2016-10-03 09:06:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጆርጂያው ሐዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው 16ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 09 ሰዓት ከጠዋቱ ሮማ ከሚገኘው ፊውሚቺኖ ዓለም አቀፋዊ ያየር ማረፊያ የተነሱ ሲሆን በዚህ ጉዞ የአየር ክልላቸውን ላለፉባቸው ለኢጣሊያ ለክሮኣዚያ ለቦስኒያ ኤርዘጎቪና ለሞንተነግሮ ለሰርቢያ ለቡልጋሪያና ለቱርኪያ ርእሳነ ብሔር ባስተላለፉት የተለግራም መልእክት እንዳሉት፥

የተከበሩ የጣሊያን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማቴሬላ

ሮም

በተለያዩ ባህሎች እና የሐይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት እንዲደረግ ለማበረታታት እና በክርስቲያኖች ዘንድ ያለው ሕብረት ይጠናከር ዘንደ እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በእምነት በጽናት መቆሟን ለማሳየት እና ብርታት ለምስጠት በማሰብ ሐዋሪያዊ ግቡኚት ለማድረግ ወደ ጆርጂያ እና አዘረበጃን በምሄድበት በአሁኑ ወቅት ለእርሶ ለተከበሩ ፕሬዝደንት እና ለመላው የጣሊያን ማሕበረሰብ ከልብ የመነጨ ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ የጣሊያን ማህበርሰብ ሁሉ መንፈሳዊ እና ማሕበረሰባዊ እድገት እንዲያመጣ መኞቴ መሆኑን እገልጻለሁ።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

የቦሲኒያ እና ሄርዘጎቪና ዋና ፕሬዚደንት የሆኑ የተከበሩ ባኪር ኤዝቴጎቪች

ሳሪዬቮ

በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄድበት በአሁኑ ወቅት የቦሲኒያን እና የሄርዘጎቪናን የአየር ክልል በማቋርጥበት በአሁኑ ወቅት ለእርሱ የተከበሩ ፕሬዚዳንት እና ለመላው የሀገሪቱ ሕዝብ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። በሀገሮ አድርጌው የነበረውን ግንኙነት በማስታውስበት በአሁኑ ወቅት የኋያሉ እግዚኣብሔር ቡራኬ በእናንተ ላይ ይወርድ ዘንድ እመኛለው።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

የሞንቴ ኔግሮ ፕሬዝዴንት የሆኑ የተከበሩ ፍሊፕ ቩጃኖቪቺ

ፖዳጎሪካ

በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄድበት በአሁኑ ወቅት የሞንቴ ነግሮን የአየር ክልል በማቋርጥበት በአሁኑ ወቅት ለእርሶ ለተከበሩ ፕሬዚዳንት እና ለመላው የሀገሮ ሕዝብ ሰላምታዬን አቀርባለሁ። በጸሎቴ እንደ ማስታውሳችሁ እየገለጽኩኝ በሀገራችው ላይ መንፈሳዊ ጸጋ ይዘንብ ዘንድ ምኞቴ ነው።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

የሰርቢያ እና የቤልግሬድ ሪፖብሊክ ፕሬዚዴንት የሆኑ የተከበሩ ቶሚስላቭ ኒኮሊች

በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄድበት በአሁኑ ወቅት የሰርቢያን የአየር ክልል በማቋርጥበት በአሁኑ ወቅት ለእርሶ ለተከበሩ ፕሬዚዳንት እና ለመላው የሀገሮ ሕዝብ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። በጸሎቴ እንደማስታውሳችሁ እያረጋገጥኩኝ በሀገሮ ላይ መለኮታዊ በረከት ይበዛ ዘንድ እጸልያለሁ።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

የቡልጋሪያ ሪፖብሊክ ትሬዚዴንት ለሆኑ የተከበሩ ሮዜን ፕሌቬኔሌቪ

በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄድበት እና የቡልጋሪያን የአየር ክልል በማቋርጥበት በአሁኑ ወቅት ለእርሶ ለተከበሩ ፕሬዚዳንት እና ለመላው የሀገሮ ሕዝብ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። በጸሎቴ እንደማስታውሳችሁ እያረጋገጥኩኝ በሀገሮ ላይ መለኮታዊ በረከት ይበዛ ዘንድ እጸልያለሁ።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

