2016-07-27 16:05:00

ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊች፥ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የሰላምና የአሃድነት ትእምርት ይሁን


ክራኮቪያ ክተለያዩ አገሮች በተወጣጡ ወጣቶች ብዛት አሸብርቃ ኅቡር ቅንስልና አሃድነት ትእምርት ሆና ሁሉም እምነት ቋንቋው በማድረግ በልሳነ እምነት የሚገናኝባት ከተማ መሆንዋ ከቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ድዚዊች ሰላምና አሃድነት የሚጎላባት ከተማ እንደምትሆን ጠቅሰው፡ የክራኮቪያ ሁኔታ ለፖላንድ ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም የትልቅ ደስታ ምክንያት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በክራኮቪያ እንገናኝ በማለት ሰጥተዉት የነበረው ቀነ ቀጠሮ መልስ በመስጠት ፖላንድ የገቡት ወጣቶች ክራኮቪያን በኅቡር ቅንስል ታሸበርቅ ዘንድ አድርጓታል። የዛሬ 25 ዓመት በፊት በክዘስቶቾዋ ተካሂዶ በነበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ክሩሲያ ከኡክራይን የተወጣጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ በቅቷል። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በእውነት ዓለም አቀፋዊ የሚያስብለው ተጨባጭ ሁነት የጎላበት ነው፡ በዓለማችን የሚገኙት አገሮች በጠቅላላ ተወክለዋል ለማለት ይቻላል።

ይኽ የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በቅዱስ የምኅረት ዓመት ወቅት የሚከናወን በመሆኑ ያለው መንፈሳዊነት እጅግ የላቀ ነው።  የምኅረት እምነት የምኅረት ጸሎት የምኅረት መዝሙር የሚኖርበት ነው ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊች አክለው፥ በተለያየ ፖለቲካ ምክንያት የተለያዩ አገሮች ክሌአዊ ግኑንነት ጭምር የሌላቸው ሆነው እያሉ በዚህ የወጣቶች ቀን ሲገናኙ በወጣቱ አማካንነት ሲገናኙ ታያለህ ስለዚህ በአገሮቹ መካከል ያለው ልዩነት መኖሩንም ትዘነጋለህ። ከሁሉም አገሮች የተወጣጡ ወጣቶች በእምነት ጥላ ሥር በመገናኘት አብረው ሰላምና አሃድነትን ይመሰክራሉ። ወጣት ትውልድ የአንድነት የሰላም ትእምርት ነው።

እነዚህ ክራኮቪያ የሚገቡ ወጣቶች በሰላም አብሮ መኖር የሚሰጠው ደስታ መስካሪያን በመሆን በዓለማችን ክልል ለሚታየው ውጥረት ግጭት ጥላቻና አለ መግባባት ትክክለኛና እውነተኛው መልስ ምን መሆኑ ይመሰክራሉ።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ኢየሱስ ለቅድስት ፋውስቲና በመገለጥ ዓለም ሰላምን እንዲያወቅ ወደ መለኰታዊ ምሕረት ያቅና ሲል የሰጣት መልእክት ይኸው ዛሬም በዚህ በቅዱስ የምህረት ዓመት ውስጥ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እያስተጋባው ነው። የሰላም መንገድ የሰላም ገጽታ ምህረት ነው።  ይኽ ደግሞ የኢይሱስ ፈቃድ መፈጸመ ነው። ለወጣቱ ትውልድ የምሕረት የሰላም የጋራ አብሮ መኖር ቅናት ፍላጎት ማስተላለፍ ይገባል።

እነዚህ ወጣቶችም በዓለም ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ድምጻቸውን ያሰማሉ። ወጣቱ ድኻ እውነተኛ በመጀመሪያ ዘመናት የነበረቸው ቤተ ክርስቲያን ትኖረው የነበረውን ሕይወት የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ይሻል። በጠቅላላ ኢየሱስ ክርስቶስን የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ይሻል። ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን ጭምር ወጣቱ ይለወጥ ጠሪ ድምጽ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.