2016-07-27 19:11:00

ር.ሊ.ጳ በፖላንድ፣ ከጦርነትና ከረሃብ ለሚሸሸውን መቀበል ያስፈልጋል


ዛሬ በፖላንድ ክራኩፍ  ከተማ  31ኛ  ዓለም አቀፍ  የወጣቶች ቀን ተጀምረዋል  ትላንትና  የጅምሩ ዋዜማ  በደማቅ  አግባብ  መከናወኑ ይትጋወቃል። ርእሰ ሊቃነ  ጳጳሳት ፍራንሲስ  ዘወትር እንደሚያደጉት ሁሉ  ትናትና አምሻቸው ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን ስኬታማ እንዲሆን ሮም ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ ካተድራ ተጉዘው ሥርዓተ ቅዳሴ ፈጽመዋል።

ዛሬ ከቀትር በኃላ  በዚሁ  31ኛ  ዓለም  አቀፍ  የወጣቶች ቀን  ለመሳተፍ   ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ   ተነስተው በሮም ሰዓት አቆጣጠር አራት ሰዓት ላይ ክራኩፍ ከተማ ገብተዋል። ቅስነታቸው  ዮሐንስ  ጳውሎስ ዳግማዊ  ዘ ባሊስ ክራኩፍ  ሀገራት  አቀፍ  አውሮፕላን  ማረፊያ እንደደረሱ  የሃይማኖት እና መንግስት ከፍተኛ  ባለስልጣናት  ደማቅ አቀባበል  አድርግውልቸዋል። የፖላንድ  ርእሰ  ከተማ ዎርሶ  መሆንዋ እና  ክራኩፍ 762 ሺ  ህዝብ  የሚኖርባት  ባአማካይ ትንሽ ከተማ መሆንዋ ይታወቃል። የክራኩፍ  ሀገረ ስብከት  ሊቀ  ጳጳሳት  ብጹዕ ካርዲናል  ስታንላው ዲቪጽ  ሲሆኑ  447 ቁምስናዎች  1.174 ካህናት 15 አብያተ ክርስትያናት እንዳሉ እና በፖላንድ  የቅድስት  መንበር  ሐዋርያዊ  እንደራሴ  ብጹዕ አቡነ  ቸለስቲኖ  ሚልዮረ ናቸው።

ይሁን እና ቅድስነታቸው  ከዮሐንስ  ጳውሎስ  ከሀገራት አቀፍ አውሮፕላን  ማረፍያ  ወደ  ቫቨል  ወደ  ተባለ ቦታ  መግጓዛቸው እና የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ፕረሲዳንት  እንድጀይ ዱዳ  አቀባበል  ያደረጉላቸው ሲሆን እዚያው    ከሀገሪቱ የሲቪል ማሕበረሰብ  ተወካዮች እና  ዲፕሎማቶች  ጋ ተገናኝተዋል። ቅድስነተቸው  የሚከተለውን  ቃል አሰምተዋል።

‘’ክቡር ፕረሲደንት፣ የተከበሩ ባለስልጣኖችና የዲፕሎማሲ ኣካል ኣባሎች፣ ጥቀ ክቡራን ኣለቆች፣ ክቡራትና ክቡራን፣ ለተከበሩት ፕረሲደንት ስላደረጉልኝ ደማቅ ኣቀባበልና ስላቀረቡልኝ መልካም ንግግር በኣክብሮት ኣመሰግናለሁ፣ የመንግስትና የፓርላመንት ኣካሎች የዪኒቨርሲቲ ኣላፊዎች እንዲሁም የተለያዪ ክልሎች ኣላፊዎችንና መላው ሕዝብ እንዲሁም ዲፕሎማቶችንና ሌሎች ባለስልጣናን ሰላምታ ላቀርብ እሻለሁ፣ መካከለኛውን የኤውሮጳ ምስራቃዊ ክብል ስጎበኝ የመጀመርያ ግዜ ሲሆን ይህንን ጉብኝት የዓለም ኣቀፉ ወጣቶች ቀን ጀማሪ የሆኑ ስመ ጥር ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኣገር በሆነችው በፖላንድ ስጀምረው የላቀ ደስታ ይሰማኛል፣ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስለ በሁለት ሳንባዎቿ የምታስተነፍስ ኤውሮጳ መናገር ደስ ይላቸው ነበር፣ ጽኑ መሰረቶቹ በክርስትና ያገኘው ስልጣኔና በእነሲሁ ሁለት ሳንባዎች ማስተንፈስ የሚታደስ ኣዲስ የኤውሮጳ ሰብኣውነት ሕልም ነበራቸው፣

