በሚመሩት ጸሎተ ዘሰርክ ይሳተፋሉ በዚህ የጸሎት ስነ ሥርዓትም ከሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ በጠቅላላ ኣርባ ብፁዓን ጳጳሳት እንደተገኙና በሁባሬ ጸልየዋል ሲሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሜ ወልባይ በጠቅላላ ከተለያዩ 38 የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መናብርት በተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት ተሸኝተው ጧት በአገረ ቫቲካን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር እንደሚገናኙም ዘንጋሪኒ ከወዲሁ ገልጠው፥ በዚህ የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የዛሬ 50 ዓመት በፊት የተጀመረው ግኑኝነት ማእከል ያደረገ በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የአንግሊካዊትና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራ ግኑኝነት በሚል ርእስ ዙሪያ ዓውደ ጉባኤ እንደሚካሄድ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.