የቱርክ ሪፕብሊክ ፕሬዚዳንት ለሆኑ ታቲፕ ኤድሮጋን

በጆርጂያ እና በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በሚሄድበት እና የቡልጋሪያን የአየር ክልል በማቋርጥበት በአሁኑ ወቅት ለእርሶ ለተከበሩ ፕሬዚዳንት እና ለመላው የሀገሮ ሕዝብ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ። በሀገሮ አድርጌው የነበረውን ግንኙነት በማስታውስበት በአሁኑ ወቅት በሀገሮ ላይ መለኮታዊ በረከት ይበዛ ዘንድ እጸልያለሁ።

ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ

.... ቅዱስ አባታችን በሮማ ሰዓታ አቆጣጠር ልክ ከቀትር በኋላ አንድ ሰዓት ላይ በጆርጂያ ሰዓት አቆጠርጥር ደግሞ ልክ 3 ሰዓት ትብሊሲ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ደርስዋል

የተከበራችሁ አድማጮቻችን እስቲ የጆርጂያ ርእሰ ከተማ ከሆነቸው ትብሊሲ ጋር እናስተዋውቃችሁ፥

ተብሊሲ በኩራ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ የጆርጂያ ዋና ከተማ ስትሆን 1,118,035 ነዋሪዎችን አቅፋ የያዘች እና በ458 ዓ.ም የጆርጅያ ግዛት ዋና ከተማ ሆና የተመሰረተች ናት። አውሮፓን እና ኤሽያን የሚያገናኝ ትራንስካውካሶ የተባለ ስልታዊ የሆነ ቦታም የሚገኝባት ከተማ ናት። ይህችህ ከተማ ከክርስቶስ ልደት ቡኋላ በስድስተኛው ክፍለ ዘመን በፋርሶች፣ በሰባታኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ በባዛንታይን እና በአረቦች ተወራ ኣንደ ነብረ ታሪኳ የሚያሳይ ሲሆን 1386 በመንጎልያ ስር ቅኝ ተገዝታ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም 1801 በሩሲያ ቅኝ ግዛት ሥር ውደቃ እንደ ነበረ እና ነጻነቱዋንም 1918 መልሳ እንደ ተጎናጸፈች ከታሪኳ መረዳት ይቻላል።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር 1999 በጊዜው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ 89ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኚት ያደረጉት በጆርጂያ ሲሆን በትብሊሲ ከተማ 112 ሺ ማለትም ከከተማይቱን ኑዋሪ 2 እጁ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥር በሚተዳደረው እና የጎርጎሮሳዊያን ስርዐተ አምልኮን በሚከተለው ቤተ ክርስቲያን የተጠመቁ ካቶሊኮች ሲሆኑ ከዚህም ተጭማሪ የላቲን፣ የርሜንያ እና ጥቂት የሶሪያ ቄልቄዶን ስርዓተ አምልኮ የሚከተሉ ካቶሊኮችም እንደ ሚገኙባት ታውቁዋል።