ዝክር የፖላንድ ሕዝብን ከሌሎች ይለያቸዋል፣  የቅዱስ ዮሓንስ ዳግማዊ ህያው ታሪክ ዘወትር እያስደነቀኝ ነው፣ እርሱ ስለሕዝብ ሲናገር ከሰብኣዊና መንፈሳዊ ዕሴቶች ዳግም ለመነሳት ሁሌ ከታሪካቸው ይጀምሩ ነበር፣ በሰብኣዊ ማህበረሰባዊ ፖሎቲካዊ ምጣኔ ሃብታዊና ሃይማኖታዊ ዕሴቶች ላይ የተመሰረተ ሃገራዊ ማሕበር ለማቋቋም ከትዕቢታዊ ውጥንቅጥ ነጻ ነሆነ የማንነት እውቅና የግድ ያስፈልጋል፣ ይህም ማህበረሰቡና ባህሉ መሰረቱን ሳይለቅ ለመታደስና ለመጻኢ ክፍት እንዲሆኑ ይረዳቸዋል፣ በዚህ መንፈስ ከቅርብ ግዜ በፊት የኣገራችሁ ፖላንድ ክርስትና መግባት 1050ኛውን ኢዮቤል ኣክብራችኋል፣ የሃገራዊ ኣንድነት ጥንካሬ ያስገኘ ሆኖ የተለያዩ ወገኖች ማንነታቸው በመጠበቅ በኣንድነት የመላው የፖላንድ ህዝብ የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ ዋነኛ መንገድ መሆኑን ተረድታችኋል፣

በዓለም ኣቀፍ ደረጃም ቢሆን የማንነት ጥናትና እውቅና ኣንዱ የሌላውን ማንነት በማወቅና በማክበር፣ እርስ በእርስ በመተባበር ስለሚያስፈልግ ከገዛ ራስ ማንነት ማወቅ የማይነሳ ድርድር ሊኖር ኣይችልም፣ በእያንዳችን ዕለታዊ ኑሮ እንዲሁም በማህበረሰቦቻችን ሁለት ዓይነት ዝክሮች ኣሉ፣ መልካም እና መጥፎ ኣዎንታዊና ኣሉታዊ፣ መልካም ዝክር ያ እመቤታችን ድንግል ማርያም በቅዱስ መጽሓፍ ተዓብዮ ነፍሴ በሚለው ለእግዚኣብሔርና የመዳን ስራውን በምታመሰግነው መዝሙር ተገልጠዋል፣ ኣሉታዊ ዝክር ደግሞ በልቡና በኣእምሮው መጥፎ ነገሮችን ያሰላስላል፣ በተለይ ሌሎች የፈጸምዋቸውን ጥፋቶች በማስታወስ፣ የቅርብ ታሪካችሁ የተመለከትን እንደሆነ ግን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው ኣዎንታዊውን ዝክር መርጣችኋል። ለምሳሌ በእናንተና ጀርመኖች መካከል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ብኋላ የዕርቅና የምሕረት መንፈስ በመልበስ ይቅርታ የተለዋወጣችሁት 50ኛ ዓመት ማክበራችሁ እጅግ መልካም ነው፣ ይህ በቤተክርስትያን ኣነሳሽነት የተጀመረው መልካም ተግባር ማህበራዊ ፖሎቲካዊ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ነገሮችን ታሪክ ዳግም ሊቀለብሰው በማይቻል መንገድ በመስራት የሁለቱ ሕዝብ ታሪካዊ ግኑኝነት ለወጠ፣ በዚህ ኣጋጣሚ የፖላንድ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንና የሞስኮ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርትያን ያደረጉት ስምምነትና የጋራ መግለጫ ለሁለቱ ኣብያተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን የሁለቱን ኣገሮች ሕዝብ እንደአወሃሃደ ነው፣

