2016-07-18 16:27:00

ብፁዕ ካርዲናል ሱራፍኤል፥ ስለ አፍሪቃ በጋራ መትጋት


አፍሪቃ የበለጠ ክፍለ ዓለም ለማድረግ በጋራ መትጋት የሚል ጥሪ ያካተተ መልእክት የአዲስ አበባ ሊቀ ጳጳሳት የምስራቅ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል በርሃነየሱስ ሱራፍኤል በርዋንዳ ርእሰ ከተማ ኪጋሊ “የሴቶች መብትና ክብር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 10 ቀን እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ተካሄደው  27ኛው የአፍሪቃ አገሮች ኅብረት ጉባኤ መልእክት አስተላልፈው እንደነበር ቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ሕገ ወጥ ስደተኝነትና የሰው ልጅ ንግድ በርትቶ መዋጋት

ብፁዕ ካርዲናል ሱራፍኤል የአፍሪቃአገሮች ኅብረት ይረጋገጣል በማለት የወጠነው እቅድ ግቡን እንዲመታ የአፍሪቃ አገሮች ክፍለ ዓለሟን የበለጠች ለማድረግ በአንድነት መሥራት ይኖርባቸውል የሚል ምእዳን ባሰላለፉት መልእክት አካተው ሕገ ወጥ የስደተኝነት ጸኣትና እንዲሁም የሰው ልጅ ንግድ በጋራ መዋጋት ያለው አስፈላጊነት አሳስበው። የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳሳት በማስከተልም ኅብረቱ ለአፍሪቃ እድገት በሚል ርእስ ሥር እስከ 2063 ዓ.ም. ይጨበጣል ያለው እቅድ መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በማሳተፍ እንዲረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት ገልጠው እንዲህ ባለ መልኵም አንድነትና መተባበር በመላ ክፍለ ዓለሙ እውን በማድረግ ግቡን እንዲመታ አደራ ማለታቸውንም ፒሮ ገለጡ።

የ2063 ዝክረ ነገር ለመላ ክፍለ ዓለሟ እድገት የሚያረጋግጥ ሆኖ ግብር ላይ ይዋል

ለአፍሪቃ እጅግ አንገብጋቢነት ባላቸው በሰባት ደረጃ የተከፋፈለው የ 2063 ዓ.ም. ዝክረ ነገር በሁሉም ተቀባይነት ባለው እሴትና ግብረ ገብ የተመራ ማንንም የማያገል ተቀባይነት ያለው እድገት፡ ተሟይነትና ፖለቲካዊ ጥምረት መልካም አስተዳደር ዴሞክራሲ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሕግ ሉኣላዊነት ፍትሕና ሰላም ደህንነት ጠንካራ ማንነት የሕዝብ በተለይ ደግሞ የሴቶችና የወጣቶች እምቅ ኃይል የመጠቀም ብቃት ባለው መንገድ እንዲረጋገጥ ብፁዕነታቸው አደራ በማለት ይኽ የልማት እቅድ ግባዊ እይታው አፍሪቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋና ተወናያንና አግባብ ባለው መንገድ ሽርክና እንዲኖራት የሚያደርግ በጥምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ አወንታዊ ተጽእኖ ያላት ክፍለ አለም ለመሆን የሚያበቃት ሊሆን ይጠበቅበታል የሚል ጥሪ ባስተላለፉት መልእክት ማስፈራቸው ፒሮ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.