2016-07-25 19:16:00

ር.ሊ.ጳ የዓመጽ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች እግዚአብሔር በመንግስተሰማያቱ እንዲቀበላቸው ጸሎት ኣሳርገዋል


ቅዱስ አባታችን  ርእሰ  ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እሁድ በቅዱስ ጳጥሮስ አደባባይ ከሚገኙ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች ጋር በጋርዮሽ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት እንደሚደግሙ የሚታውስ ነው። ትላንትና እሁድ እንዲሁ እንደተለመደ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን ጋር እሁዳዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግምዋል። 

ቅድስነታቸው ትላንትና በአደባባዩ መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ በጀርመን  ሙዩኒክ ከተማ ላይ እንዲሁመ  በአፍቃኒስታን በርእሰ ከተማ ካቡል በተፈጸሙ ጥቃቶች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጠዋል።  በሁለቱ ሀገራ የዓመጽ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች እግዚአብሔር በመንግስተሰማያቱ እንዲቀበላቸው ከምእመናን ጋር በጋራ የጸለዩ ሲሆን ለቤተ ሰቦቻቸው ጽናቱን ተመኝተዋል።

በጀርመን ሙዩኒክ ከተማ ላይ እንድ ግለ ሰው በፈጸሙት ጥቃት ራሳቸውን ጨምሮ 10 ሰዎች ሲገደሉ በአፍቃኒስታን መናገሻ መዲና ካቡል አጥፍተው ጠፊዎች በሰነዘሩት ጥቃት  80 ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸው  ተገልጠዋል።

ቅድስነታቸው በየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ  በብጹዕ ፒየትሮ ፓሮሊን  በኩል በጀርመን የሙኒክ ሊቀ ጳጳሳት ለብጹዕ ካርዲናል ራይንሀርድ ማርክስ የሐዘን ተለግራም  መላካቸው ተመልክተዋል።

ቅዱስ  አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትላንትና በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምእመናን እንደነገሩት እምነታችንን ለመጓልልመስ ዘወትር መጸለይ ይጠበቅብናል ጸሎት የእግዚአብሔር መንገድ መሳርያ ነው ብለዋል። ጸሎት ማድረግ ለእግዚአብሔር ቦታ መስጠት መሆኑ እና  እኩይ ነገር  በጸሎት ማገት እንደሚቻል  ጠቁመው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድራዊ ሕይወቱ በጸሎት ተጠምዶ መኖሩ  አስታውሰዋል። 

ኢየሱ ስክርቶስ ለሐዋርያቱ አባታችን በሰማይ የምትኖር ጸሎት ማስተማሩ አስታውሰው ከዚሁ ጸሎት ሶውስት ዓበይት መሰረታውያን ነገሮች ይገኛሉ ብለው ይኸውም ዳቦ ምህረት እና እገዛ በማለት ቅድስነታቸው በማያያዝ አስገንዝበዋል።

አለ ዳቦ ምህረት እና የእግዚአብሔር እገዛ  ከቶ መኖር  አይቻልም ያሉት ቅድስነታቸው ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ምህረት መልሰን ለሌላ መስጠት ይጠበቅብናል።

ሐጢአተኞች በእግዚአብሔር  የተማርን  ፍጥረቶች  መሆናችን   ልንረሳ  አይገባም  ሐጢአተኛ  ስለ ሆነ  በእግዚአብሔር  የተማረ መሆኑ የማይቀበል ሰው ምህረት ሊሰጥ አይችልም ይቸገራል ሲሉም አብራርተዋል ቅድስነታቸው።

እንግዲህ  ውድ  ምእመናን  እግዚአብሔር ከፈተናዎች  ሁሉ  እንዲጠብቀን መጸለይ አለብን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተን በቅዱስ ወንጌል መሰረት ሰላማዊ ሕይወት መምራት ይኖርብናል ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ  በዚሁ ረገድ እንድትረዳን እንለምናት እንማጸናት በማለትም  ቅዱስ አባታችን  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አሳስበዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፊታችን ረቡዕ  ሳላሳ አንደኛ  ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን   በፖላንድ  ክራኾቭያ ከተማ ላይ  እንደሚጀመር አስታውሰው እሳቸውም  በዚሁ  ዓለም አቀፍ  የወጣቶች ቀን  ተሳታፊ ለመሆን  ሮቡዕ ከመንበረ  ቅዱስ ጰጥሮስ እንደሚነሱ እና ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን የምህረት  ኢዮቤልዩ  እንደሆነም ቅድስነታቸው አስታውቀዋል።

ቅድስነታቸው ፊታችን  ሮቡዕ  በፖላንድ ክራኾቪያ መዲና ላይ የሚጀመረው ሳላሳ አንደኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ስኬታማ እንዲሆን ምእመናን እንዲጸልዩ ጠይቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.