2016-07-01 16:31:00

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምኅረት በሮችን ሙሉ በሚሉ የሚከፍቱ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባቀረቡት ይፋዊ የኢዮቤልዩ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ ለመቀበል ከውጭና ከውስጥ ከመጡት በብዙ ሺሕ ከሚገመቱት ምእመናን ቅዱስ አባታችንን የምኅረት በሮችን ሙሉ በሚሉ የሚከፍቱ ናቸው በማለት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት የተልእኮ ሥልጣናቸው ምን ተመስሎው ከቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፡ ምኅረት ከዳር እስከ ዳር ሁሉም የሰው ልጅ የሚያካትት የሚነካ ለተናቁት ለድኾች ለስደተኞች ለተፈናቃዮች የሚቀርብ ተጨባጭ ተግባር አዘል መሆኑ በዚህ እየተኖረ ባለው የምኅረት ዓመት ቅዱስነታቸው በሚያቀርቧቸው አስተምህሮዎች ስብከቶች ና ንግግሮች የሚያሰተምሩት ሃሳብ መሆኑ ምእመናኑ የመሰከሩት ሲሆን፡ የቤተ ክርስቲያን ዋናው ተልእኮ ለሁሉም ሰው ልጅ የሆነው የክርስቶስ ምኅረት ትእምርት መሆን ነው፡ ተልእኮዋ ቅዋሜዋ ምኅረት መሆኑ ምእመናኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሚሰጡት አስተምህሮ ለመገንዘብ መቻላችው  በተሰጠው አስተምህሮ ከተሳተፉት አንደበት ለመረዳት መቻሉንም ታማሮ ያረጋግጣሉ።

የምኅረ ተግባር ተጨባጭ ነው። በግብረ ሰናይ ለጐረቤት ለባለንጀራ ቅርብ መሆን ነው፡ ስለዚህ ባለንጀራው ታማሚው እስረኛው ወላጅ አልባ ጋለማውታ በማስተዋል ልባዊና ተግባራዊ ምኅረት ለሁሉም ማቅረብ የሚል ነው፡ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣናቸው በምኅረት መንገድ የሚጓዝ ምኅረት ማእከል ያደረገ የቤተ ክርስቲያን ዋነኛው ተልእኮ የሚያሳስብ የሚመሰክር የሚያንጽ ፍቅር የሚመሰክር እጅጌ አጥፎ ጎንበስ የሚል የሚጸልይ ሕይወት የሚያሳስብ የአንቀጸ እምነት ወንጌላዊነት ባህርዩ በቃልና በተግባር የሚያሰምር ተካፍሎ መኖር መተሳሰብ እንዲኖር ይኽ ደግሞ ግብረ ሐዋርያት የሚያስተምረው ማኅበራዊና ሰብአዊ ሕይወት እንዲኖር የሚል መሆኑ ምእመናኑ ከልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ጋር ባካኤዱት ቃለ ምልልስ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.