2016-10-04 15:23:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅርቡ የጵጵስናን ማዕረግ ለተቀበሉ ጳጳሳት ያስተላለፉት መልዕክት።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅርቡ የጵጵስናን ማዕረግ ከተቀበሉትና በህነጻ ትምህርት ላይ ከነበሩት አቡናት ጋር መገናኘታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣተር በመስከረም 16/2016 ከእነዚሁ አዳዲስ ጳጳሳት ጋር በተገናኙበት ወቅት ሰፋ ያለ መልዕክት መስተላለፋቸው ተገለጸ።

ክቡር አባታችን ፍራንቸስኮ በቅርቡ የማዕረገ ጵጵስናን ከተቀበሉ አቡናት ጋር በተገናኙበት ወቅት አስተላልፈው የነበረውን መልዕክት እንደ ሚከተለው እንቀረበዋልን።

የተወደዳችሁ ጳጳሳት ወንድሞቼ በሮም እየተካሄደ በሚገኘው የቤተክርስቲያን ጳጳስት እንድትሆኑ ይህንን ከእግዚኣብሔር የሰጣችሁን ታላቅ ጥሪ ክብደቱን በጥልቀት እንድትመረምሩ በሚያደርገው ገንቢ ስብሰባ የመጨረሻ ቀን ላይ ትገኛላችሁ። እዚህ ለተገኛችሁ የጳጳስት ጉባሄ፣ እንዲሁም ከየአከባቢያቸው ተወክለው የመጡትን የምስራቃዊ አብያተ-ክርስቲያናት ጳጳሳት ጉባሄ መሪ ካርዲናል ኦውሌት እና ካርዲናል ሳንድሪ ከልብ የመነጨ ሰላምታን ላቀርብላችሁ እወዳለህ። የጳጳሳቱ ሹመት በመልካም ሁኔታ እንዲከናወን እና በተጨማሪም በእዚህ ሳምንት ጳጳስቱን ለማብቃት በማሰብ በተካሄደው ዝግጅት የተሳተፋችሁትን ሁሉ ለመልካም ተግባራችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። የቅዱስ ጴጥሮስ ተካታይ እንደ መሆኔ የእግዚኣብሔርን ቅዱስ ሕዝብ እንድትመሩ `በእግዚኣብሔር የተጠመረጣችሁ እናንተ ፊት ቆሜ ከልብ በመነጨ መልኩ አንድ አንድ ሐሳቦችን ከእናንተ ጋር ለመካፈል በመብቃቴ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል።

  1. ተወዳጅ እንደ ሆናችሁ አስቀድሞ ማወቅ

አዎን! እግዚኣብሔር በፍቅሩ እና በእውቀት እናንተን ቀድሞኋችሁ ይሄዳል! በፍቅሩ እና አስገራሚ በሆነ ምሕረቱ እርሱ እናንተን ‘አጥምዶኋችዋል`። የእርሱ መረብ ምስጢራዊ በሆነ መልኩ ተዘርግቶ ማምለጥ እስከ ማትችሉበት ደረጃ ድረስ ማርኩዋችኋል። ሙሽራው በሆነችሁ በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ለእዚህ ተግባር መጠራታችሁ እንዳስደሰታችሁ በደንብ አውቃለሁ። ለእዚህ ዓይነቱ አስደሳች የመሪነት ሚና የታጫችሁት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ግን አይደላችሁም። ለእራሱ ብቻ የተጠራ መስሎት የነበረው እና እግዚኣብሔር ግን ሕዝቡን እንዲመራ በአደራ በሰጠው ጊዜ ሸሽቶ ወደ በረሃ የሄደው መሴ ነበር በመጀመሪያ የተጠራው። የሕዝቦች የመከራ ጩኸት ያለማቁረጥ ወደ እግዚኣብሔር ይደርስ እንደ ነበረ ሁሉ አሁን የእናንተ ስም በእግዚኣብሔር እየተጠራ መሆኑን እወቁ።

አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ሰማያት ሲከፈቱ የተመለከተውንና “በበለስ ዛፍ ሥር” (ዩሐ. 1,48) በነበረበት ወቅት ኢየሱስ አይቶት የጠራውን ናትናሄልንም ማውሳት ይቻላል።  አሁንም የብዙኋኑ ሕይወት ነጻ ወደ ሆነ ቦታ እና ወደ ላይ እያመራ ይገኛል፣ እናንተን በእሩቁ አይቶ የጠራችሁ እነዚህን ሰዎች ብያንስ ወደ ግማሽ መንገድ እንድታደርሱ ነው። ሳምራዊቷ ሴት ኢየሱስን በውሃ ጉርጓድ አጠገብ አግኝታው “ባወቀችሁ” ጊዜ ወደ መንደሩ ሄዳ ሌሎች ሰዎችን ጠርታ ከኢየሱስ ጋር ተገናኚተው የሕይወት ውሃ እንዲያገኙ እንዳደረገች ይታወቃል። ስለዚህም እናንተም በጥቂት ነገር አትደሰቱ! በቤተ ክርስቲያኖቻችሁ አከባቢ ሕዝቡ የሚጓጓለትን ነገር ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ መፈለግ ሳይሆን የሚጠበቅባችሁ ነገር ግን ሕዝቡ የተራበው እና የተጠማው ነገር የሚገኘው ከንፈራችሁ በሚወጣ ነገር ላይ መሆኑ ማወቅ አስፈላጊ ነው።

ከነበሩበት “ግላዊ የልብ መሻት” በብዙ ድካም ነቅተው ለትናንሾች የሚገለጽ፣ ለእራስ ወዳዶች ግን የሚሰወረው ወደ ምስጢራዊ የእግዚኣብሔርን ሕይወት የሚወስደውን መንገድ በደስታ ከተጓዙ  መኋል ሐዋሪያቶችም ይገኙበታል። አንድ አንድ ጊዜም ከእግዚኣብሔር ሐሳብ እና ዓላማ ውጭ በምትሆኑበት ጊዜ አትፈሩ። ይልቁንም በእራሳችን የመመካትን አስተሳሰብን አስወግዳችሁ ለትናንሾች መንግሥቱን ስለሚገልጽ  እንደ ሕጻናት ለእርሱ በአደራ ስጡት።

2. ታዛዥነትን ያለው ውበት

ተወዳጅ የሆነ የእግዚኣብሔር እውቀት ውስጣችሁን ጠልቆ እንዲገባ መፍቀድ መልካም ነው። እርሱ እኛ ማን መሆናችንን ማወቁና በምንቆሽሽበት ወቅት ሁሉ የማያስፈራራን መሆኑን ማወቅ ያጽናናናል። የሚያረጋጋንንና የጠራንን የእርሱን ድምጽ በልባችን ውስጥ በማስቀመጥ እኛን ያልተገባን መሆናችንን እንዲያስታውሰን ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግጠኛነት ሰላምን መጎናጸፍ የምንችለው እኛ በእራስችን ችሎታ ሳይሆን በእርሱ መልካም ፈቅድ ላይ ተመስርተን እርሱ የጀመረውን እንድንጨርስ የሚሰጠን ጌታ ነው።

ዛሬ ብዙዎች እራሳቸውን ይሸሽጋሉ ይደብቃሉም። የእራሳቸውን ስም መልካምነት  በመገንባትና ጥሩ የሆነ መገለጫዎቻቸውን ማሳየት ይወዳሉ። በመቃረም ባገኙት ሐብት ባሪያዎች ይሆናሉ፣ በእዚህም በገንዘብ ሊገዛ የማይችለውን ፍቅር ለመግዛት ይፍጨረጨራሉ። ከእነርሱ የሚበልጥ ትልቅ ሰው መኖሩን በማስበ የሚገኘውን ደስታ ማወቅ አይፈልጉም፣ እንዲሁም ትንሽ መሆንን ይንቃሉ ድክመቱን የማይወቅስ እና አምኖ የሚቀበል እርሱ ቅዱስ ነው። በእኛ ድክመት እርሱ አይደሰትም ስለዚህም ውድቀታችሁን አትደብቁ ወይ ዝም አትበሉ አትሸፍኑትም፣ እራስን በመግለጽ በሚገኘው ደስታ ተካፋዮች ሁኑ።

