2016-09-05 15:29:00

ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ እማሆይ ቴሬዛ ወደ ቅድስና ማዕረግ ከፍ ማለታቸው እንዳስደሰታቸው ገለጹ።


እማሆይ ቴሬዛ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በነሐሴ 26.1910 የአልባኒያ ሀገር ተወላጅ ከሆኑት ቤተሰቦቻቸው  በሜቄዶኒያ ተወለዱ። የአሥራ ሁለት ዓመት እድሜን እንደያዙ እግዚአብሔር ለተለየ ዓላማ እንደ ጠራቸው ወይም እንደ መረጣቸው ተረዱ። ገና በልጅነታቸው ነበር ምሲዮናዊ በመሆን የክርስቶስን ፍቅር በአለም ሁሉ የማሰራጨት ጥሪ እንደ ተሰማቸው መግለጽ የጀመሩት።

 

የ18 አመት እድሜን እንደያዙ የወላጆቻቸውን ቤት ጥለው በጊዜው በአየርላንድ ሀገር በሚገኘው የሎሬቶ የደናግላን ማህበር በመግባት ለተወሰን ጊዜ ያህል ስለ ማሕበሩ እና ስለ ምሲዮናዊ ሕይወት መሠረታዊ ትምህርትን ከቀሰሙ ቡኋላ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 24, 1931 በምስዮናዊነት ወደ ሕንድ ሀገር ሄዱ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1931-1948 በሕንድ ሀገር በካልካታ ከተማ በሚገኘው ትምህርት ቤት በመምህርነት እና የተለያዩ አገልግሎቶችን አበርክተዋል።

ነገር ግን ከትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውጭ በየጊዜው የሚመለከቱት አስከፊ ድኅነት ሁልጊዜም ቢሆን ልባቸውን የሚነካ ጉዳይ ሆኖ የዘለቀ ስለነበረ እና መቁቋም ከሚችሉበት ደረጃ በላይ እየሆነባቸው ስለመጣ እንድ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1948 የገዳም አለቆቻቸውን ፍቃድ በማግኘታቸው የማስተማር ተግባራቸውን ትተው እጅግ በጣም ድሃ የሚባሉ የማኅበረስብ ክፍሎችን ማገልገል ጀመሩ።

ምንም እንኳን እጅግ በጣም ድሃ የሆኑ ሰዎችን ለመርዳት በጎ ፈቃድን ይዘው ቢነሱም ይህንን ዓላማቸውን የሚፈታተን የገንዘብ አቅም ችግር ገጠማቸው። እማሆይ ቴረዛ በፍተኛ ሁኔታ በእግዚኣብሔር ላይ በነበራቸውም መተማመን ይህ የገንዘብ ችግር ቀስ በቀስ መልካም ሥራቸውም እየተፈታ መምጣቱን ቀጠለ በእዚህም ምክንያት ይህንን ሥራ በሚገባ ማቀላጠፍ ያስችላቸው ዘንድ ይህንን መልካም ተግባር የሚያከናውኑ ደናግላን እና አጋሮች ስለሚያስፈልጉዋቸው የራስቸውን ማሕበር ለመመስረት አሰቡ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን በጥቅምት 7,1950 እማሆይ ትሬዛ የራሳቸውን የደናግላን ማህበር እንድያቁቁሙ በቫቲካን የሚገኘው ከካቶሊካዊው ቅድስት መንበር ፈቃድ ተሰጣቸው። የእዚህም ማኅበር አብይ ተግባር እንዲሆን የተፈለገው እራሳቸው እማሆይ ቴሬዛ የጀመሩት “የፍቅር ሉዑካን ደናግል ማኅበር” ወይም በእንግሊዜኛው missionary of charity’ መጠሪያው ሥሙ እንዲሆን ተደርጎ ዋናው ተግባሩም ማንም ሰው ሊቀርባቸው እና ልንከባከባቸው የማይፈልገውን ሰዎች ሁሉ በፍቅር ማገልገል የሚለው እንዲሆን ተደረግ።

በአሁኑ ጊዜ ይህ ማህበር በተመሳስይ ተግባራት ላይ የተሰማሩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ወንድሞችን በማኅበሩ ጥላ ሥር እየተዳደሩ በመላው አለም ተሰራጭቶ የተሰጠውን መንፈሳዊ ተግባራትን እየተወጣ ይገኛል።

እማሆይ ቴሬዛ በህይወታቸው በፈጸሙዋቸው መንፈሳዊ ተግባራት እንዲነሳሱ ያደረጋቸው ለድሆች ያላቸው ከፍተኛ ፍቅር ስሆን በተለይም በማቴዋስ ወንጌል 25, 31 የተጠቀሰው እና በመጨረሻው የፍርድ ቀን ንጉሡ በፍርድ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ “ተርቤ አብልታቹኛል፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፣ ታርዤ አልብሳቹኛል” ይሚለው የጌታን የመጨረሻ ጥያቄን በአግባቡ ለመመለስ ስንቅ የሆነ ተግባር በመሆኑ ነው።

በእዚህም ታላቅ ተግባራቸው አለም በጣም ያደንቃቸው ስለነበር 1979 የአለም ማኅበረሰብ ታላቅ ሰባዊ ተግባራትን ላከናወን ሰዎች የሚሰጠውን የኖቤል ሽልማት እያበረከቱት ለሚገኘው ከፍተኛ ሰባዊ እና መንፈስዊ አገልግሉ ተሽለሚ ሆኑ።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.