2016-09-29 11:25:00

ቅዱስነታቸው "ማንም ሰው ከእግዚአብሔር የምሕረት አድማስ ውጭ ሊሆን አይችልም" አሉ።


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 28/2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት ጠቅላላ አስተምህሮ ዋንኛው ትኩረቱን አድርጎ የነበረው “ምሕረት እና መስቀል” በሚሉ ሁሉት ጭብጦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን “ኢየሱስ በመከራ ውስጥ በነበረበት ወቅት የተናገራቸው ቃላት አጠቃላይ ይዘት “ይቅርታ” የሚለው ቃል መሆኑን ገልጸው “ኢየሱስ ይቅር ባይ ነው! ምክንያቱም በመጨረሻው ቀን “ጌታ ሆይ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው” (ሉቃስ 23,34) ማለቱ ማረጋገጫችን ነው ብለዋል።

ይህም በቃለት ብቻ የተገለጸ ይቅርታ ሳይሆን ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ እንደ ጠቀሰው ኢየሱስ ተሰቅሎ በነበረበት ወቅት ክፋ ነገሮችን በመፈጸማቸው ምክንያት ከኢየሱስ ጋር ከጎኑ ተሰቅሎ ለነበረው ለአንድኛው ሌባ ሰው በተጨባጭ ያሳየው እውነታ መሆኑንም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“በጊዜው በመቀሉ ሥር የነበሩ የሕዝቡ አለቆች ስያደርጉት እንደነበረ ዓይነት ይህም ከጎኑ ተሰቅሎ የነበረው ሚስኪን ሰው ከጭንቀቱ የተነሳ ይሰድበው እንደነበር ገልጸው “እስቲ አንተ ክርስቶስ ከሆንክ እኛን እና እራስህን አድን!” (ሉቃስ 23,39) ይለውም እንደ ነበረ ገልጸዋል። ይህም ጩኸት የሰው ልጅ ለሞት በሚያበቃው ስቃይ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ የሚያሰማው ዓይነት የስቃይ ጩኸት እንደ ሆነ ገልጸው ከእዚህም ስቃይ ነጻ የሚያወጣው እግዜብሔር ብቻ መሆኑንም የሚያመልከት ሲሆን ስለዚህም ከእግዚኣብሔር ዘንድ የተላከ መስህ በመስቀል ላይ ሆኖ ሳያድነው ሊቀር በፍጹ እንደ ማይችል ገልጸዋል።

“ይህንን ታላቅ ምስጢር አይረዱም፣ ይህንን ትላቅ የመስዋዕት ምስጢር አለገባቸውም” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሳለ ነበር ያዳነን” ብለው ሁላችንም በየቀኑ በሕይወታችን ከሚያጋጥሙን ነገሮች ጋር በንጽጽር በምንመለከትበት ወቅት በመስቀል ላይ ሆኖ መሰቃየት ምንኛ ከባድ እንደ ሆነ ሁላችንም እናውቀዋል ካሉ ቡኋላ እርሱ ግን በእዚህ ታላቅ መስቀል ላይ እያለ፣ በእዚያ ታላቅ ስቃይ ውስጥም እያለ በጽናት አድኖናል በእዚያም ታላቅነቱን በማሳየት ይቅርታን አድርጎልናል ብለዋል።

“ከመስቀሉ ላይም ሆኖ ፍቅሩን ለግሶናል የደኅንነታችንም ምንጭ ፈለቀ” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሁለት መንጀለኞች መኋል የተሰቀለው ንጹህ ሰው ከመሞቱ በፊት የእግዚኣብሔር ደኅንነትን ለሚጠባበቀው ሰው በስቃይ ውስጥ ቢኖርም እንኳን በእግዚኣብሔር ምሕረት እንዲዳሰስ አድርጎት ነበር ብለው ይህም የሚያሳየው የእግዚኣብሔር ምሕረት ማንንም ሳያገል ለሁሉም የሚሰጥ ስጦታ መሆኑን ጠቅሰው ለእዚህም ነው ይህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ለሁሉም ማለትም ለጥሩዎች ይሁን ለክፉዎች ለጤነኞች ይሁን ለሚሰቃዩት ምሕረትን የማስገኘት ብቃት አለው የምለው ብለዋል።

“ይህ የፀጋ እና የምሕረት ዘመን ማንም ሰው ቢሆን ከኢየሱስ ፍቅር ውጭ ሊሆን እንደ ማይችል ያስታውሰናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሆስፒታል በአልጋ ላይ ለሚገኙ፣ እስር ቤት ተከርችሞባቸው ለሚገኘው፣ በጦርነት ወጥመድ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ የምላችሁ ነገር ቢኖር ‘ወደ ኢየሱስ መስቀል ተመለከቱ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፣ በመስቀላችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ነው፣ ለሁላችንም እራሱን እንደ አዳኝ መስዋዕት አድርጎ ያቀርባል ብለው የወንጌል ቃል ኋይል ልባችሁን ዘልቆ እንዲገባ ፍቀዱለት እርሱም ያጽናናችኋል፣ ተፋን ይሰጣችኋል ማንም ሰው ከእርሱ የምሕረት አድማስ ውጭ አለመሆኑን  በእርግጠኝነት መናጋር እንችላለን ብለዋል።

