2016-09-05 16:24:00

ቅዱስ አባታችን፥ እናቴ ቅድስት ተረዛ ገና ካልተወለደ እስከ እንደ ጥራጊ የሚቆጠረው ሕይወትን በሙሉ ያፈቀረች


እናቴ ተረዛ ሊገመት በሚያዳግት በከፋ ድኽነት ሥር ለሚገኘው የካልኩታ ሕዝብ ቅድስት፡ እ.ኤ.አ. መስከረመ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. እናቴ ተረዛ በመላይቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሰረት ቅድስት ተብላለች። ቅዱስነታቸው ለእናቴ ተረዛ ቅድስና ለማወጅ ከመላ ዓለም አገሮች ሊባል ይቻላል በተለይ ደግሞ ከአልባኒያና ክህንድ የመጡ በብዛት የሚገኙባቸው በጠቅላላ 120 ሺሕ ምእመናን የተሳተፉበት በ70 ብፁዓን ካርዲናሎች 400 ብፁዓን ጳጳሳት 1,700 ካህናት ታጅበው በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው፥ ብፅዕት ተረዛ ዘካልኵታ ቅድስት እንልሻለን በማህደረ ቅዱሳን ቅድስት ስንል እንደነጋለን የሚለውን የቅድስና አዋጅ ቅጽ ነበው እንዳበቁ በአጸደው የተሰበሰበው ሕዝብ በሞቀ ጭብጨባ ምስጋና ለእግዚአብሄር ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ስብከት አዲሲቷ ቅድስት ተረዛ ዘካልኵታ የመለኮታዊ ምኅረት ቻሪ ብለው በመግለጥ ለሁሉም በማስተናገድ ካልተወለደው እክሰ ተወለደው እስከ ተናቀው በኅብረተሰብ ዘንድ እንደ ጥራጊ ለሚታሰበው ሕይወት ሁሉ በመላ የሕይወት ጠበቃ በመሆን፡ ማደሪያ አጥተው መጠለያ አጥተው በጎዳና ተዳዳሪነት ለሚገኙት ቅርብ በመሆን ጎንበስ ብላ በማንሳት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩም ሳይቀር ቅርብ በመሆን ሕይወቷን ለድኾች ፍቅር በማድረግ የኖረች። አሁንም በዓለማችን ብዛቱ ከፍ እያለ ላለው ለተናቀው ሕይወቷን የሰጠች ቅድስት።

ገና ያልተወለደው ከለላ የሚያሻው የሕጻናት የድኾች በጠቅላላ የሕይወት ጠበቃ። ስለ የሰው ልጅ ሕይወት ክብር በዓለም ኃያላን በሚባሉት ፊት ቆማ በመጣበቅ ድምጽ ለሌለው ድምጽ ምክንያቱን በሚያሰሙት ድምጽ በድኾች በተናቁት ፊት ድኽነት ለመስፋፋቱ ምክንያት ከሆኑት ግድፈታቸውንና ወንጀለኝነታቸውን ሳይቀር ግልጥ አድርገው ከተጠያቂነት ሊሸሹ በማይችሉት ኃያላኑ ፊት ቆመው ያስተጋቡ። ሆኖም የእግዚአብሔር ምሕረት ለአገልግሎት ሥሪታቸው ሁሉ የሚያጣፍጥ ጨው በማድረግ ያንን ጨለማ ድኽነቱ መሮት እንባውንና ስቃዩን ሲገልጥ ዝምታ ለሚሰጠው በድንግዝግዝ ላለው ዓለም ብርሃን ያደረጉ።

የእናቴ ተረዛ ተልእኮ የከተሞቻችን የአገሮቻን የዓለማችን ጥጋ ጥጉ ክልል ጥጋ ጥጉ የኅልውና ክልል አማካኝነት የተገለጠ አሁንም የእግዚኣብሔር ልዩ ፍቅር ለድኾች መሆኑ ርቱዕ ምስክርነ ሆኖ እየቀጠለ ነው። ይህች አብነት የሆነችው የተወፈየች ለሁሉም የበጎ አድራጎት ግብረ ሠናይ አባላት ዛሬም አብነት ነች። እርሷ ለእናንተ የቅድስና አርአያ ነች። እርግጥ ነው ቅድስት ተረዛ ብለን ለመጥራት ያልተለመደ ሊሆንብን ይችላል ምክንያቱም ቅድስናዋ እጅግ ለእኛ የቀረበ ቅድስና በመሆኑ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡ ማድረ ተረዛ ብለን መጥራቱ እንደምንቀጥልበትም ይሰማኛል። ይህች የምኅረት አገልጋይ ዘወትር ብቸኛው የተግባራችን መመዘኛ ከሁሉም ዓይነት ርእዮተ ዓለም አለማንኛውም ዓይነት ትስስሮሽ ለሁሉም አለ ምንም የቋንቋ የባህል የዘር የሃይማኖት ልዩነት መስጠት የሚል በነጻ ማፍቀር እንድናደርግ ትደግፈናለች ያሉት ቅዱስ አባታችን “ቋንቋቸውም የማልናገር ልሆን እችል ይሆናል ፈገታዮን ልሰጣቸው ግን እችላለሁ” በማለት ቅድስት ተረዛ ያሉትን ሃሳብ አስታውሰው፥ እንዲህ ባለ ሁነት ብቻ ነው አመኔታው ላጣው ግንዛቤ ተስተውሎና የዋህነት እጅግ ለተጠማው ሰብአዊ አዲስ የሐሴት ምዕራፍ ለመክፈ የሚቻለው ያሉት ቅዱስ አባታችን፥ ለዚህች የምኅረት ቅድስት ለሆነቸው እናቴ ተረዛ በተወከፈው ዕለተ ሰንበት የምንናዘዘው ተአምኖተ ሃይማኖት ገቢራዊ እንናድርግ አደራ የሚል ጥሪ አቅርበው፡ ፍቅር ሌላ አማራጭ የለውም ወንድሞችን የሚያገለግሉ ሁሉ ባወቁትና ባፈቀሩት እግዚአብሔርን የሚያፈቅሩ ናቸው ብለዋል።

