2016-08-05 15:54:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ብሔራዊ ሐዋርያዊ ዑደት በአሲዚ


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአሲዚ ምሕረት በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በዚህ በምሕረት ዓመት ልዩ የምሕረት ትእምርት በማለት የገለጡት እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 4 ቀን የሚፈጸመው የሙሉ ሥርየተ ሐጢአት መንፈሳዊ ንግደት ጅማሬ ዝክረ ስምንት መቶኛው ዓመት ምክንያት  በአሲዚ በቅድስተ ማርያም ዘመላእክት ባዚሊካ መንፍሳዊ ንግደት ፈጽመው እዛው የጽሞና የግል ጸሎት እና አስተንትኖ ፈጽመው እዳበቁም ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 18 ይቅርታ ስለ ማድረግ ርእስ ዙሪያ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና በጴጥሮስ መካከል የተደረገው ውይይት ላይ በማተኰር በጸሎት ሥነ ስርዓት ለተሳተፉት ምእመናን የፍራንቸስካውያን ማኅበር ወንድሞች አስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታውቋል።

የተከበራችሁ ወንድሞቼና እኅቶቼ ከሁሉም አስቀድሜ ቅዱስ ፍራንቸስኮ እዚህ ሥፍራ ከብፁዓን ጳጳሳትና ምእመናን ፊት “ሁላችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ልልካችሁ አቢይ ምኞቴ ነው” ሲል መናገሩ የሚገልጠው ጥንታዊ ባህል ማስታወስ እወዳለሁ። የሁሉም መዳን በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ዘለአለማዊ ሕይወት ፍጻሜ የሌለው ሙሉ ሐሴት ኢየሱስ በሞቱና በትንሳኤው ያረጋገጠልን የመዳን ጸጋ ከመጠየቅ በቀር ከዚህ በላይ የአሲዚው ድኻው ወንድም ሌላ ጥያቄ ለማቅረብ በእውነቱ የሚቻል እንዳልሆነ ነው፡ መንግሥተ ሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለአለም ፍጻሜ የሌሌው እርሱን ማምለክ የሚለው የፍቅር ምስጢር መኖር ማለት ከመሆኑም በስተቀረ ሌላ ምንም ትርጉም ሊሰጠው ይችላልን? ቤተ ክርስቲያ ተአምኖተ እምነት ስትደግም በቅዱሳኖች ሱታፌ አምናለሁ ስትል ይኸንን እውነት ነው የምትመሰክረው። ስለዚህ እምነታችን በመኖር ሂደት ቅዱሳንና ብፁዓን ይሸኙናል … አንድ አካል የሚያደርገንም “በመንፈስ ቅዱስ ተነቃቅተን” (ኤፈ. 4,4,ተመልከት) የተቀበልነው አንድያ ጥምቀት ነው። እ.ኤ.አ. በ1216 ዓ.ም.  ቅዱስ ፍራንቸስኮ ር.ሊ.ጳ. ኦኖሪዮ ሳልሳዊን ይኸንን ዛሬ የምንገኝበት በቅድስት ማሪያም ዘመላእክት ውስጥ ወዳለው ቅዱስ ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ለሚፈጽሙ ሁሉ ምሉእ ሥርየተ ሐጢአት እንዲያገኙ በማለት ሲጠይቅ “በአባቴ ቤት ብዙ መኖርያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደው ሥፍራ ላቸጋጅላችሁ ነው፡ ሄጄም ሥፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ” (ዮሐ. 14, 2-3) ሲል ኢየሱስ የገባውን ቃል በማሰብ ነው።