እናንተ. . . አባታችን እስቲ ይንገሩን. . . “በጣም አጸያፊ ነገር የፈጸመ ሰው ይቅርታ ሊደረግለት ይችላል ወይ”? ብላችሁ ልትጠይቁኝ ትችሉ ይሆናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አዎ እርግጥ ነው! ማንም ቢሆን ከእርሱ የምሕረት አድማስ ውጭ ሊሆን አይችልም . . . በመጸጸት ወደ ኢየሱስ የሚቀርቡ ሁሉ በእርሱ የምሕረት እቅፍ ውስጥ ይገባሉ ብለዋል።

“ከላይ የተጠቀሰው ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት መካከከል የአንድኛውን እና ክፉ የተባለውን ወንጀለኛ ታሪክ ያሳየናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁለተኛው ግን እንደ መልካም የተቆጠረ ወንጀለኛ ሰው የተናገራቸው ቃላት ድንቅ ሊባል በሚችል መልኩ መጸጸቱን የገለጸበት እና በምን ዓይነት መንገድ ኢየሱስን ይቅርታ መጠየቅ እንደ ሚገባን ያስተማረን አጋጣሚ እንደ ነበረ ገልጸዋል። ይህ መልካም የተባለው ወንጀለኛ “አንተ ደግሞ በሞት ፍርድ ላይ እያለህ እንኳን እግዚኣብሔርን አትፈራምን? (ሉቃስ 23,40) በማለት ፈርሃ እግዚኣብሔር እንዳለው መግለጹ የመጀመሪያው የመጸጸቱ ምልክት ነው ነገር ግን ይህ ማለት እግዜብሔርን የሚፈራው ልክ ልጅ አባቱን በሚፈራበት መልኩ ነበረ እንጂ እንደ አንድ ክፉ ሰው ፈርቶት እንደ አልነበር አክለው ገልጸዋል።

ይህም በእርግጥ ፍርሃት ሊባል አይችልም ነገር ግን ለእግዚኣብሔር ያለውን ክብር ያሳያል ምክንያቱም እግዚኣብሔር ስለሆነ፣ ልጅ አባቱን ስለሚያከብር ለአባቱ የሚገባውን ክብር ስጥቶ ነበር በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው ይህ መልክሙ ወንጀለኛ ሰው በእግዚኣብሔር ላይ ያለውን ከፍተኛ መተማመን የገለጸበት መንገድን መረዳት መሰረታዊ ነገር መሆኑን ገልጸው ይህም እግዚኣብሔር ኋያል መሆኑን እና ዘላለማዊ መልካምነትን የተጎናጸፈ መሆኑን ማወቅ እንደ ሚገኝበትም ጨመረው ገልጸዋል። ይህ መተማመን ለእግዚኣብሔር ቦታ እንድንሰጠው የሚረዳን እና በእርሱ ምሕረት እንድንተማመን ከፍተኛ አስተዋጾ እንደ ሚያደርግም ጨምረው ገልጸዋል።

“ይህ መልክም ወንጀለኛ ሰው ኢየሱስ ምንም ክፋት እንዳልሰራ መስክሮ ነበር” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመቀጠልም “እኛ ባደርግነው በደል ምክንያት ቅጣትን መቀበላችን ተገቢ ነው፣ ይህ ሰው ግን ምንም ጥፋት አላደረገም” (ሉቃ 23,41) በማለት ኋጥያተኛ መሆኑን በግልጽ ማመኑ በጣም ጠቅሞት እንደ ነበር ገልጸዋል።

ስለዚህም ኢየሱስ ለኋጥያተኞች  ያለውን አጋርነት ለመግለጽ ሁልጊዜም ሚሆን በመስቀል ላይ ይገኛል  በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ቅርበት አማካይነት ደኅንነትን ይሰጣቸዋል ካሉ ቡኋላ ለካህናት አለቆች እና ለመጀመሪያ ወንጀለኛ እንደ ክፉ ነገር ሆኖ የተቆጠረው ነገር ለሌሎች ግን የመዳን ምንጭ ሆኖኋል ለእዚህም ይህ መልካም ወንጀለኛ ሰው በተቀበለው ፀጋ ምስክርነትን ሰጥቱዋል፣ ይፈጸማል ተብሎ ያልታቀደው ተፈጸመ፣ እግዚኣብሔር ስለወደደን እራሱን ለመስቀል ሞት አስልፎ ሰጠ፣ የእዚህ ሰው እምነት ፍሬያማ የሆነ ድኅንነትን አስገኘለት ምክንያቱም ዓይኖቹ ለፍቅር ብሎ በተሰቀለው መስቀል ላይ አድርጎ ስልነበረ ይህ ምስኪን ኋጥያተኛ መደናን ተጎናጽፉኋል በማለት ለእለቱ ያዘጋጁት አስተምህሮ ተጠናቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.