2016-10-05 17:01:00

ስፖርት ለሰብአዊ አገልግሎት


እ.ኤ.አ. እስለ ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ምክር ቤት እምነትና ስፖርት በሚል ርእስ ሥር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አድራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመሩት ሥነ ስርዓት መጀመሩ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግሰጫ አክሎ በዚህ ዓውደ ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቶማስ ባኽ እንዲሁም ሌሎች 15 የተለይዩ ሃይማኖቶች የበላይ መፈሳውያን መሪዎች እንደሚሳተፉ አስታውቋል።

ስፖርት ለያይ የሆነውን የግንብ አጥር በማፍረስ በሕዝቦች መካከል መገናኘት እንዲኖር የሚያበቃ ድልድይ እንዲገነባ በማድረግ ለሕዝቦች ለባህሎች ለተለያዩ ሃይማኖቶችና ጎሳዎች መቀራረብ አቢይ ሚና እንዳለው ስለ ጉባኤው በማስመልከት ጳጳስዊ የባህል ጉዳይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንጻ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የገለጡ ሲሆን እንደ አብነትም ዘንድሮ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሪዮ ኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር የኮሶቮና እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስደተኞና ተፈናቃዮች ቡድን ሱታፌ ጠቅሰው ስፖርት አገናኝ ድልድይ ነው ብሏል።

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ በሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫ ስፖርት ሰብአዊነት ባህርይ ያለው ሰብእዊነትን ወንድማማችነትን የሚያነቃቃ አካልንና አምሮን የሚያስተሳስር በጠቅላላ ሰው መሆንናዊነትን የሚመለከት ነው፡ ስለዚህ ግኑኝነትን በሁሉም ዘርፍ የሚያስፋፋ ነው፡ ምንም’ኳ ወዳሪነትን በውስጡ ያካተተ ተግባር ቢሆንም ቅሉ በውግያ በግጭትና በጦነትት እንደሚደረገው ሌላውን ለሞት በመዳረግ የበላይነትን ማረጋገጥ ከሚለው ትርጉም ጋር ምንም ዓይነት ጉኑኝነትና ተምሳይነትም የለውም፡ ስፖርት አገሮች ህብዞች ባህሎችና ጎሳዎችን ሃይማኖቶችን የሚያገናኝ የሰብአዊነት ባህል የሚስፋፋ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.