2016-07-25 16:26:00

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን: ዓቢይ የእምነት በዓል


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በክራኮቪያ የሚካሄደው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እዛው ከሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ክራኮቪያ እንደሚገቡና እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. እሁድ የወጣቶች ቀን መዝጊያ መስዋዕተ ቅዳሴ ካሳረጉ በኋላ ወደ ማምሻው አገረ ቫቲካን እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

ፖላንድ ይኸንን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሚገባ ለማስተናገድ አስተናጋጅ ተብላ ከተመረጠችበት ቀን ጀምሮ በአገሪቱ የተከናወነው ቅድም ዝግጅት የተዋጣለት መሆኑ ቀርበው ለመገንዘብ መቻላቸው ገልጠው። የጸጥታውና የደህንነቱ ጉዳይ በተመለከተ ምንም ዓይነት ስጋት የለም ብለው፥ በርግጥ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል በተለይ ደግሞ በቁጥር እጅግ ከፍ ያለ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጠ ወጣት እንዲህ ባለ መልኩ በአንድ ላይ ሲሰባሰብ ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም ለተዋጣለት ሂደቱን ለኣላማው መሳካት የሁሉም እስተዋጽኦን ትብብር እንዲሁም ኃላፊንትን ይጠይቃል ብለዋል።

ክራኮቪያ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመመረጣቸውና ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ከማስጀመራቸው በፊት በሊቀ ጳጳስነት ሐዋርያዊ ሥልጣን ሥር ይተዳደር የነበረ ሰበካ መሆኑ ያስታወሱት አባ ሎምባርዲ አክለው በዚያች ከተማ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማክበሩ ጥልቅ ትርጉም ይኖረዋል። መለኮታዊ ምኅረት የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናቸው መለያ ነው። መለኮታዊ ምኅረት ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክትና ለእናቴ ፋውስቲና ቅድስና በማወጅ እንዲሁም ዓመታዊ በዓለ ምኅረት ቅዋሜ በይፋ ያወጁ ያንን ሁለተኛ ሺሕኛው ቅዱስ ዓመት ባሸጋገሩት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ትውልድ በሆነቸው አገር የሚከናወንና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ቅዱስ ዓመት እየተኖረበት ባለው ወቅት ማክበሩ ልዩ ትርጉም ያለው የወጣቱ ቀን በመለኮታዊ ምኅረት የተመራ መለኮታዊ ምኅረት እንዲኖር የሚያነቃቃ ኃይል የሚጎናጸፍበት ይኸንን በቃልና በሕይወት ለመመስከር ለሚያደርገው ጥረት አቢይ ጸጋ የሚያጎናጽፈ እንደሚሆን አያጠራጥርም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.