2016-07-13 16:21:00

የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ


የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 4 ቀን እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በኤኳዶር ርእሰ ከተማ ኪቶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የፍቅር ሐሴት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሓዋርያዊ ምዕዳን ድኅረ ሲኖዶስ ማእከል ያደረገ ዓውደ ጉባኤ ማካሄዱ ሲር የዜና አገልጎሎት አስታወቀ።

ይኽ የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚያስፈልገው ህዳሴ መለወጥ ላይ በማተኵር “ፍቅርን አወቅን  እርሱ ላይ እምነታችን አኖርን” በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ከመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን የቤተሰብ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ልኡካን የመላ ላቲን አመሪካ መናብርተ ጥበብ የቤተሰብ መርብታዊ ግኑኝነት አባላት በጠቅላላ ከሰማንያ በላይ የሚገመቱ ልኡካን መሳተፋቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ፥

የቤተሰብ ሰበር ወደ ምሉእነት ማሸጋገር

የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የመሩት በፖርቶ ሪኮ የካጉአስ ሰበካ ጳጳስ የመላ ላቲን አመሪካና ካሪቢያን ብፁዓን ጳጳሳት የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሩበን ጎንዛለስ መዲና መሆናቸው ጠቅሶ ጉባኤው ቤተሰብአዊ ፍቅር ያለው ውበት ያጎላና ለቤተሰብ በተለያየ ችግር ለተጠቃው ቤተሰብ የሚሰጠው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ኅዳሴ እንደሚያስፈገውና ይኽ ደግሞ ቤተሰብ ወደ ምሉእነት ለመሸኘት የልጆች ሕንጸት የምስጢረ ተክሊል መንፈሳዊነት የሚል ዓላማ ያለው ኅዳሴ መሆኑ ጉባኤው ያወጣው የፍጻሜ ሰነድ በማስደገፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራራታቸው ያመለክታል።

እውነተኛ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለውጥ

የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ እንደሚያመለክተው የሐዋርያዊ ምዕዳኑ እንኳር መልእክቱን ለይቶ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ገቢራዊ ለማድረግ እርሱም እያንዳንዱ ቤተሰብ ከሚኖረው ገጠመኝ ነጻ የሆነ ቤተሰብ ወደ ምሉእነት በመሸኘት እውነተኛ ለውጥ ለቤተሰብ በተለወጠ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት በመደገፍ ቤተሰብ በምኅረት ዓይን ቀርቦ በእውነተኛ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንና ኅይል የሚደገፍ የሐዋርያት ወንጌላዊነት መንፈስ በመከተል በተስፋኛው መንገድ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሚለይ ጸሎት አማካኝነት እያንዳንዱ ቤተሰብ የገዛ እራሱን ታሪክ እንዲያነብ መደግፍ ያለው አስፈላጊነት እንደተሰመርበት ብፁዕ አቡነ ሩበን ጎንዛለስ መዲና ማሳወቃቸው ሲር የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

የቤተሰብ መልካምነት ለዓለምና ለቤተ ክርስቲያን መጻኢ ያለው ወሳኝነት

የፍቅር ሐሴት ሓዋርያዊ ምዕዳን እንደሚያስገነዝበው የቤተሰብ ጥቅም ለዓለምና ለቤተ ክርስቲያን መጻኢ ወሳኝ መሆኑ ያሰመረበት ሃሳብ የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ አበክሮ በዚህ መንፈስ የቤተሰብ ወንጌል የሰው ልጅ ጥልቅ ስብእናው በሁሉም በእነዚያ እምነትና ግብረ ገብ አላስፈላጊ ነው የሚለው ባህል በሚስፋፋባቸው አገሮች ጭምር በማነቃቃት ቤተሰብና ጋብቻ ጥሪና የቅድስና ጎዳና መሆኑ በጽናት ማወጅ ያስፈላጋል በሚል ሃሳብ የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ መጠቃለሉ ብፁዕነታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.