2016-06-29 18:30:00

ከማንኛው ዓይነት መዘጋት ነጻ ኣውጥቶ መውጫ የሚያስገኝልኝ ዋና መሳርያ ጸሎት ነው።


ላቲናዊ ስርዓተ ኣምልኮ የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በዛሬው ዕለት የቅዱሳን ጴጥሮስንና ጳውሎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ኣከበረች፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ሁሌ እንደሚደረገው ቅዱስነታቸው በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ካርዲናላት ጳጳሳትና ካህናት ተሸኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ ኣሳረጉ፣ በቅዳሴው ፍጻሜም በዚሁ ዓመት የሊቀ ጵጵስና ሲመት ለተሰጣቸው የሚታደል በፓልዩም የሚታወቀው ኣክሚም የእረኝነትና ከር.ሊ.ጳ ጋር ውህደትን የሚያመልክት ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ መቃብር ላይ በተካሄደው ጸሎተ ዋዜማ ተባርኮ በመቃብሩ ካደረ በኋላ ዛሬ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ታደለ፣

ቅዱስነታቸው በቅዳሴው ይህንን ስብከት ኣቅርበዋል፣ ‘የዛሬው ስርዓተ ኣምልኮ ቃለ እግዚኣብሔር መክፈትና መዝጋት በሚሉ ቃላት ዙርያ የሚናገር ሲሆን ያ ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠ መክፈቻም የመክፈትና የመዝጋት ምሳሌ ኣድርገን ልንጠቀምበት እንችላለን፣ ዛሬ በቀረቡን ንባቦች መሰረት ሶስት ዓይነት መዘጋቶችን ልንመለከት እንችላለን፣ ኣንዱ በሓዋርያት ስራ 12.1-11 የተመለከተው የቅዱስ ጴጥሮስ በወህኒ ቤት መዘጋት ሁለተኛው ስለ ጴጥሮስ ለመጸለይ ከሁሉም ነገር ተለይታ የነበረች ማህበረ ክርስትያን መዘጋት፣ ሶስተኛው ደግሞ ጴጥሮስ ከውህኒ ቤት መልኣክ ነጻ ካወጣው በኋላ ቤቱን ባንኳኳ ግዜ ሮዳስ የምትባል ልጅ ምንም እንኳ ጴጥሮስ መሆኑን በድምጹ ብታውቀውም ልትከፍትለት ኣልቻለም ይህም ራሱ ኣንድ ዓይነት መዘጋት ነው፣

ከማንኛው ዓይነት መዘጋት ነጻ ኣውጥቶ መውጫ የሚያስገኝልኝ ዋና መሳርያ ጸሎት መሆኑ ቃለ ወንጌሉ ይገጣል፣ ጨንቀዋቸው ተዘግተው ይጸልዩ የነበሩ ማህበረ ክርስትያን ለራሳቸውም ይሁን ለጰጥሮስ በጸሎት መውጫ መንገድ ኣግኝተዋል፣ የክርስትያኖቹ መዘጋት ስደትና መከራን በመፍራት ሲሆን ያ ያሳረጉት ጸሎት ጴጥሮስን ረድቶ ከእስር መውጫ መንገድ ሲያስገኝለት ለማህበሩም ከነበራቸው ፍርሃትና ጥራጣሬ የነጻነት በር ሆነላቸው፣ ሁኔታውን የሐዋርያት ስራ` ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።’(12.5) ሲል ይገልጠዋል፣ ጴጥሮስ ለተጠራበት ኣግልግሎት ስራ በመጀመር ላይ ሳለ ነው ሄሮድስ ያዕቆብን ገድሎ እርሱን ያሳሰረው፣ ነገር ግን የማህበረ ክርስትያኑን ጸሎት እግዚኣብሔር ስለተቀበለው መልኣኩን ልኮ ጴጥሮስ ከውህኒ ቤት በማውጣት በሄሮድስ እጅ ከመሞት ያድነዋል፣ በትሕትና ለእግዚኣብሔር ፍላጎት በመገዛት የሚደረገው ጸሎት ሁሌ ለግላዊ ጉዳይም ይሁን ለማሕበራዊ ጭንቀት መውጫ ያስገኛል፣

