2016-07-04 18:17:00

ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሰው ሊጠፋ አይፈልግም የሰው ፍጥረት ሁሉ እንዲድን ይፈልጋል


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዘወትር እሁድ እንደሚያደርጉት ሁሉ ትላንትና በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ በርካታ ምእመናን መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።  ቅድስነታቸው መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት  በደገሙበት ግዜ  የዕለቱ ቃለ ወንጌል ጠቅሰው መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ፍጥረት ለማዳን አምላክ እያለ ሰው በመሆን ከሰማየ ሰማያት ወረደ ዘወትርም ከእና ጋ ይገኛል ብለዋል። ምህረታዊ ፍቅሩ የሰው ሐጢአትን ደምስሶ ህያው ያደረጋል ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሰው ሊጠፋ አይፈልግም የሰው ፍጥረት ሁሉ እንዲድን ይፈልጋል እና ሰው ለመዳን መፈለግ አለበት ከእግዚአብሔር መራቅ የለበትም ቃል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት።

የእግዚአብሔር መንግስት በየዕለቱ ሊቋቋም እንደሚችል ጠቁመው  የእግዚአብሔር መንገድ መከተል ትእዛዛቱ መፍጸም በንጽህና መኖር ማፍቀር መርዳት ሰናይ ተግባርን መፈጸም ትሁትመሆን ማለት እንደሆነ አሳስበዋል። 

የተወደዳችሁ ምእመናን የኢየሱስ ክርስቶስ እና ቅዱስ ወንጌሉ ምስክሮች እንድንሆን ተጠርተናል እና ይህን ገቢራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ።    

12 ሐዋርያት  የኢየሱስ ክርስቶስ እና ቅዱስ ወንጌልን  ምስክሮች በመሆን አልፈዋል ክርስትያን ሁሉ የነሱ ዱካ መከተል ይጠበቅብናል ሲሉ አክለው ተናግረዋል። 

በየምህረት ዓመት እንደምንገኝ  በማስታወስ  ሮቡዕ ስድስተ ቀን እንደ ጎርጎርዮስ አቁጣጠር 

በቤተ ክርስትያን የምትዘከረው ቅድስት ማሪያ ጎረቲ ለሕልፈት ከመዳረግዋ በፊት ለገደላት ሰው ምህረት ሰጥታ በሰማዕትነት ማለፍዋ አመልክተዋል።

ከመልእከ  እግዚአብሔር ጸሎት  እና ትምህርተ ክርስቶስ  ፍጻሜ በኃላ ባለፈው ዓርብ በባንግላደሽ  ዳከ ከተማ ላይ   አሸባሪዎች  20 ሰዎች   በግፍ መግደላቸው  ትላንትና ደግሞ በዒራቅ  ባቅዳድ ላይ  የእስልማ አክራሪዎች  125 ሰዎች መግደላቸው  የሚታወስ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠው ለቤተ ሰቦቻቸው  እግዚአብሔር  ጽናቱ  እንዲሰጣቸው  ከምእመናን ጋር  በጋርዮሽ  ጸልየዋል።

ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር  ጥላቻ  የተናወጣቸውን  ሰዎች  ልብ እንዲቅይር እና ሰላሙ እንድያወርድልን እንጸልይ  በማለት ምእማናን አሳሰበዋል ቅድስነታቸው።

ነባራዊ ሁኔታው ክርስትያኖች ሁሉ የተስፋ የመጽናናት እና የሰላም መልእክቶች ለዓለማችን  ማድረስ ይጠበቅብናል በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ምእመናን  አሳስበው ሐዋርያዊ መልእክት ችረዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.