2016-09-13 11:47:00

ቅዱስነታቸው አዲስ ከተሾሙ ጳጳሳት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ጳጳሳቱ የተሰጣቸውን አላፊነት እንዳይዘነጉ አሳሰቡ።


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 09/2016 በቅርብ ጊዜ የማዕረገ ጵጵስናን ከተቀበሉ ጳጳሳት ጋር በተገናኙበት ወቅት መከፋፈል፣ ሀሜት እና ገንዘብ በሰይጣን መዳፍ ውስጥ የሚገኙ ነገሮ መሆናቸውን ማወቅ አስፈላጊ እንደ ሆነ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

በቅርቡ የጵጵስናን ማዕረግ የተቀበሉ ጳጳሳት እንዲያገለግሉ ወደ ተመረጡበት ሀገር ከመሄዳቸው በፊት ስብከተ ወንጌል ለኋዛብ በተሰኘው ማሕበር አማካይነት የተዘጋጀውን የእነጻ ትምህርት ካጠናቀቁ ቡኋላ ከቅዱስነታቸው ጋር ቆይታን አድርገው የነበረ ስሆን  ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንኙነቱ ወቅት እንዳሳሰቡት እያንዳንዱ ጳጳስ የተጠራው የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመመስከር እና መልካም ምሳሌን በሕይወታቸው በማሳየት ሕዝቦችን ለመንከባከብ እና ምሕረትን ለማምጣት መሆኑን በአጽኖት ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በግንኙነታቸው ወቅት አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት ከተለያዩ እና ሩቅ ከሆኑ ሀገራት እንደ መምጣታችው መጠን በእዚህም ረገድ ወደ የሀገራችው በምትመለሱበት ወቅት የስብከተ ወንጌል ተግባራትን በቀዳሚነት የማከናወንን ኋላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል።

“መዘንጋት የለለባችሁና ዋንኛው ተግባራችሁ መሆን የሚገባው ከካህናቶቻችሁ የሚቀርብላችሁን ጥያቄ እና ፍላጎቶቻቸውን  በአፋጣኝ መመለስ እንደ ሚገባችሁ ማወቅ ነው” ብለው “ማንኛውንም ጉዳት ከምያባብሱ እና የወንጌል ተልዕኮን ከምያደናቅፉ  ሰይጣናዊ ተግባራት መታቀብ ይኖርባችዋል” በማለት በአጽኖት አሳስበዋል።

ማንኛውም ሚስዮናዊ ጳጳስ እረኛ እንደ መሆኑ መጠን ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን የሚገባው የጠፉትን በጎች በመፈለግ ወደ በወንጌል ወደ ሚገኝ ደስታ መመለስ መሆን እንደሚገባው መሆኑን አስታውሰው በተጨማሪም ኢየሱስን ወደ ማያውቁት እና እየሱስን ለካዱት ሰዎች ሁሉ ወንጌልን ማዳረስ እንደ ሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት ይህንን የተሰጣቸውን ታላቅ ጥሪ ከሚያደናቅፉ ነገሮች መቆጠብ እንዳለባቸው ለጳጳሳቱ በድጋሚ አሳስበው በተለይም ደግሞ ወደ ሰይጣን መንገድ የሚመሩ መሳሪያዎች እና ቤተ ክርስቲያንን ከሚያፈርሱ ተግባራት መቆጠብ እንደ ሚኖርባቸው በአጽኖት ገልጸዋል።

“ሰይጣን ሁለት ቀንደኛ የሆኑ መሳሪያዎች አሉት የመጀመሪያው ልዩነትን መፍጠር የሚያስችለው መሳሪያ ነው፣ ቀጣዩ ደግሞ ገንዘብ ነው” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሰይጣን በኪሳችን በኩል ሰተት ብሎ በመግባት አንደበታችንን በመጠቀም ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ ይከተናል ይህም ደግሞ ወደ ሚያሸብር የሀሜት ስሜት ውስጥ ይጥለናል ብለዋል።

“ሀሜተኛ ሰውን እንደ አሸባሪ ልንቆጥረው እንችላለን ምክንያቱም ሀሜት አፍራሽ የሆነ ተገባር በመሆኑ ነው” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ቤተ ክርስቲያንን ልያፈርስ ከምችሉ ማንኛውም አይነት የልዩነት መንፈስን እንዲያስወግዱ አደራ ብለው ብዙ ልንጋፈጣቸው የሚገባን ተግዳሮቶች አሉ ነገር ግን ለእግዚአብሄር ፀጋ፣ ለጸሎት እንዲሁም ለንስኋ ምስጋና ይግባቸው እና እነዚህን ግብዐቶችን ተጠቅመን ተግዳሮቶቻችንን ማሸነፍ ግን  ይቻላል ብለዋል። 

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ አዳዲስ ለተሾሙ ጳጳሳት እንዳሳሰቡት በኋላፊነት የተሰጣቸውን የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ለካህናቶቻቸው እና ለዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ሁሉ መልካም ጥበቃ እንዲያደርጉ እና  ይህም ደግሞ የተሰጣችሁ ዋና ተግባራቸው መሆኑን መገንዘብ እንደ ሚኖርባቸው ካስገነዘቡ ቡኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.