በእንዲያ ያለ መንገድ ይህች የተከበረችው የፖላንድ ኣገር መልካሙ ዝክር እንዴት ሊዳብር መጥፎውን እንዴት ጥሎ መተው እንደሚችል ታሰያናለች፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የህዝቦች ዕድል ፈንታን በሚወስን የተዘጉ በሮችን በሚከፍት እንዲሁም ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል በመለወጥ ሁሉም የማይቻል በሚመስልበት ኣከባቢ ኣዳዲስ ዕድሎች በሚፈጥር ኣምላክ ጽኑ ተስፋና ሙሉ እምነት መጣል ያስፈልጋል፣ ይህንንም የፖላንድ ታሪካዊ ፍጻሜዎች ይመሰክሩታል፣ ከብዙ የጥፋት ማዕበሎችና የጨለማ ዓመታት በኋላ ክብሩን በመጠበቅ ልክ ዕብራውያን ከባቢሎን ባርነት ሲመለሱ እንዳደረጉት የድል መዝሙር መዘመር ችለዋል፣ ‘እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን። በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።’ (መዝ 126) የተፈጸመ ጉዞ ዝክርና በተገኙ ድሎች መደሰት በጊዜው ለሚያጋጥሙ ተግዳሮች ለመቁቋም ሃይል ይሰጣል፣ በዚህ የሚጠየቀው እውነትን ለመናገር ብርታት ተገቢውን ግብረገብነት ለመከተል ጽናት በመታጠቅ ወሳኝ የሆኑ ሂደቶችና ግኑኝነቶች የሰው ልጅ ክብርና መብት የሚጠብቁ መሆን ኣለባቸው፣ በዚህ ተግባር ሁሉ ይሳተፋል ምጣኔ ሃብት የኣከባቢ ሁኔታና ኣሁን ኣጋጥሞ ያለ የስደተኞች ጉዳይ በዚሁ መስፈርት ይመዘናሉ፣

በተለይ የስደተድኞች ጉዳይ ከሰብኣዊ እርዳታ ባሻገር ፍርሃትን ለማሸነፍና ታላቊን መልካም ነገር ለማድረግ ጥበብናየምህረት መሟላት ኣለበት፣  ከሁሉ ኣስቀድሞ ከፖላንድ ለመሰደድ የሚያስገድዱ ምክንያቶችን ማወቅና ኣገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉትን መርዳት ያስፈልጋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ባልተለየ መንገድ ከጦርነትና ከረሃብ በመሸሽ ጥገኝነት ለሚጠይቁም መቀበል ኣጋርነት ማሳየት፣ እነኚህ ሰዎች መሰረታዊ መብቶቻቸውና ክብሮቻቸው እንደተጣሱ በመረዳት በተለይ ደግሞ እምነታቸውን በነጻነትና  ደህነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ለመኖር ያልቻሉትን መርዳት ያስፈልጋል፣ ዓለም ኣቀፍ ማሕበረሰብ ደግሞ የችግሮቹ መንግስኤ በማጥናት መፍትሔ ማፈላለግና ፍትህ እንዲነግስ ማድረግ፣  ፍትህና ሰላም እንዲነግስ በመጣር ቤተሰብና ሕይወትን መጠበቅ ያስፈልጋል፣’ ሲሉ ኣደራ ካሉ በኋላ ስለ ቤተሰብና ሕይወት ዋነኛነት ልንከላከላቸው እንዳለብን በማሳሰብ ንግግራቸውን ደምድመዋል።’’

ከግንኝነቱ በኃላ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንሲስ  እዚያው  ህንጻ ውስጥ ለፖላንድ  መንግስት መሪ  ለፕረሲዳንት አንድጀይ ዱዳ የክብር ጉብኝት  በማድረግ   ከፕረሲሳንቱ ጋር  በግል ሐሳብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል። ከዚሁ የክብር ጉብኝት በኃላ   ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት  በመኪና  ውደ  ክራኩፍ ካተድራል ተጉዘዋል።  የፖላንድ ብጹዕን ጳጳሳት ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።  ቅድነታቸው ከብጹዓን የፖላንድ  ጳጳሳት ተገናኝተዋል። ከብጹዓን ጳጳሳቱ ተሰናብተው  ወደ  ቤተ ሊቀ መንበረ  ጵጵስና  ተጉዘዋል  በዚህም  የዛሬ  ውሎ ፍጻሜ  ሁነዋል ዛሬ  የተጀመረውን  31ኛ  ዓለም አቀፍ  የወጣቶች ቀን  እስከ ፊታችን  ስንበት  ሐምለ ወ 31 ቀን  ይቀጥላል። ከዓለም  ዙርያ ከአንድ  ሚልዮን በላይ ወጣቶች  በዚሁ በፖላንድ  ክራኩፍ ላይ  እየተካሄደ ያለውን ዓለም አቀፍ  የወጣቶች ቀን ተሳታፊመሆናቸው  ከቦታው የደረስ ዜና  አመልክተዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በፖላንድ  ለአምስት ቀናት የሚዘልቀው  ህእዋርያዊ ጉብኝት 15ኛ ሐዋርያዊ  ጉብኝት መሆኑ የሚታወስ ነው። 








All the contents on this site are copyrighted ©.