ይኸንን ቃል የተገባልንን ዘለዓለማዊ ሥፍራ ወደ ተደራሽነቱ የሚመራው መንገድ በእርግጥ ምህረት ነው። ይቅርታን መስጠት ይቅር ማለትን እጅግ ከባድ ነው! ለሌላውን ይቅርን መስጠት ምንኛ ከባድ ነው። … በዚህ ቅዱስ ሥፍራ መገኘት ምኅረትን በመሻት ነው፡ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18, 21-35 የተነበበውን እዳምጠናል። የበደለንን የጐዳንን ሰው ለምን ይቅርታን እናደርግለታልን? መልሱ ቀላል ነው ምክንያቱም ይቅርታ ስለ ተደረገልን ነውና። ወሰን አልቦ ምሕረት፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምሕረት ዙሪያ የሰጡት ቃለ አስተንትኖ በመቀጠል በዚህ ቅዱስ ፍራንቸስኮ መሐሪ እጅ መሓሪ ልብ፡ የሚምር ልብ የሚዳብስ ልብ መሆኑ በማስተዋል። ብዙውን ጊዜ እኛ ሰዎች ታየኛለህ ካተበቀልኩህ፡ የሚሉት ብድር በምድር ካልሆነ ወዮልኝ የሚል የሚከተሉት መንፈስ ከምሕረትና መሓሪነት እጅግ የራቀና ከምህረት ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት የለዉም። የበደለንን ስንምር መማራችን አውቀን ነው፡ ይኽ ደግሞ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ የሚል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ጸሎት ልብ እንድንለው ያሳስበናል። እግዚአብሔር ለእኛ ምሕረቱን በመሰጠት የማይደክም አምላክ ነው፡ ምሕረቱ ምሉእ በመሆኑ ምንም’ኳ ዳግም ብንወድቅ ከመማራችን የማይደክም የማይሰለች ነው። … የእግዚአብሔር ምሕረት ወሰን የለውም። ከምናስበውና ከምንገምተው ልንገልጸው ከሚቻለን ሁሉ በላይ ከፍ ያለ እጅግ የላቀ ነው። የምሕረት ጠያቄው ልብ የሚመለከት አምላክ ነው።

እኛ ምሕረት የሚያስፈልገን ስንሆን ምሕረት ይገባኛል ባዮች እንሆናለን። ምሕረት ጠያቂው ሌላው የሚመለከት ሲሆን ግን ፍርድ ይበየን እንላለን። ይኽ የክርስትና ሕይወት ዘይቤ አይደለም። ኢየሱስ እንደተማርነው ሁሉ መሐሪያን እንድንሆን ነው የሚሻው። ምሕረት ለማግኘት መሐሪያን መሆን። የአባቱን ፍቅር ያቀርብልናል እንጂ ፍርድ ይበየንባቸው አላለም። ስለዚህ ቅዱስ ፍራንቸስኮ በዚህ ቅዱስ ሥፍራ አሁንም ከስምንት ዘመናት በኋላ ዛሬም መንግሥተ ሰማይን ይመሰክርልናል። ቤተ ክርስቲያንና ዓለንም የሚያድሰው ምሕረት ነው። ማናችንም የምሕረት መስካርያን ከሚለው ክርስቲያናዊ ጥሪ ሊያፈገፍግ አይችልም። ዓለም ምሕረትን ይሻል። ብዙ ሰው በልቡ ቂም ታቅፎ ይኖራል ምክንያቱም ለመማር ብቃት የሌለው በመሆኑ፡ የእርካታና የሰላም ሐሴት ከመታደል ይልቅ እንዲህ ባለ መልኩም የእራሱን ሕይወትና የሌላውን ሕይወት ለአደጋ ያጋልጣል ያሉት ቅዱስ አባታችን ትሁታን የምሕረት ምልክቶችና መሣሪያ እንድንሆን የቅዱስ ፍራንቸስኮ አማላጅነት እንጠይቅ ብለው ከዚህ ጋር በማያያዝም በወንጌል ሉቃስ 15, 11-32 ያለው ጠፍቶ ስለ የተገኘው ልጅ ያለውን ታሪክ አስደግፈው፤ እግዚአብሔር ለመማራችን ፈጣን መሆኑ አብራርተዋል። ገና ምሕረትን ለመጠየቅ አፉን የከፈተው ጠፍቶ የተገኘው ልጅ አባቱ አፉን ከድኖ በእቅፉ ያኖረዋል። እግዚአብሔር ወደ ቤቴ ልመለስ የሚለውን ሃሳብ ወደ ቤት በሚወስደውን መንገድ ለመጓዝ የሚነሳው የሚያሳየው ቁርጥ ፈቃድ የሚያይ አባት ነው፡ ሁላችን የጠፉ ልጆች ነን ወደ አባታችን ለመመለስ ቁርጥ ፈቃድ በማደረግ እንነሳ  በማለት  የለገሱት አስተንትኖ አጠቃለው እንዳበቁም ማንም ሳያስበው ወደ የማናዘዣ ሥፍራ በመሄድ እዛው 19 ምእመና አናዘው ሁሉንም የፍራንቸካውያን ወንድሞች የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳትና አንድ ከፐሩጃ የመጡት ኢማም ሰላምታን አቅርበው እውጭ ለተገኙትን ምእመናን ሰላምታን አቅርበው እንማርም ዘንድ መሐሪዎች እንሁን አደራ በማለት መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.