3. የክርስቶስ ልብ ወደ ምሕረት የሚውስደን ትክክለኛ በር ነው።

ባለፈው ሳምንት እለተ ሰንበት የእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በር በብዙ ሺ በሚቆጠሩ ከሁንብሪያ እና ከኦርቤ የመጡ ምዕመናን ይህንን በር ማለፋቸው ይታወቃል። እናንተም በምስጋና ይህን ዓይነት የግል ሕይወት ተሞክሮ እንዲኖራችሁና እርቅን እንድታሰፍኑ፣ በሙልኋት እንድታምኑ እንዲሁም የእረኞች እረኛ ለሆነው ምንም ሳትቆጥቡ እራስችሁን እንድትሰጡ ጥሪ አደርግላችኋለሁ።

4. ሐዋሪያዊ ተግባራችሁን ምሕረትን ባማከለ ምልኩ ፈጽሙ

በምሕረት የተሞላውን የእግዚኣብሔርን ሐዋሪያዊ ተግባራትን በምሕረት የማከናወን ምስጢር እንዲገልጽላችሁ እና ወደ የሀገረ ስብከቶቻችሁ ይዛችሁ መሄድ እንድትችሉ ይህንን ፀጋ እርሱን ጠይቁት። በእርግጥ ምሕረት በቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ የሚከናወኑትን ሐዋሪያዊ ተግባሮቻችንን እንዲቀርጽ እና እንድያንጽ ማድረግ  አስፈላጊ ነው። ይህም መስፈርቶቻችንን የሚያሳንስ ወይም ደግሞ በርካሽ ሐዋሪያዊ ተግባሮቻችንን መሸጥ ማለት ሳይሆን ይልቁንም ይህንን እንደ እንቁ የሆነውን የሐዋሪያዊ ተግባሮቻችሁን ለማግኘት እድል ላላገኙ ሁሉ እድሉን እንዲጎናጸፉ የሚያደርግና እኔም ይገባኛል የሚለውን አይነተኛ ጥያቄን በማስነሳት ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ግን ያጡትን ነገር መልሰው እንዲጎናጸፉ የሚያደርግ አይነተኛ ዘዴ ነው። 

ምሕረት እግዚኣብሔር ለዓለም የሰዋው ታላቅ ነገርን ጠቅልሎ የያዘ በመሆኑን መናገርን እና ሐሳብን ማቅረብን አትርሱ ምክንያቱ ከእዚህ የተሻለ እና የሰውን ልብ መሳብ የሚችል ነገር ስለሌለ። ይህም በቂ አይደለም “የተገተረውን ማጠፍ፣ የቀዘቀዘውን ማሞቅ፣ አቅጣጫ የሳተውን ወደ ትክክለኛው መንገድ መመልስ”. . . ከእነዚህ የተሻለ ሰው ላይ ኋይል መፍጠር የሚችል ነገር ምን አለ? እነዚህን ነግሮች መፈጸም ካልቻልን ባለመቻላችን ተረግመናል ማለት ነው። ምን አልባት የእኛ ፍርሃቶች ከግድግዳን  ጋር የመጋፈጥ እና የተከፈቱ በሮችን የመዝጋት ኋይል ያለው ይመስላችኋል? እርግጠኛ ያለመሆናችን እና አለመተማመናችን  በብቸኝነት ወቅት እና በተረሳንበት ወቅት ሁሉ ጣፉጭ ጣዕምን በመስጠት መጽናናትን በጋጣሚ ያስገኛሉ ብላችሁ ታስባላችሁ?