የክርስትና ሕይወት ሲያስፈልግ መልካም ነገር ማቅረብ ወይንም ማድረግ ማለት አይደለም። እንዲህ ቢሆን ኖሮማ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት በቅጽበት የሚሰጥ ሰብአዊ ትብብር ሆኖ በቀረ። እንዲህ ሲሆን ደግም መሰረት የሌለው በመሆኑም መኻን ሆኖ ይቀራል። ጌታ የሚጠይቀው ታታሪነት ያንን ዕለት በዕለት በፍቅር እንድናድግ የሚያደርገን ለፍቅር ጥሪ እንጂ ስለ ለገዛ እራስ ሕይወት አገልግሎት የሚል ገዛ እራስ የሚያስቀድም ፍቅር አይደለም። የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነትም የእግዚአብሔርን ጥሪ መለየትና የእግዚአብሔር ፈቃድ በእራስ ሕይወት ማስተናገድ ነው፡ ይኸንን ጥሪ አለ ምንም ማቅማማት ለማስተናገድም የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን መሆኑ ለመለየት ፈቃድህ በሕይወቴ ምን ይሆን ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።

እግዚአብሒር ደስ የሚሰኝበት እያዳንዱ የምሕረት ሥሪት ወይንም ግብረ ምሕረት በእያንዱ ድጋፋችን በምናቀርብለት ወንድም ዘንድ  ያንን ማንም ያላየው የእግዚአብሔር ተክለ ገጽ የምናይበት በመሆኑ ነው (ዮሐ. 1,18) ወንድሞቻችን የሚያስፈልጋቸው ነገር ለይቶ አውቆ ለማቅረብና ለመደገፍ ጎንበስ ስንል ለኢየሱስ የሚጠጣ ውኃና መብል እንሰጣለን ኢየሱስን እንጎበኛለን እንጠይቃለን (ማቴ. 25,40) ስለዚህ ባጭሩ የክርስቶስን አካል እንነካለን።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ በምኅህረት ዓመት በሚኖረ የበጎ ፈቃድ አባላት ቀን ለመሳተፍና  በዚያ በቅዳሴው ስነ ሥርዓት የተገኙትን የበጎ ፈቃድ አባላትና ማኅበራትን የተገኙትን ሁሉ በማሰብም የእግዚአብሔር ፍቅር ተጨባጭ የሚያደርጉ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለውም የአንተ ፍቅር ለእኔ የዓቢይ ሐሴትና መጽናናት ምክንያት የሚሆነኝ የአማኞች ልብ በሥሪቶቼ ተጽናንተዋልና የሚለውን ቃል ይኖራሉ፡ የበጎ ፈቃድ አባላት የስንቱን ልብ ያጽናናሉ። የስንቱን እጆች ይደግፋሉ። የስንቱን እንባ ያብሳሉ። እዩልኝ በማይለው ትሁት ጥቅማ ጥቅም ባልተካነ አገልግሎት ፍቅርን መሰከሩ። ይኽ የሚደነቅና የሚመሰገን አገልግሎት ለእምነት ልሳን ይሰጣል። ያ ለሁሉም ቅርብ ለተቸገሩት ቅርብ የሆነው የአብ ምኅረት የሚገልጥ ተግባር ነው።

የተናቁት የተገፉት የመጨረሻ ተብለው ለሚታሰቡት ስለ ኢየሱስ ፍቅር ብሎ የሚያገልግላቸው እውነተኛ ፍቅር ስላገኘ ተመስጋኝነትና ግብረ መልስን አይጠብቅም።

