2016-09-26 15:47:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ክርስቲያኖች ለጎሬቤቶቻቸው ፍላጎት በርኋቸውን ዝግ ማድረግ አይገባም አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 25/2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በተነበበው ወንጌል ላይ ትኩረቱን አድርጎ የነበረ እና ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ እና እንዲሁም ከሁልም በላይ ስጋቶችን ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑን ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ተገለጸ።

በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 6.20 በተወሰደው እና ስለ ሃብታሙ ሰው እና በበሩ ስር ተቀምጦ ሰለ ነበረው ድኋው ዓልዐዛር በሚያወራው ምሳሌ ላይ ተመስርተው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እውነታውን በምናይበት ወቅት ይህ ሃብታም ሰው በማንም ላይ ክፉ ነገር አልፈጸም እንዲሁም መጥፎ ሰው መሆኑን የሚያሳይ ነገርም የለም ነገር ግን ሰውነቱ በቁስል ከተወረረው ከዓልዐዛር የበለጠ በሽታ ነበረው፣ በከፍተኛ ሁኔታ በእውርነት በሽታ ይሰቃይ ነበር ምክንያቱም እርሱ ከሚኖርበት የድግስ እና ጥሩ የመልበስ ዓለም አልፎ አሻግሮ መመልከት ተስኖት ስለነበረ መሆኑን ገልጸዋል።

ከእርሱ ቤት ውጭ የሚከናወኑ ነገሮች ምንም ሰለማያሳስቡትና አይመለከተኝም ብሎ ያስብ ስለነበር እርሱ ከሚኖርበት ቤት አሻግሮ ዓልዐዛርን መመልከት እንኳን አልቻለም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአይኖቹ ችግሩን ባለማያቱ ምክንያት ልቡም ታውሮ ነበር ይህም ዓለማዊ ተግባሩ ነብሱን አደንዝዞት እንደ ነበር ገልጸው የእዚህ ዓለማዊ መንፈስ መልካም ነገሮችን እንደ ሚውጥ እና ፍቅርን እንደ ሚያጠፋ “ጥቁር ጉዳጓድ ነው” ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ለእራሱ እና በእርሱ ይጠቀም ስለነበር መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።

ብዙን ጊዜ በዓይነስውረንት  የሚሰቃይ ሰው “የተዛባ ባሕሪን” እያዳበረ ይመጣል፣ ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን፣ ከፍተኛ የሆኑ ቦታ ያሉትን፣  የዓለምን አድናቆት ያተረፉትን ሰዎች በማድነቅ እይታውን እንደ ዓለዐዛር ካሉ ብዙ ድሆች እና ጌታ የሚወዳቸው ነገር ግን በስቃይ ላይ ከሚገኙ ሰዎችን መመልከት ግን ይሳነዋል ብለዋል።

ነገር ግን  ዓለም ያገለላቸውን እና የተረሱትን ሰዎች ጌታ በትኩረት ይመለከታቸዋል በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በምሳሌዎቹ ከጠቀሳቸው መኋከል ዋንኛው ዓለዐዛር እንደ ነበረ እና ስሙም  “እግዚአብሔር ይረዳል” የሚል ትርጓሜ እንደ ነበረው አውስተው እግዚአብሔር አልረሳውም በመንግሥቱ በተዘጋጀው ግብዣ ላይ ከአብርሐም እና ተሰቅይተው ከነበሩ ሁሉ ጋር አብሮ እንዲገኝ አድርጎታል ብለዋል።

ነገር ግን በምሳሌው ውስጥ የተጠቀሰው እና ስም እንኳን ያልተሰጠው ሃብታሙ ሰው በተቃራኒው ተርስቶ የነበረ መሆኑን አውስተው ለእራሱ ብቻ የሚኖር ሰው ታሪክ መጻፍ አይችልም ክርስቲያኖች ግን ታሪካቸውን መጻፍ ይጠበቅባቸዋል ብለው ይህንንም ለማድረግ ከእራስችን መውጣት እንደ ሚጠበቅብን አክለው ገልጸዋል።

ኢየሱስ ባቀረበው ምሳሌ ውስጥ ሁለት ንጽጽሮችን እናያለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስሙ ያልተጠቀሰው እና ማሸብረቅ ይወደ የነበረው ሰው በተመለከተ የተጠቀሰው ስለእርሱ ፍላጎቶች እና መብቶች ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ አልፎም ተርፎም ሞቶ በነበረበት ወቅት እንኳን መረዳት  እንዳለበት እና የምያስፈልገው ነገር እንዲደረግለት በአጽኖት ይጠይቅ እንደ ነበረ ገልጸው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ድሃው ዓለዐዛር በትላቅ ክብር አቀባባአል እንደ ተደረገለት እና ከአፉም ምንም አይነት ማጉረምረም፣ ተቃውሞ ወይም ተመሳሳይ የሆነ የተማጽኖ ንግግር እንዳልወጣ ገልጸዋል።

ይህ ለእኛ በጣም አስፈላጊ አስተምህሮ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ ኢየሱስ ቃል አገልጋዮች የተጠራነው ስለውጫዊ ገጽታችን እና ስለእራሳችን ክብር ልንመሰክር እንዳልሆነ መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን ማወቅ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም እኛ በአደጋዎች እና ልዩነቶች በሚፈጠሩበት ወቅት የምንደሰት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዳሉ ነቢያት አይደለንም፣ በእራሳችን ዙሪያ በሚታዩ ነገሮች ብቻ የተዘጋን ሰዎች አይደለንም፣ በማህበረሰባችን፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በሁሉም ነገር ላይ እና በማንም ሰው ላይ በምሬት ፍርድ የምንፈርድ አይደለንም፣ በጠቅላይ ዓለምን በአሉታዊ ፍርድ ልንበክላትም አይገባም ለእግዚአብሔር ቃል ቅርብ የሆነ ሰው ሁሉ አሉታዊ አስተሳሰብን ልያስወግድ እንደ ሚገባም መክረዋል።

የኢየሱስን ተስፋ የሚመሰክር ሰው ሁሉ ደስተኛ እና አሻግሮ መመልከትም ይችላል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች አድማስ ይከፈትላቸዋል፣ ምንም የሚያግዳቸው ግድግዳ አይኖርም አሻግረው ረጅም እርቀት መመልከት ይችላሉ ምክንይቱም ከክፋት  እና ከእራሳቸው የግል ችግር  ባሻገር መመልከት እንዳለባቸው ስለሚያውቁ ነው በለዋል።

በተመሳስይ መልክም በቅርበት የጎረቤቶቻቸውን ፍልጎት ለመረዳት ጉጉት ያሳያሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር ዛሬ የሚጠይቀን ይህንኑ ነው ዓልዐዛርን የመሳሰሉ ሰዎች በሚያጋጥሙን ወቅት ሁሉ ልንረበሽ እና “ነገ መጥቼ እረዳኋለሁ፣ ዛሬ ግን ጊዜ የለኝም፣ ነገ እረድኋለው” የሚለውን በማሰውገድ ከችግራቸው ይወጡ ዘንድ በስቸኳይ መፍትሄን መፈልግ እና ማገዝ አስፈላጊ ነው ምክንያቱ ሌላውን ለማገዝ የሚናባክነው ጊዜ ለኢየሱስ እንደ ባከነ ስለሚቆጠር መሆኑን ገልጸው ይህም የሚያተርፍልን ለሰማያዊ ሃብታችን የሚያበቃን እና በምድር በፈጸምነው በጎ ሥራ የሚሰጠን ፍቅር መሆኑን አበክረው ከገለጹ ቡኋላ የእለቱን ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.