2016-07-13 16:12:00

የሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ዚሞውስኪ ዜና ዕረፍት


የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙት ዚሞውስኪ በ 67 ዓመት ዕድሜያቸው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጧት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቲዚያና ካምፒዚ ገለጡ።

ነፍሴ ኄር ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 1949 ዓ.ም. በአገረ ፖላንድ በምትገኘው በኩፔኒን ከተማ ተወልደው እ.ኤ.አ. ግንቦት 25 ቀን 1973 ዓ.ም.  በታርኖው ሰበካ ጳጳስ በነበሩት በብፁዕ አቡነ ጀርዝይ ካሮል ኣብለዊች ማዕርገ ክህነት ተቀብለው  በፖላንድ የራዶም ሰበካ ጳጳስ እንዲሆኑ በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተሰይመው እ.ኤ.አ. መጋቢት 28 ቀን 2002 ዓ.ም. በዚያኑ ወቅት የሥርወ እምነት በሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በነበሩት በብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ራትዚንገር (ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ) ማዕርገ ጵጵስና ተቀብልው እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2002 ዓ.ም. የራዶም ጳጳስ ሆነው እንዳገለገሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካምፒዚ አያይዘው በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሰይመው የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር እንዲሆኑ ተሹመው በማገልገል ላይ እያሉ ታህሳው ወር 2014 ዓ.ም. ባደረባቸው የጣፊያ ነቀርሳ በሽታ ምክንያት በቫርሳቪያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ወደ አገረ ቫቲካን ተመልሰው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቀርብ ተባባሪነት በነበራቸው የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሐዋርያዊ ኃፊነት ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለዩባት ቀን ድረስ ማገልገላቸው ልእክት ጋዜጠኛ ካምፒዚ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.