2016-09-29 13:31:00

የቅዱስ ቪንሰንት ዲ ፖል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመስከረም 27/2016 በመላው ዓለም ተከበረ።


በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 27/2016 የቅዱስ ቪንሰንት ዲ ፖል ዓመታዊ በዓል መከበሩ እና በእለቱ ይህ ታላቅ ለድሆች አብነተ የነበረ ቅዱስ በጊዜው የፈጸማቸው ተግባራት ተዘክረው እንደ ነበረ ታወቀ።

የመላው የላዛሪስት ማህበርን ለሚቀጥሉት 6 ዓመታት በዋና አለቃነት ለማስተዳደር በቅርቡ የተመረጡት ክቡር አባ ቶማስ ማቪሪች በእለቱ በአጠቃላይ ኩሪያ በሚገኘው የጸሎት ቤት በዓሉን ለማክበር ካርዲናል ሮዲሄ እና የተለያዩ የላዛሪስት ማሕበር ጳጳሳት እና ካህናት በተገኙበት አስተንትኖ ሰጥተው የነበረ ሲሆን “የማሕበራችን መስራች የሆነው ቅድሱ ቪንሰንት የላዛሪስት ማሕበር መስራች ቢቻ ስይሆን ለአለፉት 400 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን እና እንዲሁም መላው ዓለም የፍቅር መገለጫ የሆነውን በጎነትን እንዲያሳዩ ያነሳሳ ታላቅ ቅዱስ እንደ ነበረ” አስታውሰዋል።

ይህም መልካም ተግባር እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1617 መሰረቱን በፈረንሳይ ሀገር አድርጎና ቅዱስ ቪንሰንት መንፈስዊ ለውጥን ከማድረጉ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን የገለጹት የማሕበሩ የበላይ አለቃ ክቡር አባ ቶማስ ማቪሪች ይህም ቅዱስ ቪንሰንት ሕይወት መንፈስዊ ለውጥን እንዲጎናጸፍ በቀዳሚነት የረዳው በፈረንሳይ ፎሌቪል በነበረበት ወቅት በሕዝቡ ላይ የተመለከተውን መንፈሳዊ ድህነት በቀዳሚነት የሚገለጽ መሆኑን አስረድተዋል።

የቅዱስ ቪንሰንት ሕይወት እንዲቀየረ የረዳው  ሁለተኛው  አጋጣሚ የተፈጠረው በሻቴሎን ለስ ዶበስ የተመለከተው ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ ድህነት መሆኑን ገልጸው ከተለያዩ ተባባሪ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ከሚያከናውኑ ሰዎች ጋር በመተባበር የሕዝቡን መንፈስዊ እና ቁሳዊ ድህነትን መዋጋት መጀመሩንም አውስተዋል።

ቅዱስ ቪንሰንት እነዚህን ማለትም የመንፈሳዊና የቁሳዊ ድህነትን በመዋጋት ላይ ባለበት ወቅት የእርሱንም ሕይወት ይገመግም እንደ ነበረ እና በመጨረሻም “ከሁሉም በላይ ሊታዘንለት የሚገባው ድሃ እኔው እራሴ ነኝ” በማለት የእርሱን መንፈስዊ ድህነት መመርመር መጀመሩን የገልጹት ከቡር አባ ቶማስ ቅዱስ ቪንሰንት ከእዚህ ልምዱ በመነሳት ማንኛውም ተግባራቱ ጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት እንደ ሚገባው ተገንዝቦ ጠንክሮ በመስራቱ “ታላቅ የፍቅር ሥራ አባት ሊባል” መቻሉን ገልጸዋል።

ቅዱስ ቪንሰንት እነደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1581 በፈረንሳይ ሀገር የተወለደ ሲሆን በመስከረም 27 1660 ከእዚህ ዓለም በሞት የተለየ ነገር ግን መልካም ሥራው እርሱ በመሰረታቸው የተለያዩ መንፈስዊ ማሕበራት በቀጣይነት ልድሆች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.