2016-09-26 16:54:00

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ከሕግና ፍትሕ ሥርዓት ውጭ የሚተላለፉ ብይኖችና የጸረ ሕይወት ባህል አወገዙ


ጽንስ ማስወረድ ግብረ ሽበራ የመሳሰሉት በጠቅላላ በሕይወት ላይ የሚሰነዘሩት እኩይ ተግባሮች ሐጢአቶች ናቸው። ማንኛውም ጸረ የሰው ልጅ ሕይወት የሆነ ተግባር ሁሉ ወደ መለኰታዊ ፍትሕ የሚጮኽ የስሞታ እንባ ነው የሚል ቅዉም ህሳብ የተኖረበት የፊሊፒንስ ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባከበረቸው የአዛኚቱ ማሪያም አመታዊ በዓል ምክንያት ማስተላለፉ ኢሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት አስር ሳምታት ውስጥ ብቻ 1,400 በአደንዛዥ እጸዋት አዟሪነት የተጠረጠሩ በአገሪቱ የመከላከያ ኃይል አባላት እጅ የተገደሉ የሚገኙባቸው በጠቅላላ 3,500 ዜጎች መገዳላቸውና በተጨማሪም እ.ኤ.አ. መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በዳቫኦ ከተማ በቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ሌሎች 60 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥

በዚህ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሶክራተስ ቪለጋስ ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት፡ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ሊጣስ አይገባውም፡ ምንም’ኳ አመጽና ቅትለ ምክንያት ወንልጀና ሐጢአት የሚያስከትለው ጠባሳ ቢኖርም መቼም ቢሆን ልኡል የሰው ልጅ የሕይወት ክብር ጸድሎ የሚታይ ነው እንዳሉና እ.ኤ.አ. ወርሃ ነሐሴ ማብቂያ የሊንጋየን ዳጉፓን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ቪለጋስ በአገሪቱ ሮድሪጎ ዱተርተ ርእሰ ብሔር ሆነው ከተመረጡበት ቀን ወዲህ የሚታየው ክሕግና ፍትሕ ስርዓት ውጭ በቀጣይነት አደንዛዥ እጸዋት አዟሪዎች ናቸው በሚባሉት ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ቅትለት እንዲቆም ጥሪ አስተላፈው እንደነበር ያስታወሰው ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግሎት አያይዞ ብፁዕነታቸው የሟች ቤተሰቦች ለመበቀል እንዳይነሳሱ አደራ ብለው እየተፈጸመ ያለው ቅትለት ከፍትሕና ሕግ ጋር እንዳያገናኙትም ኣሳስበው እንደነበር በማስታወስ፥

ለእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት ያልተገባ ሕይወት የለም

የአደንዛዥ እጸዋት ሱሰኞች ቅትለት ሳይሆን ድሕነትና ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ወንድሞቻችን ናቸው። እርዱኝ የሚሉ ህሙማን ናቸው። ምንም’ኳ ግብረ ገብ ያልተካነ ሕይወትም የሚኖሩና የሰው ልጅ እንደ ውዳቂ የሚመለከታቸውም ቢሆን የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኙ ፍቅር በበለጠ ለእነርሱ ነው። ለእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት ያልተገባ ማንም ሰው የለም። ስለዚህ የአደንዛዥ እጸዋት ሱሰኞች ዕድል ሊሰጣቸውና ወደ መዳን እንዲያቀኑ መደገፍ ይኖባቸዋል። ምክንያቱም በጥገኝነታቸው ምክንያት ጤነኛ ነኝ ባዩ ዓለም ከመኖር በታችን በሕይወት እያሉ እንደ ሞት የሚያስባቸውና የሚያገላቸውም ቢሆንም እነዚህ ወንድሞቻችን ከወደቁበት ለመነሳት ፍላጎቱ እንዳላቸው በማሳየት ለታደሰ ሕይወት ዝግጁነት ሊኖራቸው ይገባል፡ ሁሉም ለሕይወት እንጂ ለሞት አልተፈጠረም እንዳሉ ያመልክታል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.