2016-09-08 10:27:00

ቅዱስነታቸው "ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ምሕረት መገለጫ ልሆኑ ይገባል" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስነታቸው እንደ የጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 07.2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ  አስተምህሮ ለተገኙት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉት አስተምህሮ መሰረቱን በማቴዎስ ወንጌል ላይ አድርጎ የነበረ ስሆን የወንጌሉ አጠቃላይ ይዘት የኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት አጥማቂው ዩሐንስ ቀደም ሲል ጠብቆት የነበረ ዓይነት እንዳልነበር የሚያወሳ ነው።

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉትን ጠቅላላ አስተምህሮ የአማረኛ ትርጉዋሜውን እንደ ሚከተለው እናቀርባለን።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዛሬው ጥዋት የወንጌል ቃል አጥማቂው ዩሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ኢየሱስ ልኮ “ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው መስህ አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ”? ብለው እንዲጠይቁት ላካቸው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ይፈጽመው የነበረው ተግባር ዩሐንስ ጠብቆት ከነበረው ተግባር ጋር የተመሳሰለ ስላልነበረ ነው። እርሱ ጠብቆት ከነበረው የእግዚአብሔርን ፍትህ ያመጣል ከሚለው ሐስተሳሰቡ ጋር የተመጣጠነም አልንበረም።

ኢየሱስም የተላኩትን ደቀ መዛሙርት “ሄዳችሁ የምትሰሙትን እና የምታዩትን ነገር ሁሉ ለዩሐንስ ንገሩት ፣ እውሮች ያያሉ፣ አንካሶች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም የምስራች እየተሰበከ ነው” ብለው እንዲነግሩት ምልሶ ላካቸው። ኢየሱስ የምሕረት መሳሪያ መሆኑን አሳያቸው፣ መጽናናትን እና ደህንነትን ለሁሉም በማምጣት የእግዚአብሔር ፍትህን ገለጸ። እግዚአብሔር ልጁን የላከው ኋጥያተኛውን እንዲቀጣ እና ክፉ የሚሠሩትን እንዲሰባብር ሳይሆን ነገር ግን ወደ እርሱ ይመለሱ ዘንድ ወደ ንስኋ ሊጋብዛቸው እንጂ። ኢየሱስም ለዩሐንስ ደቀ መዛሙርት “በእኔ የማይሰናከለም ብጹዕ ነው” አላቸው። የእርሱ በእኛ ዘንድ በእርግጠኝነት መኖሩን እንዳንለማመድ በሚከለክሉን የእራሳችን ሐሰተኛ የሆነ የመሲህን ገጽታ ስንገነባ እና እኛ በፈለግነው መንገድ አምላክን ስንቀርጸው ነው። ብዙን ጊዜ የእራሳችንን ፍላጎት ለማስፈጸም ይረዳን ዘንድ የእርሱን ስም እንጠቀማልን፣ በችግራችን ወቅት ብቻ እንፈልገዋል፣ እንዲሁም እምነት ከራሳችን ወጣ ብለን በዓለም ውስጥ ሚስዮናዊያን እንድንሆን የሚያስተምረንን መልከታ እንዘነጋለን በአጠቃላይ ወደ ሐሳባችን እና እኛ ወደ አሻነው ነገር ዝቅ እንዳርገዋለን። የአምላካችንን ምሕረታዊ ተግባራትን እንዳንለማመድ የሚገቱን እንቅፋቶችን ለማስወገድ የገባነውን ቃል ኪዳን በድጋሚ እናድስ፣ የምሕረት ምልክቶች እና መሳሪያዎች እንድንሆን የሚያደርገንን  ጥልቅ የሆነ እምነት የሰጠን ዘንድ አምላካችንን እንለምነው። አሜን

አንባቢዎቻችን ከላይ የተጠቀሰው ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴትሮስ አደባባይ ያደረጉትን ጠቅላላ አስተምህሮ ነበር።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.