 በጆርጂያ በአርመኒያና አዘርበጃን  የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ማረክ ሶልዝይኒስኪና እንዲሁም የክሌአዊ ግኑኝነቶች ስነ ሥርዓት ጉዳይ ኃላፊ ወደ አይሮፕላኑ በመግባት ከቅዱስነታቸው ጋር ሰላምታን በመለዋወጥ መርተው ከአይሮፕላኑ ሲወርዱም መርተው እዛው በሚጠበብቁዋቸው በአገረ ጆርጂያ መራሔ መንግሥት ጆርጂ ማርግቨላሺቪና ክብርት ባለ ቤታቸው እንዲሁም የመላ ጆርጂያና የካቶሊኮስ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኢሊያ ዳግማዊ በካውካሱስ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መስተናብር ብፁዕ አቡነ ጂዘፐ ፓሶቶና በምስራቅ ኤውሮጳ ለአርመን ካቶሊካውያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ራፋኤል ሚናሲያን አቀባበል ተደርጎላቸው ለክብራቸው የወታደራዊ ሰልፈኛ የክብር ሰላምታ አቀርቦ የአገረ ቫቲካንና የጆርጂያ ብሔራዊ መዝሙሮች ተደምጠው እንዳበቃም  በአገሪቱ መራሔ መንግሥትና በቀዳሚት እመቤት ተሸኝተው በአየር ማረፊያው ወደ ሚገኘው ወደ የርእሰ ብሔር የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ በመሄድ ቆይታ አድርገው ልክ በጆርጂያ ሰዓት አቆጣጠር 03 ሰዓት ከሩብ ወደ ቤተ መንግሥት አቅንተው ልክ 03. ተኩል ቤተ መግንሥት እንደደረሱም ርእሰ ብሔር ጂርጂ ማርግቨላሽቪልና ቀዳሜ እመቤት ማካ አቀባበል ተድርጎላቸው እዛው የክሌኣዊ የግል ግኑኝነቶች አጠናቀው ርእስ ብሔሩም ሁለቱን ልጆቻቸው ጨምረው መላ ቤተሰቦቻቸውን ለቅዱስ አባታችን አስተዋውቀው ካበቁ በኋላ ቅዱስ አባታችንና መርሔ መንግሥቱ በጆርጂያ ሰዓት አቆጣጠር 04 ሰዓት በርእሰ ብሔሩ ተሸኝተው የፖለቲካ አበይት አካላት የተለያዩ ሃይማኖት የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች ልኡካነ መንግሥታትና የሕዝባውያን ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም ከባህል አካላት ጋር ተገናኝተው በዚህ በተካሄደው ግኑኝነትም ርእሰ ብሔር ማርግቨሽቪል ካስደመጡት ንግግር በመቀጠል  ቅዱስ አባታችን  የሚከተለውን መልእክት አስደምጧል።

የተከበሩ ፕሬዚዳንት

የተከበራችሁ ባለስላጣናት እና የዲፕሎማቲክ ጓድ አባላት

ወንድሞች እና እህቶች

በእዚህች በተባረከች ምድር፣ በተለያዩ ባህሎች እና ስልጣኔውች የግንኙነት ቦታ በሆነችው እንዲሁም ከአራተኝው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቅዱስ ኒኖ ተሰብካ ክርስትናን የተቀበልች እና የክርስትና እመነት ሥር መሰረት ያላት እና ጠንካራ የእመንት መሰረት ባላት ሀገር በመገኘተ እግዚኣብሔርን አመሰግናለሁ።

ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ ሀገራችሁን ከጎበኙ ቡኋላ “የጆርጂያን ባሕል እንደ አበባ እንዲፈካ ያደረገው ዘረ ክርስትና መሆኑን” ታዝበው ነበር ይህም ዘረ ፍሬያማ መሆኑን ቀጥሉዋል። ባለፈው ዓመት ክቡር ፕሬዝዳንት በቫቲካን ያደረጉትን ግንኙነት ወቅት ከጆርጂያ ጋር የቅድስት መንበር ያላትን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ እና ይህም ግንኙነት ቀጣይ እንዲሆን በማሰብ በጆርጂያ ሕዝብ እና ባለስልጣናት ስም ክቡር ፕሬዚደንቱ  እዚህ እንድመጣ ስለጋበዙኝ ከልብ ላመሰግኖት እወዳለሁ።

ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠረው ታሪክ ያላት ሀገራችሁ ከባህል፣ ከቋንቋ እና ከዎጎች ጋር የተሳሰረ ጥብቅ እሴቶች እንዳላችሁ ነው። ይህም ሀገራችሁ ባጠቃላይ እና በከፊሉ ለአውሮፓ ስልጣኔ መሰረት ሆኖዋል እንዲህም ሀገራችሁ ከመልካዐምድር አቀማመጧ የተነሳ በኤሽያ እና በአውሮፓ ሀገራት መካከክል አገናኝ ድልድይ በመሆን በሁለቱ አህጉራት የሚገኙትን ሕዝቦች እንዲገናኙ አስተዋጾ አድርጉዋል።

