2016-09-16 16:26:00

በዚህ በምህረት ዓመት የመላ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ኢዮቤልዩ ቀን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በዚህ እየተኖረ ባለው የምህረት ዓመት ምክንያት በመላ የዓለማችን አህጉራት የሚገኙትን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ለኢዮበልዮ ቀን አገረ ቫቲካን እንዲገኙ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት በተለያዩ አገሮች የሚገኙ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡካን አገረ ቫቲካን መግባታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

በዚህ አጋጣሚም የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ወቅታዊው ዓለምና ወቅታዊ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚል ርእሰ ጉዳይ ሶፊያ ለተሰየመው መንበረ ጥበብ ሊቀ መንበር የቲዮሎጊያ ሊቅ የኔታ አባ ፒየሮ ኮዳና በተጨማሪም ከሁለቱ የጾታዊ ስሜት  ወንድና ሴት ከሚለው ባህርያዊ የጾታዊ ማንነት ውጭ በአሁኑ ወቅት ኅብረ ጾታዊነት የሚል ትምህርቱና የዚህ አዲሱ ባህል መንስኤውና ክትለቱ። አዲስ ባህላዊ ተግዳሮት በሚገባ ገጥሞ የተሟላ መልስ እንዴት ማቅረብ በሚል ርእስ የተመራ ጥልቅ አስተምህሮ ጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ የመሰረታዊ ሥነ ምግባር መምህር ፕሮፈሰር ክቡር አባ ሮበርት ግሃል አስተምህሮ በሚያቀርቡበት ዓውደ ጉባኤ እየተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ዓውደ ጉባኤው በመላ አህጉራት ዓለም የሚገኙት 106 የማዕርገ ሊቀ ጵጵስና ክብር ሌሎች አምስት ደግሞ የኔታ ማእርግ ያላቸው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን የጠራ ሲሆን።  በጠቅላላ 108 የቅድስት መንበር ሐርያዊ ልኡካን የሚያሳትፍ መሆን ሲገባው ከእነዚህም ውስጥ ሁለት ሐዋርያዊ ልኡካን በተለያየ ምክንያት በጉባኤ ሊገኙ ባለ መቻላቸው አገረ ቫቲካን የገቡት 103 ሐዋርያዊ ልኡካን መሆናቸው አየቅድስት መንበር የዜናና ምኅተም ክፍል መግለጫ ያመለክታ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ይኸንን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን የጠራው ዓውደ ጉባኤና ኢዮቤዩ ቀን የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በአገረ ቫቲካን ቤተ መዘምራን በተሰየመው ቤተ ጸሎት በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ መጀመሩ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ በማስታወስ፡ ከቅዳሴው ሥነ ሥርዓት በኋላም ተገባእያኑ ጧት ጳውሎስ የጉባኤ አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው በሲኖዶስ አዳራሽ ጧትና ከሰዓ በኋላ ቀጥሎ በሚካሄደው ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ የዕለቱን መርሃ ግብር አጠናቀው እንዳበቁም ቅዱስ አባታችን የተሳተፉበት የእራት ማእድ መቋደሳችው ጠቅሶ፡ እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጋባእያኑ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ቢሮ አበይት አካላት ጭምር ያሳተፈ በቡድን በተከፋፈለ የክብ ጠረጴዛ ውይይት ተሳትፈዋል። ከሰዓት በኋላ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት ለሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን በይነ ሃማኖቶች፥ ከምስልምና ሃማኖት ጋር የሚከናወነው የጋራው ግኑኝነት በሚል ርእስ ሥር አስተምህሮ ተሰጥቶ እንዳበቃ ተገባእያኑ በሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅርብ ተባባሪ ከሆኑት አበይት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ባለ ስልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ሊቀ ጳጳሳትና እንዱሁም በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መግሥታት ጋር በአገረ ቫቲካን ቤተ መዘክር ባለው የጉባኤ አዳራሽ የተገናኙ መሆንቸውም የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ እ.ኤ.አ. መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም.  አገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መላ 106 ተጋባያንና ሌሎች 40 የቅድስት መንበር ልሂቅ ሐዋርያዊ ልኡካን በማካተት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልክ ዘነግህ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተሳትፈው እንዳበቁም ቀጥሎ የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፒየርአንጀሎ ስኵይሪ የሚሰጡት መንፈሳዊ አስተንትኖ ይቀርባል በሮማ ሰዓት አቆጣጠር  10 ሰዓት በዚህ እየተኖረ ባለው የምህረት ዓመት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮ ባዚሊክ በተከፈተው ቅዱስ በር በማለፍ ልክ 11 ከሩብ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል ተቀብለው እንዳበቁም ልክ 1 ሰዓት ቅዱስ አባታችን በተገኙበት የምሳ ግብዣ በመቋደስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ኢዮቤልዩ ቀን እንደሚጠናቀቅ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.