2016-07-18 16:24:00

የእስያ ወጣቶች በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊነት


ከተለያዩ የእስያ አገሮች የተወጣጡ ወጣቶች በዚህ በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንድሚሳተፉ ኤግለዘ ዳ ኤሺያ የተሰኘው የዜና አገልግሎት ገልጦ ከደቡባዊት ኮሪያ በጠቅላላ ከ18 ሰበካዎች የተወጣጡ 800 ወጣቶች ከፊሊፒንስ 1,500 ከኢንዶነዚያ 170 ከህንድ  150  ከጃፓን 120 ወጣቶች እንደሚሳተፉ ያመለክታል።

በድኽነት ምክንያት ወደ ክራኮቪያ ለመጓዝ የሚያስፈልገው ወጪ ለመሸፈን የማይችሉ የድኾች አገሮ ወጣቶች እንዲሳተፉ በማድረጉ የትብብርን የድጋፍ መርሃ ግብር ረገድም የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት የተባበሩ መሆናቸው የገለጠው ኤግለዘ ዳ ኢሺያ አያይዞ ከካምፖጃ 30 ወጣቶች ከታይዋን 140 ከሆንግ ኮንግ 60 ወጣቶች በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ንዲችሉ ትብብር ተድርጎላቸዋ። ሁሉንም ለማሳተፍ የማይቻል ነው ሆኖም ከሁሉም አገሮች የተወጣጡ ወጣቶች ለማሳተፍ የተደረገው ጥረት አቢይ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ያመለክታል።

ከሆንግ ኰንግ የተወጣጡ ተሳታፍያን ወጣቶች በፖላንድ የሚገኙት ታርካዊ ሥፍራዎች እንዲሁም የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ባሰቃቂ ሁነት ለእልቂት የተዳረጉበት የአውሽዊዝ የመቅሰፍት ሠፈር ከዛም ሃንጋሪን ረፓብሊካዊት ቸክ ከጎበኙ በኋላ በሮማና በአሲዚ መንፈሳዊ ንግደት እንድሚያካሂዱ ኤግለዘ ዳ እሺያ የተሰየመው የዜና አገልግሎት ካስራጨው የዜና ምንጭ ለመረዳ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.