የተከበሩ ፕሬዝዳንት፣ ጆርጂያ ነጻነቱዋን ከተጎናጸፈች እነሆ 25 ዓመታትን አስቆጥራለች።  ጆርጂያ መሉ ነጻነቷን በተቅዳጀችበት ወቅት ዲሞክራሲያዊ የሆነ አሰራሮችን በመገንባት እና በማጠናከር በተጨማሪም ዲሞክራሲያዊ ተቁዋማትን በመገንባት ቀጣይነት ያለው እድገትን ለማስበዝገብ የበኩሉዋን ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች። ይህም ሁሉ የሆነው ምንም ዕእይነት መስዋዕትነት ሳይከፈልበት አልነበረም፣ ነገር ግን ሕዝቡ በከበለው ከፍተኛ መስዋዕት የተጎናጸፋችሁት ነበረ እንጂ። ይህ የጀመራችሁት የሰላም እና የልማት መንገድ በሲቪል ማህበርሰብ ተሳትፎ ቀጣይነት ይኖረዋል ብዬ ተስፋ በማድረግ ለመረጋጋት፣ ለፍትህ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ለሁሉም የማኅበርሰብ ክፍሎች እድገት እና የሥራ እድል እንደ ሚፈጥር ተስፋ አደርጋለሁ።

በሁሉም ሕዝቦች መካከክል እና በአከባቢው በሚገኙ ሀገራት መካከል ሰላማዊ የሆነ የአብሮ መኖር መንፈስ ይመጣ ዘንድ ከፍተኛ አስተዋጾ የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው እድገት መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል። ይህም ሁሉም ሀገር የራሱ ሉዋላዊነት በቅድሚያ ሲከበርለት እና ዓለማቀፋዊ መርሆችን ተከትሎ እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መሉ ኋልፊነት እንዲኖረው ሲደረግ ብቻ ነው። ይህም እውን ይሆን ዘንድ የአከባቢው ሀገራት ተጨባጭ የሆነ የአብሮ መኖር ስሜትን እንዲያጎለብቱ ጥሪ እናደርጋለን።

ከልብ በመነጨ መልኩ ለሰው ልጆች ቀዳሚውን ሥፍራ መስጠት ይገባል እንዲሁም ልዩነቶቻችን መረጋጋትን ወደ ሚነሳ እና ማሕበርሰቡ ወደ ሚያናጋ  ብጥብጥን ማምራት የለበትም። አለምግባባት ብጥብጥን ይፈጥራል፣ ብጥብጥ ደግሞ ወደ ማይታለም የዘረ፣ የቋንቋ፣ የፖሌቲካ ወይም የሐይማኖት ጎራ እንድንሰልፍ አድርጎን  ትፋትን ስለሚያመጣ ይህንን ጎዳና በመተው በንጻሩም ቤራዊ መግባባትን ወደ ሚያስገኘው የጋራ መልካም አስተሳሰብ መምጣት ያስፈልጋል።

ለብዙ መቶ ዓመታት በእዚህ ሀገር የኖረችው እና እራሱዋን የሰው ልጆች ቀጣይ እድገት እንዲኖራቸው ጠንክራ እየሰራች የምትገኘው፣ እንዲሁም የበጎ ሥራ ተግባራትን በምፈጸም የምትገኘው፣ የጆርጂያ ህዝብን ደስታ እና መከራ እየተካፈልች ያለችሁ፣ በተጨማሪም ለጆርጂያ ሕዝብ ሰላሙን ይጎናጸፍ ዘንድ በባለ ስልጣናት እና በሲቪል ማህብረሰቡ ውስጥ ትብብር ይፈጠር ዘንድ የበኩሉዋን ሚና እያበረከተች የምትገኘው   የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጆርጂያ በመቶዎች ለሚቆጠር ዓመታት በሀገሩ ቆይታን አድርጋለች። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለጆርጂያ ሕዝብ እና ማሕበረሰብ እድገት እያደርገች ያለችሁን እውነተኛ አስተውጾ አንድ ለሚያደርገን የክርስትና ባሕል ምስጋና ይግባውና ለተቸገሩት ተደራሽነትን ጥንጣዊ በሆነችሁ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በሌሎችም በሀገሪቷ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካካል ቀጣይነት ያለው ውይይት ይደረግ ዘንድ የበኩልዋን አስተዋጾ አጠናክራ እንድትቀጥል ከፍተኛ የሆነ ምኞቴ ነው።

