2016-08-08 16:52:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት በሪዮ 2016 ኦሎምፒክ ለተሳታፊው የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቡድን


በሪዮ ደ ጃነይሮ በተጀመረው ዓለም አቀፍ  እ.ኤ.አ. የ2016 ዓ.ም. የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር በተባበሩት የዓለም አቀፍ መግሥታት አነሳሽነት ለመጀመሪያ ጊዜ የስደተኞና ተፈናቃዮች ወካይ ከሁሉም አገሮች ጎን በመሆን ለመሳተፍ ለበቃው ቡድን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው ለስደተኞችና ተፈናቃዮች ቡድን ባስተላለፉት መልእክት፥ “መቼም ቢሆን የወንድማማችነትና የስፖርተኛነት ብቃት መስካሪያን ሁኑ፡ ውድ ወንድሞቼ በማለትም የእያንዳንዱ የስደተኞና የተፈናቃዮች ቡድን ስፖርተኛ ስም ራሚ አኒስ፡ ያች ፑር ባይል፡ ጀምስ ንያንግ ኪየንግጀክ፡ ዮናስ ኪዳነ፡ አጀሊና ናዳ ሎሃሊት፡ ሮሰ ናቲከሎኮንየን፡ ፓውሎ ኣሞቱም ሎኮሮ፡ ዩስራ ማርዲኒ፡ ፖፖለ ሚሰንጋና ዮላንደ ቡካሳ ካቢካ አንድ በአንድ በመጥቀስ በዚህ በዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር አመርቂ ውጤት ይቀዳጁም ዘንድ ተመኝተው፡ በውስጣችሁ ይዛችሁት የምትጓዙት ድፍረት ብርታትና ኃይል በዚህ የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር ትገልጡትና ወድማማችነት ሰላም የሚል ይኸንን እሴት የሚጮህ መሆን አለበት። በእናንተ አማካኝነት ዓለም ወድማምችነት ሰብአዊነትና ሰላም ያለው ክብር እንዲያስተውልና በሰላም ሁሉም ይገኛል በጦርነት ግን ሁሉም ይወድማል፡  እናንተ የምትሰጡ ምስክርነት ለእኛም የሚበጅ ነው። ስለ እኔ አደራ ጸልዩ፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፥ በወንድማዊ መንፈስ ፍራንቸስኮ በሚል ቃል ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የገለጡት ቸቶፋንቲ እክለው፥

የስደተኛው ቡድን በሚያጠልቁት የስፖርት መለያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት እርማ ያተኖረበት መሆኑ ገልጠው፥ የዚህ የበላይ ድርገት ይፋዊ ድረ ገጽ እንደሚያመለክተውም የድርገቱ የበላይ ተጠሪ ፊሊፖ ግራንዲ፥ አነዚህ የስደተኞች ቡድን ለሁሉም ስደተኞችና ተፈናቃዮች ብርታትና የሰብአዊነት ምስክርነት ነው። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ፈጽሞ ያልታየ በዚህ ዘመን እየተከሰተ ያለው የስደትኞች ጸአት መስተዋል እንዲያገኝና መንግሥታም ይኽ እጅግ መለኪያ የሌለው ሰብአዊ ችግር እልባታ እንዲያገኝ ጥረት እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ነው፡ በዚህ አጋጣሚም እያንዳንዱ ስደተኛና ተፈናቃይ ሁሉ አስፈላጊ ሰብአዊ እንክብካቤ አግኝቶ በተሰደደበት አገር ሰብአዊ መብቱ ተከብሮለት እንዲኖር ጥሪ የሚያቀርብ ፊማር በማሰባሰብ ተግባር የሚከወን መርሓ ግብር በእቅድ መያዙንም ገልጠው ፊርማ የተኖረበት ሰነድም እ.ኤ.አ. መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በኒው ዮርክ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ይረከባል እንዳሉ የድርጅቱ ድረ ገጽ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳ መቻሉንም ቸንቶፋንቲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.