2016-08-16 12:13:00

“ፀሐይን የለበሰች፣ ጨረቃን ከእግሮቿ በታች ያደርገች፣ በእራሱዋም ላይ 12 ከዋክብት ያሉት አክሊል የደፋች አንዲት ሴት ታየች”


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ አውሮፓዊያን ስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር በኔሐሴ 9-2008 የተከበረውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ወደ ሰማይ በነፍስና በሥጋ ያርገችበትን ዕለት የሚዘከርበት የፍልሰታ ዓመታዊ በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ይህንን ታላቅ ዓመታዊ በዓል ለመታደም  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን፣ “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት ንግግራቸውን የጀምሩት ቅዱስነታቸው የማሪያም ዕርገት የሁላችንንም የወደ ፊት እጣ ፋንታ የሚጠቁም ታላቅ ሚስጢር መሆኑን ገልጸዋል።

በእለቱ በተነበበውና ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 1:39-56 በተወሰደው የወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው ስብከተ ወንጌላቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ማሪያም ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት በተራራማ አከባቢ ወደ ሚገኘው የይሁዳ ከተማ በፍጥነት መሄዱዋን” አውስተው ይህም አሁን በእዚህ ዘመን ለምነገኘው ለእኛ የሚያሳየው የእግዚአብሔር አብን እና የልጇን የኢየሱስን ፊት ለማየት ወደ ሰማያዊቱዋ እየሩሳሌም የምናደርገውን ጉዞ ያሳያል ብለው ማሪያም በሕይወት ዘመኑዋ  ኢየሱስ እስከ ተሰቀለበት ተራራ ድረስ ብዙ የተራራ ላይ ጎዞ ማድረጓን የሚያሳይ እና ይህም የኢየሱስ መከራ ተካፋይ መሆኑዋን እንደ ሚያሳይ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህንንም በማከናወኑዋ በዛሬው ሁለተኛ ምንባብ ላይ በዩሐንስ ራእይ በምዕራፍ 12 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ፀሐይን የለበሰች፣ ጨረቃን ከእግሮቿ በታች ያደርገች፣ በእራሱዋም ላይ 12 ከዋክብት ያሉት አክሊል የደፋች አንዲት ሴት ታየች” የሚለው የሚያሳየው በቅድሚያ በእግዚአብሔር ልጅ ያመነች በመሆኑዋ ነው በቀዳሚነት በነፍስ እና በሥጋ ወደ ሰማይ ለማዕረግ የበቃቸው ብለዋል።

“ኢየሱስን በሕፃንነቱ በማቀፉ የእግዚአብሔርን የዘላለም መንግሥት እንድትተዋወቅ ረድቱዋታል” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ ማሪያም ትሁት እና ተደራሽነት ያላት ልጃገርድ በመሆኑዋ በእግዚአብሔር ለዘላለም ከልጁ አጠገብ እንድትሆን መመረጧን ገልጸዋል።

“የማሪያም ዕርገት የእያንዳንዳችን መጭውን ጊዜ የሚያመልክት መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም የሚያሳየው ልክ ማሪያም እንደ ተገበረችው በሚስጢረ ጥምቀት እራስቸውን ከኢየሱስ ጋር ያቆራኙትን ሰዎች ሁሉ እንደ ሚመለከት ገልጸው ኢየሱስ ሞትን ድል እንደነሳ ሁሉ በእርሱ ያመኑ ሁሉ ድል እንደ ሚነሱ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።  

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው እንደ ገለጹት ከገሊላ ከተማ የተገኘች የእዚህች ትሑት ልጃገረድ መክበር እና “ነብሴ ጌታን ታከብረዋለች” በማለት ያቀረበችው ውዳሴ እግዚአብሔር የተናቁትን እና ብቸኛ የሆኑትን ሰዎች ከፍ በማድረግ ከእርሱ ጋር ይኖሩ ዘንድ ወደ ሰማይ እንደሚወስዳቸው የሚያወሳ በመሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ውዳሴ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ እየተዘመረ መሆኑን ገልጸዋል።

“በተጨማሪም የማሪያም ውዳሴ በአሁኑ ጊዜ የሚታዩትን ብዙ አሳዛኝ ሁኔታዎችን  በተለይም ደግሞ በከፍተኛ የሕይወት ጫና ውስጥ እና በስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሴቶችን ያስታውሰናል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ አክለውም በኋያላን እና በጉልበተኞች አስገዳጅነት ሰባዊ ላልሆን አስገዳጅ ሥራ የተጋለጡ ሴቶች ብዙ እንደ ሆኑ ገልጸው አክለውም አካላቸው እና መንፈሳቸው በግዳጅ በወንዶች እንዲበዘበዝ እየተዳርጉ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።

“በእዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴት እህቶቻችን ሰላማዊ የሆነ፣ ፍትህን እና ፍቅርን የተጎናጸፈ ሕይወት ይጀመሩ ዘንድ በማያዋርዳቸው እጅ እንደ ታቀፉ ይሰማቸው ዘንድ ያችን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው በርኅራኄ  እነርሱን ከፍ ከፍ የሚያደርጋቸው እና በሕይወት መንገድ ላይ እየመራቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያደርሳቸውን ኋይል እንደ ሚሹ ገልጸዋል።

“ማሪያም ሴት እና ወጣት ልጃገረድ በመሆኑዋ በሕይወቱዋ ብዙ መከራን አይታ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህም በስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሴቶች እንድናስብ ያደርገናል” ብለው “ ጌታ በእጆቹ ወደ ሕይወት ጎዳና እንዲመራቸው እና ከባርነት ነፃ ያወጣቸው ዘንድ እንማጸናለን” ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ቅዱስነታቸው ባለፈው አርብ እለት በሮም ከተማ የሚገኘውን እና በግዳጅ በዝሙት ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በአሁኑ ጊዜ ግን ከእዚህ ተግባር ታድገው በመጠልያ ጣቢያ የሚገኙትን በርካታ ሴቶችን መጎብኘታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህም ጉብኝታቸው ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ በእለተ አርብ የሚከናወን እና ይህም እለት ‘ምሕረተ አርብ’ ተብሎ መሰየሙ ታውቁዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.