እግዜብሔር ጆርጂያን ይባርካት፣ ሰላም እና ብልጽግናም ያጎናጽፋት።

እንዲህ ባለ ሥነ ስርዓት ከርእሰ ብሔሩ ተሰናብተው እንዳበቁም ልክ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር  ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ ትብሊዚ ወደ ሚገኘው ወደ የመላ ጆርጂያና የካቶሊኮስ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኢሊያ ዳግማዊ መንበር በማቅናት በጆርጂያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 04 ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ከብፁዕ ወቅዱስ ኢሊያ ዳግማዊ የመላ ጆርጂያ ካቶሊኮስ ፓትሪያርክ ጋር ተገናኝተው በባህሉ መሰረትም የቡናና የሻይ የመስተንግዶ ሥነ ስርዓት ከተከናወነ በኋላ በፓትሪያርኩ ተሸኝተው ለክብራቸው የቀረበውን መስተንግዶ ተቋድሰው  የፓትሪያርኩ መዘምራን ማህበር ያቀረቡት ማህሌት ቀርቦ እንዳበቃም በቀጥታ ብፁዕ ወቅዱስ ኢሊያ ዳግማዊ ንግግር እስደምጠው እንዳበቁም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባደመጡት ንግግር፥

ከእርስዎ ቅዱስነትዎና ብጹዕነትዎ ጋር ከጥቀ ክቡራን ሜጥሮፖሊታ ከሊቃነ ጳጳሳትና ከብጹዓን አቡናት ጋር በመገናኘቴ አቢይ ሐሴት ይሰማኛል። ቅዱስነትዎትና ብፁዕነትዎት ዛሬ በጆርጂያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል በታሪክ አንድ የጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገረ ቫቲካንን ሲጎበኝ የመጀመሪያ የሚያስብልዎት ይፋዊ ጉብኝት በመፈጸም ከሮማ ጳጳስ ጋር በመሳሳም ሰላም በመባባል በጸሎት እንተዋወስ በሚል መንፍሳዊ ቃል ኪዳን በመግባበት አዲስ የግኑኝነት ምዕራፍ መርቀው ያስጀመሩ ነአዎት። ያንን በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል በቀዳማው የክርስትና ዘመን የነበረውን ግኑኝነት እንዲጠናከር አድርገዋል። የግኑኝነቱ ቀጣይነትም በተደረገልኝ የሞቀ የእቀባበል ሥነ ምርምርና ኣንዲሁ በአገረ ቫቲካን ቤተ መጻሕፍት የመጠቀሙ እድል ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የእርስዎ ተማሪዎች ለትምህርት መላክ በመሳሰሉት መርሃ ግብሮች ግኑኝነት የተዋጣለት መሆኑ ለማረጋገጥ ችያለሁ። በዚህ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምህረት ዓመት መዝጊያ ይህችን የተባረከች አገር ለመጎብኘት ችያለሁ ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው በ 1999 ዓ.ም. ወደ ሁለት  ሺሕኛው ቅዱስ ዓመት ሊገባ ጥቂት ወራት ቀደም በማድረግ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጆርጂያን የጎበኙ ቀዳሜ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የነበረውን ግኑኝነት እጅግ እንዲጠነክር ለማድረግ ባላቸው ፍላጎት ያከናወኑት ጉብኝት መሆኑም ህዳር 8 ቀን 1999 ዓ.ም.  በትቢሊዚ ባስደመጡት ንግግር አስምረውበት እንደነበር አስታውሰዋል። ያኔ የጆርጂያ ባህል የፍቅር ባህል በማለት እንደገለጡትና የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በዚህ ዓለም እጅግ ምሕረት አንድነትና ሰላም በተጠማበት ወቅት እዚህ ለመገኘት ችያልሁ። ይኽ ደግሞ ወድማማችነታችን ለማደስና በአዲስ መንፈስ ለማነቃቃትም ነው። የጆርጂያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ምስክርነት በተለይ ደግሞ በቅዱስ እንድሪያን ስብከተ ወንጌል የጸናች የሮማ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ሰማእትነት የጸናች በመሆንዋ ዛሬ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው የኢየሱስ ስምና ክብር ሐዋርያዊ ወድማማችነት ውበት ዳግም ለማደስ ጸጋው ሆኖልናል።