ከእኔ ቀድሞ የነበሩትና የማከብራቸው ጥበበኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኔደክቶስ 16ኛ “ለክፉት ገደብ የሚያበጀው ምሕረት ነው” ብለው እንዳስተማሩኝ በእዚህም የእግዚኣብሔር ልዩ ተፈጥሮ፣ ቅድስናው፣ የእውነት እና የፍቅር ኋይል ባሕሪይ የተገለጸበት በእዚህ በምሕረት ነው። ይህም "አምላክ ያለው የተለያዩ መለኮታዊ ኃይል ጋር በቅንጅት ከጨለማ ሥልጣን የሚያወጣን ዓይነተኛው መንገድ የምሕረት መንገድ ብቻ ነው”። ስለዚህ “የጨለማ ኋይል ሊያስፈራራችሁ አይገባም”። ከሁሉም በላይ በእነዚህ ነገሮች እርግጠኛ እንድትሆኑ በሚያደርጋችሁን እግዚኣብሔር የእያንዳንዱን ልብ በምያንኳኳበት ወቅት የሚጠቀመን የዋህ የሆነ ኋይልን መጠቀምን የሚያስችላችሁን ቅድስናን፣ እውነትን እና ፍቅርን ተላበሱ ወይም ጠብቁ። ልክ በአንድ ትልቅ የእንግዳ ማረፊያ እንዳለ ትልቅ ሰው የባለቤትነት ስሜት ሳይሰማችሁ ነገር ግን ሁል  ጊዜ እንደ አንድ አገልጋይ መድገም ይሚጠበቅባችሁ “ጌታዬ በፊትህ ሞጎስ አግኝቼ የሆነ እንደ ሆነ ባሪያህን አልፈህ አትህሂድ” (ዘፍ 18.3) ማለት ይኖርብባችኋል።

5. የምሕረት አገልግሎት ለማድረግ የሚያስችሉ ሦስት ምክሮች

እናንተ በተሰጣችሁ ኋላፊነት የሐዋሪያዊ ተግባራትን በምሕረት ለማከናወን ማለትም ተደራሽነት ያለው፣ ተጨባጭ በሆነ መልኩ እና በማይጣረጽ መልኩ የተሰጣችሁን ታልቃ ኋላፊነት በሚገባ መወጣት ያስችላችኋል ብዬ ያስበኩትን ሦስት አጫጭር ሐሳቦችን ለማቅረብ እወዳለሁ።

5.1  አንደበተ ርቱ እና የማሳብ ችሎታ ያላችሁ ጳጳሳት ሁኑ።

የሰዎችን ልብ ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመሳብ እና ለመማረክ አይነተኛ ኋይል የሆነውን ምሕረት የአገልግሎታችሁ ሁሉ አምድ አድርጉ። በመጨረሻው ሰዓት እንኳ ሌባው "መልካምነትን ብቻ ስላገኘ" መልካምነትን በተጎናጸፈው በእርሱ ተሳበ (ሉቃ. 23.41) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የነበረውን እያዩ ደረቶቻቸውን እየ ደቁ የተሰቀለውን ባያዩ ኖሮ መቼም ቢሆን ስለእራስቻው  እንደ ማያውቁ ይናዘዙ ነበር፣ ያንን ታላቅ ፍቅር ባይረዱ ኖሮ መቼም ቢሆን በነጻ እና በብዛት የሚሰጠውን ፍቅር አይረዱም ነበር። እግዚኣብሔር ሩቅና ግድየለሽ የሆነ ከሆነ እርሱን ማግለል በቀላሉ ይቻላል ነገር ግን በጣም ቅርብ የሆነ እና በተለይም ደግሞ ለፍቅር ብሎ የቆሰለውን እግዚኣብሔር በቀላሉ መቃወም ግን ከባድ ነው። መልካምነት፣ ውበት፣ እውነት፣ ፍቅር፣ በጎነት . . . ወዘተ። አዎ! አንዲት ጎድጓዳ ስህን ብታክልም  ለእዚህ ለተጠማ ዓለም ብዙ ነገር ማበርከት እንችላለን።

ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ሰዎችን ወደ ራሳችን መሳብን አይመለከተም። ዓለማችን የውሸት አቀንቃኞችን መስማት ደክማለች። ሰዎች ከሚያባብሉዋቸው፣ ከሚጫንዋቸው፣ የእራሳቸውን ጥቅም ብቻ የምያሳድዱ እና ከሀዲዎችን  “አይቀበሉም“። ከሁሉም በላይ እናተ ከመምጣታችሁ በፊት የነበረውን እግዚኣብሔርን አስቀድሙት።

