2016-07-06 14:57:00

ከቤተ ክርስቲያን ቀውስ ማዶ፥ የበነዲክቶስ 16ኛ ር.ሊ.ጳ. መንበረ ሥልጣን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አሃድነትና  እርጋታ

እንደ ጠባቂ መላእክት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እርስ በእርሳቸው የሚጠባበቁ በሰብአዊና በመንፈሳዊ ደረጃም እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉ ናቸው። በዚህ መንገድም ያ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በገዛ ፈቃዳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ወንበረ ሥልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ ቀጥለው በተመረጡት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መካከል አቢይ ልዩነት እንዳለና ከዚህ ይባስም ብዙ የሚያጋጭ የአመለካከትና የሃሳብ ልዩነት እንደሚኖር ነው የሚል በእርግጠኝነት የተለያዩ ምሁራና የመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ሃተታ ሲያቅርቡበት የነበረና አሁንም የሚያቀርቡት ትንተና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የአሃድነትና የስምረት ትእምርት በመሆን ቅዱስ አባታችን በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የምታቀብ ነኝ ሲሉ በነዲክቶስ 16ኛም በተራቸው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከለላ ሥር ነኝ በማለት በሰጡት መግለጫ እንዳስተባበሉት በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ ኣባ ሮበርቶ ረጎሊ “ከቤተ ክርስቲያን ቀውስ ማዳ፥ የበነዲክቶስ 16ኛ ር.ሊ.ጳ. መንበረ ሥልጣን” በሚል ርእስ ሥር በደረሱት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ለንባብ ባበቁት መጽሓፋቸው በጥልቀት ያብራሩታል።

ታሪካዊ ራእይ አስፈላጊነት

ኣባ ረጎሊ በደረሱት መጽሓፋቸውም የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ስልጣናቸው ምን ተምስስሎው ክወናውና ፍጻሜው ምሉእነቱን በቫቲካን ዝግ ቤተ መዝገብ የታቀበው የበነዲክቶስ 16ኛ ሰነዳት ክፍት የሚሆንበት ጊዜ መጠበቁ ግድ ይሆናል ከሚል ሃሳብ ጋር በማጣመር ይተነትኑታል ። ነገር ግን መታወቅ ያለበት ልክ እንደ ቃለ ቅዱስ መጽሓፍና ወንጌላዊ ክፍለ ምዕራፍ ታሪክን በሙላት ለብቻው የሚገልጥ ሳይሆን ከሌሎች  የቅዱስ መጽሓፍ ክፍለ ምዕራፍ ጋር ተያይዞ የሚሄድ ነው፡ ይኽ ደግሞ በምሉእነት ለመተንተን ያስችላል። በዚህ መልኩም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ስልጣን ሊመጡ ከሆኑት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ምንም በልዩነት ቀጣይ ሃሳብ የሌለው በገዛ እራሱ ላይ ተዘግቶ የሚቀር አይደለም። ተያይዞ የሚሄድ መሆኑ በደረሱት መጽሓፍ ያብራሩታል።

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣን (ወንበር) የጎላ መልኩ(ዋነኛ መለያው)

የበነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ ስልጣናቸው የጎላው መልኩ ሲስተዋል፥ በቅድሚያ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለአንድነት ታልሞ የሚደርግ የጋራ ውይይት እንደ አብነት ለመጥቀስ ይቻላል። ሱታፌ ለሚለው ቃል በአዲስ ግልጸት የተነተኑ ለምሳሌም ከአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወደ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ የሚጠይቁ የሚከታተል ልዩ ክፍለ ሥርዓት ያቆሙና አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም ይኸንን የሳቸው ራእይ በመከተልም ወደ አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ለመግባት የሚጠይቁትን የሚከታተል ክፍለ ሥርዓት እንዲያቆሙ አግዟል። ከኢአማንያን ከግራ ዘመም ሄገላውያን ጋር ያነቃቁት ውይይት ስነ ሰብእ ዙሪያና በራቲስቦና እምነትና ሥነ ምርምር ርእስ ዙሪያ የሰጡት አስተምህሮ የበነዲክቶስ 16ኛ ሥልጣን ጉልህ መልኩ ከሚባሉት ውስጥ በጥቂቱ የሚጠቀሱ መሆናቸው አባ ረጎሊ በደረሱት መጽሓፍ ያመለክታሉ።

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አንድ ብቻ ነው

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በገዛ ፈቃዳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናቸው ካስረከቡ በኋላ መጽሓፉን ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተሳተፉት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ጋንስዋይን፥ ቤተ ክርስቲያን ሁለት አርእስተ እርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት በአንድ ጊዜ ሊኖራት አይችልም። ስለዚህ የበነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበረ ሥልጣን መልቀቅ ሁለት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲኖሩ የሚያደርግ ሁነት አይደለም ያሉትን ሃሳብ አባ ረጎሊ ጠቅሰው ሥልጣናዊ ተደማጭነት ያለው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አንድ ብቻ ነው፡ ሆኖም ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. የሚለው ሁነት ቲዮሎጊያዊና በሕገ ቀኖናዊ እንዲሁም በሥነ ቤተ ክርስቲያን ምርምር ደረጃ መልስ የሚያሻው ጥያቄ ከስቷል። በመሆኑም ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. የሚለው ሁነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የጥናት ዘርፎች በተለይ ደግሞ በቲዮሎጊያና በሕገ ቀኖና ደረጃ ጥልቅ ጥናት ተደርጎበት በማያሻማ ሁኔታ በሥልጣናዊ ትምህርት የተደገፈ ትርጉምና መልስ ሊሰጥበት የሚገባው ጥያቄ መሆኑ አባ ረጎሊ በደረሱት መጽሓፍ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.