2016-07-22 16:31:00

ወደ 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


በአገረ ፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ የሚካሄደው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በይፋ ሊጀመር ጥቂት ቀናት የቀረው ሲሆን ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት የድምጸ ርእየት መልክእት አማካኝነት እየተኖረ ባለው በቅዱስ የምኅረ ዓመት ጥላ ሥር የሚከናወን የምኅረት ምልክት የተኖረበና የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አስጀማሪው የፖላንድ ተወላጅ የፖላንድ ሕዝብ ታሪካዊ ወደ ሆነው ነጻነት የመሩ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሚዘክር መሆኑ ያስታወሱ ሲሆን፡ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ከቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተክለ ሰብነት ጋር ያለው ጣምራነት ማስታወሳቸው የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለቅድስና አዋጅ የሚያበቃ የቅድስናቸው መሥረተ ነገር አቅራቢ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ስላውሚር ኦደር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውሰው፥ በዚህ ዓለማችን በጥላቻ መንፈስ እጅግ እየተሰቃየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን የመሠረቱት የእግዚአብሔር መኃሪነት ያስተጋቡ ይኸንን መንፈሳዊነት ያስፋፉትን ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማስታወሱ ተገቢ ነው። በዚያ እግዚአብሔር በአንድ ልጁ አማካኝነት በቃልና በተግባር ባረጋገጠው ፍቅር ዙሪያ ወጣቱን በማሰባሰብ የምንኖርበት ዓለም የበለጠና ሰብአዊ ልክንት ያለው እንዲሆን ማድረግ ያለው አንገብጋቢነት ዓቢይ ግምት በመስጠት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ያነቃቁትን ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መእክት ሲያስታውሱ አለ ምክንያት አልነበረም። በሁለተኛም ደረጃም ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የእግዚአብሔር ምኅረት ማእከል ያደረገ የኖሩት ያስተጋቡት ያስተማሩት መንፈሳዊነትን ጠቅሷል። ይኽ ደግም አገረ ፖላንድ የእነዚያ ሁለቱ የምኅረት ሓዋርያ የሆኑትን የቅድስት ፋውስቲናና ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳማግማዊ ሥርወ መንፈሳዊነት የሚገኝባት አገር ነች ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለብዙ ወጣቶች ብሶል በመሆን ጥሪያቸውን ለመለየት ያስቻላቸው ቅዱስ መርሓ ግብር ነው።  ብዙ ካህናት ጳጳሳት ብዙ ባለ ትዳሮችን ያፈራ እያፈራ ያለው ተመክሮ ነው። ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለልጆቻቸው ብቃት ግድ የሚሉ የታረመ ጠባይ የሚሹ ፍቅር በመግለጥም የሚበጀው መንገድ ያመላከቱ ናቸው። ስለዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የቅዱስ ዮሓንስ ጳውልስ ዳግማዊ የመንፈሳዊነት ዱካ ያለበት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ብለው፡ ይኽ ደግሞ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፍቅርና ኃላፊነት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት መጽሓፋቸው ዘንድ የምናገኘው መፈሳዊነት ነው። ለሁሉም ሰው እንደየ ጥሪው ሊከተለው የሚገባው መንፈሳዊነት ያመላከቱበት ምዕዳን የለገሱበት ዓቢይ መጽሓፍ መሆኑም አስታውሰዋል።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና እንዲሁም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለወጣት ልብ የመናገር ብቃት ያላቸው ዓለም  የሚሻው ወጣቱን ተገዥ ሊያደርገው ነው ኢየሱስ ግን ነጻነት የሚያሰጥ ብቻ ሳይሆን እውነተና ነጻነትም ነው። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ወጣቱ ከኃሰት ነቢያት ከአታላይ ጽንሰ ሓሳብ ለመከላከል የሚያስችለው ጸረ ጎጂነት እንዲያጎለብት የሚያበቃው ትምህርት የሚቀስምበት የተባረከ ሁነት ነው ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቤተ ክርስቲያናዊነት የሚኖርበት የወጣቱ ህርመት ልብ የሚደመጥበት የወጣቱ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዴትና ምን መሆን እንዳለበት አመልካች ኃሳብ የሚፈልቅበት መድረክ ነው ካሉ በኋላ ስለ ወጣቱ የሚሰጠው የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝንት የሚገለጥበት ቅዱስ መርሓ ግብር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.