2016-08-13 11:30:00

በአሜሪካ የሚገኙ ካቶሊካዊ ገዳማዊያት፣


በአሜሪካ የሚገኙ ካቶሊካዊ ገዳማዊያት፣ መጪው ፕሬዚደንታዊ የምርጫ ዘመቻ ከጥላቻና ከፍርሃት ነጻ እንዲሆን ተማጸኑ።

ከጥላቻና ከፍርሃት ነጻ የሆነ የቅስቀሳ ንግግር፣ በሁለቱ ተወዳዳሪ ወገኖች መካከል ሰላማዊ ውይይትን ለማካሄድ ይጠቅማል ብለዋል ። በሀገሪቱ ከሚገኙ ገዳማዊያት መካከል 5.671 የሚሆኑ በኅብረታቸው አማካይነት ለሁለቱም የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪዎች ያለፈው ሰኞ ዕለት ጥያቄአቸውን አቅርበዋል።

በአሜሪካ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከታቀፉት 49 ሺህ ገዳማዊያት መካከል 80 ከመቶ የያዘው የገዳማዊያት ምክር ቤት ደበዳቤ እንደሚለው “ሀገሪቱን ለመምራት የሚፈልግ የማንም ወገን፣ ጨዋነት ከጎደለው ንግግር በመታቀብ፣ የጋራ ጥቅምን በማስቀደም፣ የቆመለትን ዓላማ በትሕትናና በእውነት እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ መስከረም ወር 2007 ዓ. ም. ለአሜሪካ መንግሥት ምክር ቤት የላኩትን ሐዋርያዊ መልዕክት ያስታወሰው ይህ ደብዳቤ፣ የእያንዳንዱ አሜሪካዊ ዜጋ ሰብዓዊ ክብርን ማረጋገጥና ማስከበር፣ የጋራ ጥቅምን ማስቀደም የፖለቲካ አቋም መሆን አለበት ብለዋል።

የጥላቻና የፍርሃት ድምጽ የበላይነትን እንዳይጎናጸፍ ያሉት ገዳማዊያት፣ የአሜሪካ መንግሥት የፖለቲካ ምሕዳር፣ ለገዳማዊያት ዕድላቸውን ያጠበበ ከመሆኑ በላይ፣ ጾታን ያማከለና ወደ ግል ጥቅም ያዘነበለ፣ በራስ ወዳድነትና በጽኑ ወገናዊነት ርዮተ ዓለም የተሞላ በመሆኑ፣ በፍርሃት በተዋጠው አቋማቸው የሃገሪቱን የፖለቲካ ገጽታ እንዳያበላሽ፣ በቃላት ሽኩቻ የተሞላው የምርጫ ውድድሩ በጥላቻና በፍርሃት ድምጽ የበላይነትን እንዲያገኝ አንፈቅድም ብለዋል ገዳማቱ በደብዳቤአቸው ማጠቃለያ።








All the contents on this site are copyrighted ©.