2016-10-04 11:51:00

ቅዱስነታቸው 2ሚ. ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት 700 የካቶሊክ ምዕመናን ብቻ የሚገኙባትን አዘረበጃንን መጎብኘታቸው ተገቢ ነበር አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአዘረባጃን ያለአዳም ኋጥያት በተጸንሰችሁ ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ ክርስቲያን መስዋዕተ ቅድሴን ካሳረጉ ቡኋላ በእዚያ ለሚገኙ ጥቂት የካቶሊክ ማሕበርሰብ ከመልዐከ እግዚኣብሔር ጸሎት ቡኋላ ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት ይህንን ረጅም ጉዞ በማድርገ ጥቂት የካቶሊክ ማሕበርሰብን ለመጎብኘት መምጣታቸውን “ጊዜ እንደ ማባከን አልቆጥረውም” ካሉ ቡኋላ ወደ እዚህ የመጡበት ዋነኛው ምክንያታቸው “ከእነርሱ ጋር ለመሆን በመፈለጋቸው” ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

 

ምን አላባት አንድ አንድ ሰዎች በጣም ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጬ እዚህ 2 ሚልዮን ሕዝብ በሚገኝባት አዘረበጃን 700 የካቶሊክ ማሕበረሰቦችን ለምጎብኘት መምጣቴ ጊዜን እንደ ማባከን ሊቆጥሩት ይችሉ ይሆናል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ይህ ማሕበርሰብ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገር በመሆኑ የተነሳ ወጥ የሆና ማሕበርሰብ ባይመስልም ለእኔ ግን ከምርጫዎቼ አንዱ በመሆኑ ነው እዚህ የተገኘሁት ብለኋል።

መንፈስ ቅዱስ በፍርሃት ተውጠው በራቸውን ዘግተው በነበሩ ጥቂት ሰዎች ላይ ከመውረዱ ጋር የሚያመሳስላችሁ ብዙ ነገር አለ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በፍርሃት፣ በድህነት፣ በስደት ወይም በመገለል ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖችን መንፈስ ቅዱስ ብርታት እና ከለላ እንደ ሆናቸው እንዲሁም ያለምንም ፍርሃት ወደ ፊት እንዲጓዙ እና ክርስቶስን እንዲመሰክሩ እንደ ረዳቸው፣ በኢየስሩሳሌም የሚገኙት የክርስቲያን ማሕበርሰቦች በራቸው በፍርሃት ወይም በሃፍረት ተዘግቶ በነበሩበት ወቅት በሩ ወለል ብሎ እንዲከፈት የረዳው መንፈስ ቅዱስ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። መንፈስ ቅዱስ በዚያን ጊዜ ጊዜን እንዳባከን ሁሉ እኔም ጊዜ ባባክን ምንም አይደልም ብለዋል ቅዱስነታቸው።

በእዚህ ረገድ ሁለት አስፈላጊ ነገሮች አሉ በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማሪያም ከማሕበረሰቡ ጋር ነበረች፣ ስለዚህም እናታችንን አትርሷት! በዚህ ፍቅር ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ፣ በእዚህ የወንድማማችነት ፍቅር ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ፀጋውን ስለሚያዘንብ  ያለምንም ፍርሃት ወደ ፊት ጉዞዋችሁን ቀጥሉ! ብለዋል።

ይህንንም ጸሎታችንን በእመቤታችን ቅድስት ማሪያም አማላጅነት እያቀረብን ይህም ጸጋ በቤተሰቦቻችሁ፣ በታመሙት እና አረጋዊያን እንዲሁም በሥጋ እና በመንፍስ የሚሰቃዩ ሰዎች ሁሉ ላይ ይዘንብ ዘንድ መጸለይ እንደ ሚገባ ገልጸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአዘረበጃን ያደርጉትን ጉብኚት አጠናቀው በመሰክረም 2/2009 የሀግሪቷ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚንስቴር እና የተላዩ ታላልቅ ሰዎች በተገኙበት ደማቅ አሸኛኜት የተደረገላቸው ሲሆን በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1.15 ከኤይዳር አሊዬቭ ዓለማቀፍ የአየር ማረፊያ ተነስተው 3,119 ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነውን የአዘረበጃን፣ የጆርጂያን፣ የቱርክን፣ የቡልጋሪያን፣ የሰርቢያን እና የቦሲኒያ ኤርዘጎቪናን የአየር ክልል አቋርጠው በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከምሺቱ 4 ሰዓት ላይ በሮም በሚገኘው የቻምፒኖ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ደርሰው በቫቲካን ወደ ሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው አምርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.