በመጀምሪያ መጽሐፈ ሳሙኤል የተጠቀሰው የሳሙኤል ታሪክ ትዝ አለኝ። ምንም እንኳን “የእግዚአብሔር ቃላ ብዙ ባልነበረበት ወቅት. . .ወይም ግልጸት ብዙ አልንበረም” (1ሳሙ. 3.1) ይሆናል። ይሁን እንጂ እግዚኣብሔር እራሱን ደብቆ አያውቅም ነበር። ነገር ግን በሦስተኛው ጥሪ ኤሊ ወጣቱን ሳሙኤልን ለእርሱ ሳይሆን መልስ መስጠት የሚገባው ነገር ግን ለእግዚኣብሔር መሆኑን ተረዳ። ዛሬ ዓለም እንደ ሳሙኤል ግራ ተጋብታለች፣ በየቦታው ለሚነዙ የውጥረት ድምጾች ወይም ደግሞ ምስጢራዊ በሆነ መልኩ እየጠራት ለሚገኘው እግዚኣብሔር. . ለየተኛው ድምጽ አቤት ማለት እዳለባት ማወቅ አስፈላጊ ነገር ነው። ትሁት እና በማይከብድ ቀላል ቋንቋ የሚናግረውን ሰምተው “ጌታ ሆይ ተናገር” ማስባል የሚችሉ ድምጹን ለይተው የሚያውቁ ሰዎች ያስፈልጋሉ። በተጨማሪም ይህንን ቃል በጸጥታ ውስጥ መስማት የሚችሉ ሰዎችም ያስፈልጋሉ።

እግዚአብሔር ፈጽሞ አይረታም! ውድድር የለመድን እኛ ነን እንጂ ብዙን ጊዜ  የምንመርጠው ተደላድለን በምንቀመጥበት ወቅት የእርሱን ስም ስያጠፉ ማየት እና የእርሳችንን ስንፍናን ለመደበቅ በማሰብ ጎምዛዛ የሆኑ ክርክሮችን እናነሳለን ይህም ደግሞ የከንቱ ቅሬታዎች ድምጽን እንድናስተጋባ ያደርገናል።

5.2 በአደራ የተሰጣችሁን ነገር ሁሉ በታማኝነት በመያዝ የተሰጣችሁን የጵጵስና ተግባር ጀምሩ

ሁሉም ነገር በታላቅ ፍላጎት የመመርመር ፍላጎት ማዳበር የመጀመሪያው መንገድ ነው።  ሊሻር የማይችለው የመለኮታዊ ምሕረት ቀዳሚ ሊሆን የገባዋል። በቅድሚያ በምሕረት ከተማረካችሁ ከእዚያም በመቀጠል መንገዱን የመጀመር ጉጉት በውስጣችሁ ያድራል። ቤተ ክርስቲያን የእግዚኣብሔር መንፈስ የሚመነጭባት እናት መሆኑዋን መረዳት እና እውነትን በሙልኋት በመረዳት መንገዳችንን መጀመር እንዳለብን መረዳት በራሱ በቂ ነው። ምስጢራቶቹ ታላቅ ሐብት መሆናቸውን፣ እነርሱን ሁልጊዜ በተደጋጋሚ መጎብኘት በእራሱ አስፈላጊ መሆኑን መረዳት፣ በሐዋሪያዊ ተግባራቶቻችን ቤተ ክርስቲያን ከእርሷ የተወለዱትን ሁሉ እንደ እናት እንደምትመግብ እና በእርሷ በኩል ሰዎች ከእግዚኣብሔር መወለዳቸውን ማወቅ በእራሱ በቂ ነው። የእግዚኣብሔር ምሕረት ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዳልጠፉና ከእርሱ እቅፍ ውጭ አለመሆናቸውን እንዲረዱ የሚያደርግ ሁነኛው ማረጋገጫ የሚሰጣቸው ብቸኛ እውነታ ነው። በምሕረት ብቻ ነው የሰው ልጅ እንዳልተጣለ እና ከእግዚኣብሔር እቅድ ውጭ በሚገኘው አድማስ ውስጥ ተንሸራቶ አንዳልገባ እርግጠኛ ሊሆን የሚችለው።