ቅዱስ እንድሪያስና ቅዱስ ጴጥሮስ መረባቸውን ትተው ሰውን እንዲያጠምዱ በጌታ የተጠሩ ወንድማማቾች ናቸው (ማር. 1.16-17 ተመል.) ወድ ወንድሞቼ በኢየሱስ እንታይ ዘንድ እንፍቀድለት በእርሱ እንማረክ በእርሱ ጥሪ ዳግም እንማረክ በአንድ ላይ እንዳንሆን የሚገፋፋን ነገር ሁሉ ወደ ጎን በማድረግ ህላዌውን እንመስክር።

ያ ሐዋርያትን የለወጠው ፍቅር ያጽናን። ያ ተመጣጣኝ የሌለው ስለ ወንድም የሚሰዋው ፍቅር (ዮሐ. 15,13) ለእኛ የሰጠበት ምክንያትም እርስ በእርሳችን እርሱ በማፍቅር እንፋቀርም ዘንድ ነው (ዮሐ. 15,12) ይኸንን በተመለከተ ታላቁ የዚህች አገር ተወላጅ ገጣሚና ደራሲ ሩስታቨሊ “ሐዋርያትየጸፉትና ያወሱትና የወደሱት ፍቅር እንብበሃልን? ይኽ ፍቅር ከፍ ከፍ ያደርግሃል፡ አእምሮህን ወደ እነዚህ ቃላቶች አቅና” ሲል የጻፈውን እናስታውስ። እውነት ነው የጌታ ፍቅር ከፍ ከፍ ያደርገናል ምክንያቱም ካለፈው ያለ መግባባት ታሪክ ከወቅታዊው ስሌትና መጻኢን ከመፍራት ተላቀን ከፍ ከፍ እንድልን ያደርገናል በማለት አያይዘው የጆርጂያ ሕዝብ ይዚህ ፍቅር ታላቅነት መስካሪ በመሆን ካጋጥሙት ውጣ ውረዶች ሁሉ ለመነሳት ችሏል። …  አለ ፍቅር በሚለው ርእስ ዙሪያ ገጣሚው የጆርጂያ ተወላጅ ታቢድዘ “አለ ፍቅር በሰማየ ሰማያት ቆብታ ጸሐይ አይነግሥም እንዳለው ነው፡ የዘለዓለማዊነት አመክንዮ ከፍቅር ዘንድ የሚገኝ ነው። ይኽ ደግሞ በባህላችሁ በተለያየ ገጽታው የሚመሰከር እውነት ነው። በዚህች አገር ያለው ክቡር የወንጌል ታሪክ ከቅድስት ኒኖ ጋር ትስስር የለው ታሪክ ነው። እውነተኛ ሕይወት ከሆነው ጋር መሆንን የሚመሰክር የቃልና የሕይወት አብነት። የዚህች አገር ኅብረ ቅዱሳን ዛሬም እንደ ትላንትናው ወንጌልን እንመሰክር ዘንድ አደራ የሚሉ ከዚህ ዓለም ጭንቀት ሁሉ ተላቀን እግዚአብሔር ለሚያመጣው ህዳሴ ክፍት እንድንሆን የሚያነቃቁን ናቸ። ችግሮች እንቅፋት ሳይሆኑ በበለጠ እንድንተዋወቅ በጋራ የሕይወት ምንጭ የሆነውን እምነት ለማካፈል እርስ በእርሳችን በጸሎት በመተሳሰብ እንድንበረታና በሓዋርያዊ ፍቅር በመተባበር የጋራው በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር በምድር ስለ ሰላም አገልግሎት ምስክርነት እንድናቀርብ የሚያበቃን አወንታዊ ግፊት ነው ብለዋል።

