2016-07-04 16:16:00

በእግዚአብሔር ስም መግደል ጸረ እግዚአብሔር ተግባር ነው


በባንግላዲሽ የራጅሻኒ ጳጳስ ለአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህና ሰላም ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጀርቫዝ ሮዛሪዮ በዳካ የተጣለው ግብረ ሽበራ ፈጽሞ ምክንያታዊ ሊሆን የማይችል ጸረ እግዚአብሔርና ጸረ ሰውና አገር ከመሆንም ባሻገር ለወጥረት የሚያጋልጥ ማኅበርዊ ሰላም ለማደፍረስ ያቀደ ተግባር ነው፡ እግዚአብሔር ሕይወት እንጂ ሞት አይደለም ብለው ሁሉም የምስልምና ሃማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸው የሰላም ሃይማኖት መሆኑ ለመመስከር ሊነሱ ይገባቸዋል እንዳሉ ኤሺያን ነውስ የዜና አገልግሎት አስታወቅ።

ሰላም በሁሉም ላይ ድል ይንሣ

የተጣለው ግብረ ሽበራ ሁሉም በአንድነት አለ ምንም ማቅማማት ሊያወግዙት ይገባል። ሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች። ማንኛውም ሃይማኖት ቅትለት ምክንያታዊ የሚደርግ ሊሆን አይችልም። የተጣለው ግብረ ሽበራ በሌሎች ሃማኖት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ለማንም የተሰወረ አይደለም። ሁሉም የአገሪቱ የምስልምና ሃማይማኖት ተከታዮች ይኸንን ግብረ ሸበራ በማውገዝ ለሞት ስለ ተዳረጉት ሁሉ አንዲጸልዩና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሞት ስለ ተዳረጉት በምታሳርገው ጸሎት እንዲያብሩ ጥሪ ማስተላለፋቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና እውገልግሎት አስታወቅ።

ስለ ተገደሉ መጸለይ አሸባሪያኑ እንዲለወጡም መጸለይ

የዳካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፓትሪክ ዳሮዛሪዮ በበኩላቸውም ግብረ ሽበራ ሁከትና የተሸበረ ኅብረተሰብ እንዲረጋገጥ የሚያደርግ የሞት ባህል ነው፡ ስለዚህ ምንም አይነት ፈጽሞ ምክንያታዊ ሊሆን የማይችለው ለግብረ ሽበራ የሚገፋፋው ምክንያት በሚገባ በቅንነትና በጽናት ተጢኖ  መፍትሔ ሊያገኝ ይገባዋል። የሁሉም አገሮች መንግሥታት አለ ምንም አድልዎ የመላ ዜጎቻቸው ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲችሉ ስለ መንግሥታት እንዲጸለይ አደራ ብለው ግብረ ሽበራ ስለ ፈጸሙት በመጸለይ አሸባሪያኑ እንዲለወጡ ስለ እነርሱም እንጸልይ ብለው ኢሰብአዊ ድርጊት የሚያልሙ ለጥፋትና ለሞት የሚያፈሱት ኃይላቸው ለሰላም ግንባታና ለተቃና ውህደት መረጋገጥ ዓላማ እንዲያውሉት ስለ እነርሱ እንጸልይ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ጠቁሞ፡ የአገሪቱ መራሔ መንግሥት ሻይክህ ሓሲና ግብረ ሽበራውን አውግዘው አሸባሪያኑ የተደናበሩ እሴት አልቦ በማለት ገልጠው የምስልምና ሃይማኖ ያለው እሴት የሚወክሉ አይደሉም በማለት እንደገለጡዋቸው አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.