የምሕረት መገለጫው ክርስቶስ ነው። ምሕረት በእርሱ የተሰጠን ቋሚ እና የማይሻር ስጦታ ነው። በእርሱ ነው ማንም ሰው ጠፍቶ መቅረት እንደ ሌለበት የታወጀው።  ለእርሱ እያንድ አንዱ ሰው ልዩ ነው። እንደ ጠፋው በግ እያንዳንዱን ሊፈልግ እንደ ሚሄድ፣ ጠፍቶ እንደተገኘችሁ አንድ ሳንቲም ሁላችንም በደሙ ገዝቶናል፣ ጠፍቶ እንደ ነበረው ልጅ ነገር ግን ተመልሶ በሕይወት እንደ ተገኘው እኛንም ይፈልገናል። እናንተን ጳጳሳት አደራ የምላችሁ በኋላፊነት የተሰጣችሁን እያንዳንዱን ሰው ልዩ እንደ ሆነ አድርጋችሁ እንድትቆጥሩ እና በእዚህም ረገድ እንድትንከባከቡኋቸው አደራ እያልኩኛ ማንኛውንም መንገድ ተጠቅማችሁ የጠፋውን መመለስ እንደ ሚገባችሁ ማወቅም በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። 

5.3 ከምዕመናኖቻችው ጋር አብሮ መጓዝን ማወቅ ተገቢ ነው

ሐዋሪያው ተግባሮቻችሁ ውስጥ ምሕረትን ማካተት የምያስችላችሁን አንድ የመጨረሻ ምክር እንድሰጣችሁ ፍቀዱልኝ። ይህንንም ለመረዳት በኢያሪኮ መልካሙ ሳምራዊ ያከናወንውን ተግባር በልባችን ማሰላሰል ግድ የሚል በመሆኑ እና የአንድ እናትን ባሕሪ ተላብሶ ያን ስም ያልተሰጠውን እና በወንበዴዎች ተደብድቦ ወድቆ የተገኘውን ሰው በምሕረት እንደነካው ማስታወስ ተገቢ ነው። በመጀምሪያም ቆስሎ በሞት አፋፍ ላይ የነበረው ሰው እይታ ልቡን እንዲወጋው ፈቀደ፣ እንደ ምታውቁት ከዚያ በኋላ ነው እንግድህ አስደናቂ የሆኑ ግሦች የተከተሉት። እነዚህም ግሦች የምሕረት ተግባር እንዲፈጸም ከፍተኛ እገዛን አድርገዋል። የሐዋሪያዊ ተግባሮቻችሁ በምሕረት የታጀበ ሊሆን የግባዋል የምላችሁ ለእዚሁ ነው እነዚህ ሦስት ግሶች መቆም፣ መንበርከክ እና መሥራት የሚባሉ ሲሆን እነዚህን ቃላቶቻች ተጨባጭ በሆነ ተግባር ማሳየት አስፈላጊ ነው። ሰዎች ምሕረትን በጣም ተጠምተዋል፣ ያስፈልጋቸዋልም ነገር ግን ሳያውቁት በተለያየ መንገድ ይፈልጉታል። እንደ ተጎዱ እና በሞት አፋፍ ላይ እንዳሉ ብያውቁም በተግባር ለማዋል ግን ይፈራሉ። ባልጠበቁበት ሰዓት በምሕረት ስንቀርባቸው ግን እንድናክማቸው እጃቸውን ይዘረጉልናል። ሌሎች ምንም ሳይረዱዋቸው በሚያልፉበት ወቅት እናንተ ግን አንድ ጊዜ ቆም ብላችሁ ስትመለከቱኋቸው ይማረካሉ፣ ጎንበስ ብላችሁ ስትነኩዋቸው ልባቸው ይሰበራል፣ የተጎዳውን ሰውነታቸውን ስትነኩ ይደሰታሉ በእዚህ ተግባራችሁ ሁሉም ደስተኞች ይሆናሉ በለዋል።

