2016-07-18 16:37:00

ደቡብ ሱዳን፥ ልኡካነ ወንጌል ለሰላም


ምንም’ኳ የቶክስ አቁም ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ቅሉ በሱዳን የተሟላ ሰላም አለ መኖሩ ሲነገር እንደ የተባበሩት መንግሥታት መግለጫም ተከስቶ ባለው ውጥረት ሳቢያ አንድ ሚሊዮን የሚገመቱ የአገሪቱ ዜጎች ተፈናቅለውና አለ የመጠጥ ውሃና መጠለያ መቅረታቸው በአገሪቱ የሚገኙት 8 ሺሕ ተፈናቃዮችን መጠለያ የሚስጠው የሳሊዛውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር ከሰጡት  መግልጫ ለመረዳት ሲቻል። በአገሪቱ ያለው ሁኔታ አመጽና ውጥረት የተሞላ መሆኑ በደቡብ ሱዳን ያለው የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ለደቡብ ሱዳን ሰላም የጸሎት ቀን በማወጅ የፖለቲካ አካላት በውይይት የአገሪቱን ችግር እንዲፈቱ ጥሪ ማስተላለፉንም በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት እ.ኤ.አ. ከ 2007 ዓ.ም. እስከ 2011 ዓ.ም. በደቡብ ሱዳን ያገለገሉት የሳሊዢያን ማኅበር አባል ወንድም አሚልካሬ ቦኩቻ በማሳወቅ፥ 

የቶክስ አቁም ስምምነቱ አሁንም የተጠበቀ ቢምሰልም ቅሉ የሕይወት ዋስትናና ደህንነት እጅግ አስጊ ነው እንዲህ በመሆኑም ቤቱንና ንብረቱን ጥሎ የተፈናቀለው ሕዝብ ወደ ነበረበት ክልል ለመመለስ ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል።

ለአገሪቱ ሕዝብ የዓለም አቀፍ እርዳታ እጅግ ያስፈልገዋል ቢሆንም የእርድታው አቅርቦት ወደ ክልሉ ለማድረስ እጅግ አዳጋች ነው በአገሪቱ በሚገኙት የአየር ማረፊያዎች በጣም ተናንሽና ለጥቃት ኢላማ በመሆናቸውም ተረጋግቶ እርዳታ ለማቅረብ እንቅፋት ሆኗል። ወደ ክልልይ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ አገናኝ መንገዶችም ሳይቀሩ ጸጥታና ደህንነት የተጓደለባቸው ናቸው። በአገሪቱ የሚገኙት ልኡካነ ወንጌል ሕዝቡን ለብቻው ላለ መተው የወሰኑና በተለያየ ዘርፍ ሕዝብን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።  በተለያየ ምክንያት የሚቀጣጠለው ግጭትና ውጥረት መፍትሔው የሚያሰጠው የውይይት መድረክ እንጂ የጦር መሣሪያ አይደለም። ይኽ እውነት ሆኖ እያለ ነገር ግን በተደጋጋሚ  እንደ መፍትሔ የሚመረጠው ኃይል የመጠቀም መንገድ ነው፡ በአገሪቱ ሰላም እንዲረጋገጥ የአገሪቱ የፖለቲካ አካላት መልካም ፍላጎት ሊኖራቸው አስፈላጊ ነው ሆኖም የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ውይይት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑ በተለያየ መንገድ ማሳወቅና የግጭቱ ተወናያን አካላት በሰላም  የጠረጴዛ ውይይት እንዲገናኙ ግፊት ሊያደርግ ይገባዋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.