ቅዱስ ጳውሎስም ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ ‘ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ’ (2ጢሞ 4.17) በማለትም ምንም እንኳ የሞት ፍርድ ባከባቢው ቢንዣበብ ጌታ ኣጠገቡ እንደነበረና ስብከተወንጌሉን እንዲቀጥል ነጻ እንዳወጣው የገዛ ራሱን ተመኲሮ ይጽፋል፣ ይህ ጳውሎስ የሚናገረው ክፍተትና ነጻነት ግን ወደላቀው ወደላየኛው ዘለዓለማዊው ነጻነትም ነው፣ የሓዋርያው ወደ ክፍቱ የመውጣት ታሪክ እንደገና ማየቱ ጥሩ ነው፣ መጀመርያ ሁሉንም ትቶ ወንጌል ለመስበክ ይወጣል፣ የዚህ ዓላማ መጨረሻም ‘በሰላም ክፍት ወደ ሆነው ሰማይ መመንጠቅ ወደ መንግስተ ሰማያት መምጠቅ መሆኑ ነው’፣

ወደ ጴጥሮስ የተመለስን እንደሆነ በማቴዎስ ወንጌል 16.13 ጌታ ‘ክርስቶስ መሆኑና የእግዚኣብሔር መሆኑን’ ይመሰክራል፣ ይህንን የገለጠለት ደግሞ ልቡ በመክፈቱ የእግዚኣብሔር መንፈስ ነው፣ ከዚህ ግዜ ጀምሮ ጴጥሮስ ጉዞውን ይጀምራል፣ ይህ ጉዞ ረዥምና ኣድካሚ ብዙ ውጣ ውረድ ያለበት ነበር፣ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ` እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤’ (ሉቃ 22.32) በማለት ዋስትና ስለሰጠው እንዲሁም ይህ ጥሪ ለገዛ ራሱ ብቻ ሳይሆን ለወንድሞቹም እንደሆነ ሊይስረዳውም ‘አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና’ ብሎ ኣደራ ይለዋል፣ ምንም እንኳ ኣልክድህም ብሎ ቢፎክር ሶስቴ ሲክደው ይገኛል ግን ያች የጌታ ጸሎት ስላለች ከጌታ ኢየሱስ ጋር ዓይን ለዓይን በተጋጩበት ግዜ ወዲያውኑ ተጸጽቶ ማልቀስ ጀመረ(ሉቃ 22.61) ይህ ውርደትም ከእብሪትና እኔነት እስረኛ መሆን ነጻ ኣወጣው፣ እንዲሁም ፍርሃትን ኣስወግዶ ብርታት ኣለበሰው በዚህም በሁሉም ማለት እስከ በመስቀል ተሰቅሎ መሞት ጌታን ለመመስከር በቃ፣

ሶስተኛው መዘጋት ደግሞ ሮዴ የምትባል ገረድን ያጋጠመ ነው፣ ጴጥሮስ መሆኑ በድምጹ ኣውቃ ሳለች ሰዎችም በቤት ተዘግተው ለእርሱ እየጸለዩ መሆናቸውን እያወቀች ታላቅ ደስታም ቢፈጥርላት ልትከፍትለት ግን ኣልቻለችም፣ ይህም ኣንድ ዓይነት መዘጋት ነው፣ ማድረግ ያለብህን ቀላሉን ነገር እንኳ ላለማድረግ እጆችህና ኣእምሮህን የሚዘጋ ፍርሃት ወይም ድንዛዜም መከፍቻ የሚያስፈልገው ነው፣ ፍርሃት ሁል ግዜ እንድንጠራጠርና እንድንደንዝዝ ያደርገናል፣ እግዚኣብሔር ለሚገልጥልና ለሚሰጠን ያልታወቀ ጸጋ ዝግ እንድንሆን ያደርገናል፣ ይህ ዓይነት ፍርሃት ለቤተክርስትያን ፈተና ከሚሆኑ ነገሮች ኣንዱ ነው፣ በፍራቻ እየተንከተከቱ በገዛ ራሷ ተዘግታ የመቅረት ፈተና እጅግ ኣዳጋች ነው አለ። ስለዚህ እግዚኣብሔር በእኛ ላይ እንዲሰራ ለጸሎታችን የሚሰጠንን መልስ ለመቀበል ከመዘጋት ወደ መከፈት ማለፍ ያስፈልጋል ከፍርሃት ወደ ብርታት ከሓዘን ወደ ደስታ በመጨረሻም ከመከፋፈል ወደ ኣንድነት ያሸጋግረናል፣ ይህንን ደግሞ ለዚሁ ታላቅ በዓል ከእኛ ጋር ኣብረው እንዲጸልዩና ያለንን ቅርበት ለመግለጥ መካከላችን የሚገኙ የተከበሩ ኢኩመኒካዊ ፓትርያርክ በርጠለሜዎስ ከላክዋቸው ተወካዮች ጋር ልንደግመው እንችላለን፣ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ ኣብረን በደስታ እንድንጓዝ ነጻ የሚያወጥእውን የእግዚኣብሔር ጸጋ ለሁሉም የሚሆን ምስክርነት እንድሰጥ ዘንድ ያማልዱልን፣ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.