ሩስታቨሊ እንደሚለውም ጓደኝነት የማይሻ የገዛ እርሱ ጠላት ይሆናል። ስለዚህ ለዚህች አገር ህዝብ ቅን ወዳጅ ለመሆን እሻለሁ። … በጸሎትና በመሐሪነት አነዚያ ሥጋና ደም ሳይሆኑ መንፈስ የሆኑት ውጫዊና ውስጣዊ ክፋቶች እውነተኛ ጠላቶቻችንን እንድናሸንፍ ተጥርተናል (ኤፈ. 6,12) … ይኽች የተባረከች በወንጌላዊ እሴት ሃብታም የሆነ  ባህል ያላት ምድር እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የክፋት መንፈስ ሁሉ አሸንፋለች ብለው ከዚህ ጋር በማያያዝም ለስደትና መከራ የተዳረጉትን የደም ሰማዕነት የከፈሉት የአገሪቱ መነኩሴዎች የእምነትና አትእግስት ድል አድራጊነት የመሰከሩ … ዛሬ በጌታ ዙሪይ የሚኖሩ የትንሣኤውን ፍሬ የሚኖሩ በዚያ በዚህች እገር ምድር በፈሰሰው ደማቸው እማካኝነትም ፍቅርን ያርከፈከፉና ፍቅርን ያጠጡ የአገሪቱ ቅዱሳን አማላጅነት በዓለም ዙሪያ ለስደትና ለስቃይ የሚዳረጉትን ክርስቲያኖች ብርታት ይሁን በእኛ መካከልም መልካም ወንድማማችነት ኅብረት ወንጌላዊ ሰላም የማበሰር ኃይል ይሁንልን በማለት ያደመጡት ንግግር አጠቃሏል።

 በመጨረሻም የገጸ በረከት ልውውጥ ሥነ ስርዓት ተከናውኖ የፓትሪያርኩ ማኅበረ መዘምራን ያቀረቡት የውዳሴ መዝሙር አማካኝነት ግኑኝነቱ ተጠናቆ ቅዱስ አባታችን ከፓትሪያርኩ ተሰናብተው ልክ በጆርጂያ ሰዓት አቅጣጠር ከቀትር በኋላ 5 ሰዓት አምስት ደቂቃ እንደ መርሃ ግብሩ መሠረት በጆርጂያ የሶሪያ ከላውዲ ስርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጋር ለመገናኘት በርእሰ ከተማይቱ ወደ ሚገኘው ቅዱስ ሲሞነ ባር ሳባኤ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ እዛው እንደደረሱም በባቢሎም የከለዳዊ ስርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስትያኒቱ ቆሞስ አቀባበል ተደርጎላቸው በምእመናን የታጀበ ወደ ቅድስተ ቅድሳን ቤተ ጸሎት መንፈሳዊ ዑደት ተከናውኖ በአራማይስጥኛ ቋንቋ ጸሎት ቀርቦ እንዳበቃልም ቅዱስ አባታችን ስለ ሰላም ጸልየው ከሁሉ የከላዳዊ ስርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ አባላት ጋር ሰላምታን ተለዋውጠው ልክ በጆርጂያ ሰዓት አቆጣጠር 6 ሰዓት ሰዓት ተኩሉ በትብሊሲ ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንጻ አቅንተው ከ 15 ደቂቃም እዛው ደርሰው የጆርጂያን የመጀመርያው ቀን የሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን መርሓ ግብር አጠናቋል።