ሳምራዊው ሰው ከተናገራቸው ቃላት በአንዱ ላይ ማተኮር እፈልጋለሁኝ። ቆስሎ ያገኘውን ሰው አንስቶ ወደ እንግዳ መቀበያ ድረስ ወሰደው እዳውን ሁሉ እንደ ሚከፍልለትም ለእንግዳ መቀበያ ባለቤት ቃል ገባ።  ለእዚህም ነው በተሰበረ ልብ ካደረገው መልካም ነገር ባሻገር አሳስቦት የነበረው ጉዳይ የዚህ ሰው መዳን ብቻ ሳይሆን የነገ ተፋውን ማለምለም ስለ ነበር ያለውን ነገር ሁሉ ሳይቆጥብ ለእዚህ ሰው አዋለው። ምንም አልሳሳም ነበር። ትቶትም ሊሄድ አልፈለገም ነበር። ምንም እንኳን ሳምራዊ ቢሆንም ቅሉ ያደረገው የምሕረት መልካም ተግባር በእግዚኣብሔር ፀጋ እንዲሞላ አደረገው።

እንደ እዚህ በምሕረት የተሰበረ ልብ ያላችሁ ጳጳሳት እንድትሆኑ እና በታላቅ ትህትና ሳትደክሙ በድንገት ቆስሎ የምታገኙትን ሰው አድናችሁት በትክክለኛ መንግድ ላይ ይቆም ዘንድ እንድትረዱት ያስፈልጋል። በምትሄዱበት ቦታ ሁሉ ከእንደነዚህ ዓይነቱ መንገድ አትራቁ። እናንተ የምታስተዳድሩት ቤተ ክርስቲያንት ውስጥ የእዚህ ዓይነት ችግር ያላቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ እወቁ። እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች በመቅረብ ወንድማችሁ እና ጎረበታችሁ ማድረግ ብዙም ከባድ ነገር አይደለም።

በቅድሚያ ግን ባታላቅ ትዕግስት እና እንክብካቤ ካህናቶቻችሁን አገዙ። ወደ የሀግራችሁ ስትመለሱ ለካህናቶቻችሁ የእኔን ሰላምታ እና ለሚያከናውኑት ታላቅ የምሕረት ተግባር ያለኝን ከፍተኛ አድናቆት ማድረስን እንዳትረሱ። በተጨማሪም ክርስቶስ የእነርሱ እጣ ፋንታቸው መሆኑን እና የወረሱት ታላቅ ሐብታቸው እርሱ ብቻ እንደር ሆነ ይረዱ ዘንድ ካህናቶቻችሁን አግዙዋቸው ይህም በእየለቱ በሚጠጡት ጽዋ እውን እንደሆነም አስገንዝቡዋቸው። እስቲ ማነው የአንድ የእግዚኣብሔር አገልጋይ ልብ ከክርስቶስ ሌላ ሊሞላ የሚችለውበችግር ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችን ሁሉ አግዙኋቸው። የእግዚኣብሔርን ፍቅር እንዲረዱም አድርጉዋቸው።

ውድ ወንድሞቼ

አሁን አብረን እንጸልይ፣ እንደ መልካም እረኛ፣ እንደ አባት እና እንደ ወንድም በመሆን ከልብ የመነጨ ቡራኬን ልስጣችሁ። ማንኛውም ቡራኬ የእግዚኣብሔር ፊት መገለጫ እና መቀበያ ነው። የእግዚኣብሔር ፊት ገጽታ የሆነው ኢየሱስ ይጠብቃችሁ፣ በምባርካችሁ ወቅት እርሱ ከእናንተ ጋር ይራመድ ዘንድ ጠይቃለሁ። የማረከን የእርሱ ፊት በእኛ ውስጥ ይቀረጽ ከእኛም ጋር ይጓዝ። እንዲህም ይሁን!

All the contents on this site are copyrighted ©.