ጌታ ሊገናኘኝ እንደመጣና በሚያፈልገኝም ወቅት ወደ እኔ ጎንበስ እንደሚለው ሁሉ እኔም እርሱ ጋር ለመገናኘት እምነታቸውን ባጡት እግዚአብሔር ኢህልው እድርገው በማሰብ በሚኖሩት የሕይወት እሴት በጠፋባቸው በችግርና በቀውስ በሚገኙት ቤተሰቦች፡ በታመሙት በተናቁት በተገፉት በስደኞች ገዛ እራሳቸው በሥጋም ሆነ በመንፈስ ለመከላከል በማይችሉት በታናናሾች ለገዛ ራሳቸው በተተዉት በአዛውንት በአረጋውያን የኅብረተሰብ ክፍለ  አባላት ፊት ጎንበስ እላለሁ።

በማንኛውም ዳግም ተነስቶ ለመራመድ በመሻት እጆቹን ከፍ አድርጎ በሚያነሳው እርዳታን የሚማጸን እጅ ባለበት ስፍራ ሁሉ ያንን እግዚአብሔር እኔ በመሬት ተዘርሬ እያለሁ ደርሶ የረዳኝ ፍቅሩ ተዘክሮ የሚያደርግ ድጋፍና ፍቅር የሚሰጥ  የእኛና የቤተ ክርስቲያን ኅላዌ እውን መሆን አለበት በማለት ያስደመጡ ስብከት አጠቃለዋ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ ልክ መሥዋዕተ ቅዳሴው እንዳበቃም ቅዱስ አባታችን በለገሱት የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ከተለያዩ የዓለምችን ክልሎች የተወጣጡ የፍቅር ደናግልና ካህናት ማሕበር ልኡካን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማኅበራት አባላት ሁሉ አመስግነው እንዳበቁም፥ ቅድስት ተረዛ የሁሉም ቅድስት ነች። ይኽ ደግሞ እውነት መሆኑ ይኸው ለቅድስናው አዋጅ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ የተለያዩ ኃይማኖቶች ባህሎች አባላት መገኘቱ ህያው ምስክርነት ነው። ቅድስት ተረዛ በምድራዊ ሕይወቷ እያለች፥ ደሜ አልባኒያዊ በዜግነት ሕንዳዊት ነኝ፡ በእምነቴ ደግሞ ካቶሊካዊት በጥሪዮ ደግሞ በዓለም ነኝ ልቤ ሙሉ በሙሉ የኢየሱስ ነው ይሉ እንደነበርም በማስታወስ፥ በቅዳሴው ስነ ሥርዓት የተገኙትን የአልባኒያ የመቄዶኒያ የኮሶቮ ርእሰ ብሔሮች የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ሱሽማ ስዋራጅ አንዲት የሂንዱ ሃይማኖት ተጠሪ የበክታሺ መሪ የአልባኒያ ሙስሊም ወንድሞች ማኅበር ልኡክ በካልኩታ የፖሮተስታንት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የስፐይን ንግስት ሶፊያ የተሳተፉ ሲሆን፥ ሁሉንም አመስግነው በቀጥታ በዚህ እየተኖረ ባለው የምሕረት ዓመት ምክንያት በዚያኑ ዕለት የተዘከረው የበጎ ፈቃድ አባላት ቀን ምክንያት የተገኙትን ሁሉ በማሰብ፥ ሁሉንም ዕለት በዕለት በጎስቋላ ሕይወት በድኽነትና በስቃይ በሚገኙት ወንድሞች ዘንድ ያለው ስቁል ኢየሱስ እንዲያውቁና እንዲያገለግሉ እንዲያስተነትኑ ለቅድስት ተረዛ ጥበቃ አወክፈው አያይዘውም በግብረ ሠናይ ተልእኮ እጅግ በድኽነት የሚኖሩት ሕይወታቸው ለአደጋ የተጋለጠባቸውን ወንድሞችን የሚያገለግሉት ለሕይወታቸው የማይሳሱትን በተለይ ደግሞ ሕይወታቸውን የሚሰዉ ደናግሎችን አስታውሰው እ.ኤ.አ. መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በዚያች እጅግ በስቃይና መከራ በተፈተነው አገረ ሃይቲ ርእሰ ከተማ የተገደሉት የስፐይን ተወላጅ ወንጌላዊት ልእክት ድንግል እናቴ ኢዛቤላን ዘክረው፡ ስለ እሳቸው እንጸልይ ብለው በዚያች አገር ያለው አለ መረጋጋት እልባት አግኝቶ በአገሪቷ አቢይ ጸጥታና ደህንነት እንዲገኝ እንጸልይ በማለት ስለ ሁሉም በተለያዩ አገሮች ባለፉት ቅርብ አመታት የሕይወት መሥዋዕት የከፈሉትን እናስብ ብለው ጸሎተ መልአከ እግዚኣብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት አሰናብቷል።








All the contents on this site are copyrighted ©.