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጆርጂያ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ ስምንት ሰዓት በጆርጂያ ሰዓት አቆጣጠር ስምንት ሰዓት በትቢሊሲ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ እንደደረሱ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ጆርጂ ማግቨላሺቪን እና በመላ ጆርጂያ ካቶሊኮስ ፓትርያርክ ቅዱስነታቸውና ብፁዕነታቸው ኢሊያ ዳማዊ አቀባበል ተድርጎላቸው አጭር ክሌአዊ ቆይታ በማድረግ የአገረ ቫቲካንና የጆርጂያ ብሔራዊ መዝሙሮች ተደምጠው  እዛው ከተገኙት ብፁዓን ጳጳሳት በጆርጂያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወደ ሚጓዙበት አይሮፕላን በመግባት ጉዞውን ቀጥለው በአዘርበጃን ሰዓት አቆጣጠ ከጠዋቱ ዘጠኝ ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃ በርእሰ ከተማ ባኩ በሚገኘው ሀዳር አሊየቭ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ደርሰው እዛው በአዘርበጃን ምክትል መርሔ መንግሥት በአዘርበጃን የቅድት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል አቀባበል ተደርጎላቸው ለክብራቸው የወታደራዊ ሰልፈኛ ሰላምታ ቀርቦላቸው እንደ መርሐ ግብሩ መሠረትም  በቀጥታ ወደ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማሳርግ አቅንተው አስር ሰዓት ተኩል የዕለተ ሰንበት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው የላቲን ስርዓት ሊጡርጊያዊ ባሕረ ሃሳብ መሠረትም የዕለቱ ከነቢይ እንባቆም ምዕ. 1, 2-3, Mዕ. 2, 2-4 በራሻኛ ቋንቋ

2ጢሞ. ምዕ. 1, 6-8, 13-14 በእንግሊዝኛ

የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 17, 5-10 በአዘረኛ ቋንቋ ተደምጦ እንዳበቃም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስደመጡት ስብከት ጽማሬ መእክቱ እንደሚከተለው ነው፥ እግዚአብሔር ዓለምንና ልባችንን የሚለውጥ አምልካ መሆኑና እንዲሁም እምነት ልዩ ሥልጣናዊ ኃይል ሳይሆን ጨርሶ ከተግባር የማይነጣጠል እርሱም አገልግሎት ጋር የተጣመረ መሆኑ በማብራራት አገልግሎት ሲባል አለ ምንም ስሌትና ለግልጥ ጥቅማ ጥቅም ዓላማ ሳይውል የሕይወት ያኗኗር ስልት ነው። ምንም’ኳ እናንተ ማኅበረ ካቶሊካውያን በዚህች አገር አናሳ የኅብረተሰብ ክፍል ብትሆኑም ለእግዚአብሔር ብርቆች ናችሁ። በእርሱ እይታ ትልቅ ሃብት ናችሁ ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ስብከት ሲያጠቃልሉ አገልግሎ ለእራስ ልዕልናና ስመ ጥሩነት ዓልሞ የሚከወን አይደለም። የእምነት ፍሬ አገልግሎትና ሰላምን የሚመነጨው ፍቅር ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅዳሴው እንዳበቃም ጸሎተ መልአከ እግዚኣብሔር እሳርገው አስተምህሮ ለግሰው እንዳበቁም ልክ እኩለ ቀን ከ 45 ደቂቃም እዛው ከሚገኙት ከሳሊዚያን ማኅበር ልኡካነ ወንጌል የቀረበላቸው የምሳ መዓድ ተቋድሰው 3 ሰዓት ተኩል በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ኢልሃም ሀይዳ አሊየቭ በቤተ መንግሥት ለክብራቸው ባቀረቡላቸው የእንኳን ደህና መጡ ሥነ ስርዓት ተሳፈው ልክ 4 ሰዓት ከ 30 ደቂቃም ለአዘርበጃን ነጻነት የተሰዉት መታሰቢያ ወደ ሚገኝበት የሰማዕታት ሐወልት በመሄድ የሕሊና ጸሎት አሳገዋል።

5 ሰዓት ላይ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ተሸኝተው ከአሪቱ የመንግሥት የፖሊቲካ አካላትና ከሕዝባውያን ማኅበራት ተወካዮች ጋር ተገናኝተ የርእሰ ብሔሩ ለቅዱስ አባታችን የእንኳን ደህና መጡ መእክት ተደምጦ እንዳበቃም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችድስኮ በመቀጥል መልእክት በማስደመጥ ግኑኝነቱ ተጠናቋል።

አምስት ሰዓት ከ 45 ደቂቃም ከካውካሱስ የምስልምና ሃይማኖ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ጋር ክሌኣዊ ግኑኝንት ካከናወኑ በኋላ ልክ ስድስት ሰዓት ላይ ከሁሉም በአገሪቱ ከሚገኙት ከተለያዩ ሃማኖት መሪዎች ጋር ተገናኝተው ሰላምታን ተለዋውጠው የአዘርበጃን ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.