2016-09-08 10:39:00

ቅዱስነታቸው ከሕጻኑ ኢየሱስ (Banbino Gesu') የሕጻናት ሆስፒታል ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት ማሪዬላ ኤኖክ ጋር ተገናኙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 7-2016 በቫቲካን ሥር የሚተዳደረው እና ሕጻኑ ኢየሱስ ተብሎ የሚጠረው የሕጻናት ኦስፒታል ዋና ሆስተዳዳሪ ከሆኑት ማሪዬላ ኤኖክ ጋር በቫቲካን በሚገኘው የጽህፈት ቤታቸው በተገናኙበት ወቅት ሆስፒታሉ በማከናውን ላይ ያለውን ተግባር እድንቀው ለሆስፒታሉ የእራሳቸውን የግል አስተውጾ ለማበርከት ቃል መግባታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በግንኙነታቸው ወቅት ለሆስፒታሉ ዋና አስተዳዳሪ እንደ ገለጹት ለእዚህ ሆስፒታል የሚያደርጉትን ማንኛውም እገዛ አጠናክረው እንደ ሚቀጥሉ ገልጸው በአንጻሩም ይህ ሆስፒታል ከመቼው ጊዜ በላይ “ታላቅ የምሕረት ተግባር “የሚከናወንበት ቦታ እንዲሆን እንደ ሚፈልጉም ገልጸዋል።

የሕጻኑ ኢየሱስ ሆስፒታል ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ማሪየላ ኤኖክ በበኩላቸው ግንኙነቱን አስመልክተው እንደ ገለጹት የተደረገው ውይይት መግባባት የተፈጠረበት እና በቅርበት እና በጓደኝነት መንፈስ መፈጸሙ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ቅዱስነታቸው ይህ እየተከናወነ የሚገኘው መልካም ተግባር ቀጣይነት ይኖረው ዘንድ ማሳሰባቸው እንዲሁም በቫቲካን ሥር የሚተዳደሩ የበጎ አድራጎት ተቋማት በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በባንጉዊ የሚገኘውን የሕጻናት ሆስፒታል ለመርዳት ፍላጎት እንዳላቸው መገለጻቸውንም እክለው ተናግረዋል።

የሕጻነ ኢየሱስ ሆስፒታል ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ማሪየላ ኤኖክ አክለው እንደገለጹት ይህንን በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በባንጉዊ የሚገኘውን የሕጻናት ሆስፒታል ጋር እየተደርገ ለሚገኘው የእትሞሽ ግንኙነት እና በመገንባት ላይ ለሚገኘው የሕጻናት እስፔሻሊስት የሕክምና ተቋም ትምህርት ቤት ቅዱስነታቸው የግል አስተዋጾዋቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን እንደ ገለጹላቸው ግንኙነቱን አስመልክተው ለቫቲካን ሬዲዮ መገልጻቸውም ታውቁዋል።

በተጨማሪም የሕጻኑ ኢየሱስ ሆስፒታል ለስደተኞች ልዩ ድጋፍ እያደርገ መሆኑን እና ከዓለም የምግብ ድርጅት ተቋም በእንግሊዘኛ ምጻረ ቃል FAO ተብሎ ከሚትወቀው ዓለማቀፋዊው ድርጅት ጋር  እንዲሁም ከጣሊያን መንግሥት ጋር በመቀናጀት በመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ የአስተራረስ ዘዴን ለማዘመን እየሠሩ እንደ ሚገኙ የሕጻኑ ኢየሱስ ሆስፒታል ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ማሪየላ ኤኖክ በግንኙነት ወቅት ለቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የገለጹላቸው መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

የሕጻነ ኢየሱስ ሆስፒታል በሮም ከተማ የሚገኝ የሕጻናት ሆስፒታል ስሆን በተለያዩ በሽታዎች የሚሰቃዩ ሕጻናትን ተቀብሎ በማከም የሚታወቅ፣ በተለይም ደግሞ ምንም ዓይነት ገቢ የሌላቸውን የድሃ ቤተሰብ ልጆችን ከዓለም ዙሪያ በማስመጣት የሕክምና አገልግሎት በነጻ እየሰጠ እንደ ሚገኝ ይታወቃል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.