2016-09-20 13:50:00

ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች እርሳቸውን በእምነት ብርሃን ውስጥ ለይሳድጉ እንደሚገባ ገለጹ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 19/2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባስተላለፉት ስብከት ሃብታም እና ኋይለኛ በሆኑ ጎረቤቶችህ ላይ አትቅና ወይም አታሲር ይልቁንም እራስህን በእምነት ብርሃን ሕይወትህን ለማሳደግ ሞክር ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል (8,16-18) በተወሰደው ምንባብ ላይ መሰረታቸውን አድርገው የእምነት ብርሃናችንን የመደበቅያ የተለያዩ ዘዴዎች መኖራቸውን በሚያወሳው ሀረግ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በቅናት እና በክርክር እንዲሁም በጎረቤቶቻችን ላይ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ መሞከር ወይም በቀላሉ ዛሬ እኛ ማድረግ የሚገባንን መልካም ነግሮች ለነገ ማስተላለፍ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል።

“የእምነት ብርሃን” አሉ ቅዱስነታቸው “እያንዳንዳችን በተጠመቅንበት ወቅት ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ስጦታ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ በመጀመሪያው ምዕተ-ዓመት ለነበሩ ክርስቲያኖች ጥምቀት “ብርሃን” ይሆናቸው እንደ ነበር አስታውሰው ይህም ቃል በአንድ አንድ የምስራቃዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ዘንድ ጥምቀት እሰክ ዛሬ ድረስ “ብርሃን” ብለው እየጠሩት እንድሚገኝም አስታውሰዋል።

ኢየሱስ ሕዝቡን መብራታቸውን መደበቅ ተገቢ እንዳልሆነ አስጠንቅቆኋቸው እንደ ነበር ያስታወሱት ቅዱስነታቸው መብራታችንን የምንደብቅ ሰዎች ከሆንን ለብ ወዳለ ክርስትያንነት እንለወጣለን፣ ጎረቤቶቻችን ከሚያቀርቡልን የድረሱልኝ ጥሪ አንስቶ በተለያዩ ብዙ መንገዶች መብራታችንን በመደበቅ ክርስትያንነታችንን አደጋ ላይ እንጥለዋለን፣ በፍጹም መልካምን ለማድረግ ነገር ለመፈጸም ቀን አትቁረጥ፣ ፍትህንና መልካም ነገሮችን ለማድረግ ነገሮች ጫፍ ላይ እስኪደርሱ አትጠብቁ ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ለጎረቤቶቻቸው መልካምን ነገር ከማድረግ ይልቅ ክፋትን ለሚመኙ ሰዎች በአጽኖት እንደ ገለጹት በተጣለባቸው እምነት ላይ ተመስርተው ለሚቀርብላቸው ጥሪ መልስ መስጠት እንደ ሚገባቸው ገልጸው በጎረቤቱ ላይ ክፉ ነገርን ለማድረግ የሚያውጠነጥን ሰውና በተደራጀ የወንጀል ቡድን የሚመካ ሁሉ በወንጄለኛው ቡድን ብርሃን የእምነትን ብርሃን እንዲዋጥ ያደርጋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አስከትለውም “ክርክር” ወደ ፈተና የሚያስገባ ነገር መሆኑን ገልጸው ወደ ተወሳሰብ ነገር ከመግባት ይልቅ በይቅርታ ማለፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኋያላን፣ ውጤታማ ወይም ጠበኛ በሆኑ ሰዎች ላይ መቅናት ተገቢ አለመሆኑን በድጋሜ ገልጸው ገልጸው አምላክ የሚያስቀይመውንና መልካም የሆኑትንም ጓደኞቹ እንዲሆኑ እንደ ሚጋብዛቸውም ጠቁመው በእነዚህ ነገሮች ላይ ማለትም በስልጣን እና በሐብት የምንቀና ከሆነ የተሰጠንን ብርሃን በተዘዋዋሪ እንደ መደበቅ ይቆጠራል ብለዋል ።

በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ያለውን ቃል በመድገም እና አጽኖት ስጥተው ‘የብርሃን ልጆች’ እንድንሆን እና በአደራ የተሰጠንን ብርሃን በአልጋችን ሥር ከመደበቅ ይልቅ መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን በአጽኖት ገልጸው በጥምቀት የተቀበልነው መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ብርሃናችንን በልጋ ሥር እንድንጠብቅ የሚያደርጉንን ምጥፎ ባሕሪያትን እንድንተው ይረዳን ዘንድ እና በምትኩም የወንድማማችነት፣ የየዋህነትን፣ የእምነት እና የተስፋ እንዲሁም የትግስትን እና የመልካምነትን ብርሃን ይዘን እንድናድግ ይረዳን ዘንድ ልንለምነው ይገባል ብለው ስብከታቸውን አጠንቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.