2016-10-05 16:53:00

የካቶሊካዊትና ሉተራናዊት አቢያተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት የጋራ መግለጫ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስዊድን ሉንድ ከተማ ዝክረ 500ኛው ዓመት የሉተራናዊት ቤተ ክርስቲያን ህዳሴ ምክንያት በሚከናወነው መንፈሳዊ መርሃ ግብር እንደሚሳተፉ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ ርእስ ዙሪያ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. መጥቅምት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመቱ እንዳመለክተውም፥ የአቢያተ ክርስትያናት ውህደት ላይ በማነጣጠር የሚደረገው የጋራ ጉዞ ብዙ እንቅፋት የሚያጋጥመው ቢሆንም ቅሉ ለውህደት ታልሞ የሚደረገው የጋራው ግኑኝነት አበረታችና ተስፈኛ ምልክቶች ለዓለም የሚሰጥ እንዲሆን ብሎም ግኑኝነቱ  ለውህደት ያለው ጥልቅና ቅን ፍላጎት የሚያጐላ ነው የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ የስቶኮልም ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ አንድረስ ኣርቦረሊዩስና በሉተራናዊት የህዳሴ ቤተ ክርስቲያን በስቶኮልም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ አንትዠ ካከለን ፊርማ የተኖረበት የጋራ ሰነድ ይፋ መውጣቱ አስታውቋል።

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስዊዲን ለዝክረ 500ኛው ዓመት የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ቅዋሜ ምክንያት በሚከወነው በዓለ ለመሳተፍ የዛሬ 50 ዓመት በፊት በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የተጀመረው የጋራው ግኑኝነት ያስገኘው ወጤት የሚመሰክር መሆኑ የስቶኮልም የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በጋራ ባወጡት ሰነድ እንደተሰመረበት ሲር የዜና አገልግሎት ጠቅሶ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል በየድህነት ሥርወ ትምህርት (ጠመቅ ትምህርት) ዙሪያ የተደረሰው ስምምነት እንዲሁም ሌላው ከግጭት ወደ ውህደት የተሰየመው የጋራው ሰነድ ዋቢ በማድረግ በማልሞ ሜዳ የህዳሲያዊት ቤተ ክርስቲያ ቅዋሜ ዝክረ 500ኛው ዓመት ምክንያት በተስፋ በጋራ በሚል ርእስ ሥር የተመራ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ለመላ ዓለም የእግዚአብሔር መሐሪነት የሚመሰክርና በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚከናወነው ግኑኝነት ይኸንን የሚያጎላ መሆኑ የሚያብራራ ሃሳብ እንዳሰፈሩበትም አክሎ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.