2016-06-29 15:39:00

በርጥለመዎስ ቀዳማዊ፥ ክርስቲያናዊ አንድነት እውነት በፍቅር ነው


እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በተከበረው በሮማ ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ቅዱሳን ጴጥሮስ ዎጳውሎስ ዓመታዊ በዓል ለመሳተፍ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በርጠለመዎስ ቀዳማዊን ወክለው ቅድስት መንበር የገቡት ልኡካን በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉላቸው መልእክት ከቅዱስነታቸው በበዓሉ ዕለተ ዋዜማ እ.ኤ.አ. ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ማስረከባቸው የቫቲካን ራዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ያስተላለፉት መልእክት ስደተኞች እናሳ የኅብረተሰብ ክፍል ለመከላከል የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን በጋራ የሚሰጡት አገልግሎት በዚህ በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ባለው የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቀውስ መፍትሔ እንዲገኝለት የሚያሳስብና እንዲህ ባለ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ ፊት ክርስቲያናዊ መሰረተ ደንብ እጅግ አስፈላጊ ነው። የሚል ሃሳብ የተኖረበት ሲሆን አቢያተ ክርስትያን የጸንፈኝነት የአድልዎና የስደት የማኅበራዊ ኢፍትሓዊነት ድኽነት እና የእርሃብ ሰለባ የሆኑት የሚያሰሙት ፍትህ ጠያቂ ጭኾት የራሳቸው የሚያደርጉ መሆንቸው ጠቅሰው ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በመሆን በለስቦ የሚገኙትን ስደተኞችና ተፈናቃዮች ድጋፍና ብርታት እንዲሁም ተስፋ ለማቅረብ ታልሞ በዚህ ብቻ ሳይታጠርም ለዚህ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እየታየ ያለው አቢይ ሰብአዊ ቀውስ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ሰላማዊ መፍትሔ ያፈላልግ ዘንድ ለማሳሰብ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዘክረው፥

የኤውሮጳ ሥልጣኔ አለ ክርስቲያናዊ ስርወ መሰረት ማስተዋል ያዳግታል

ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ባስተላለፉት መልእክት ኤውሮጳን በመመልከት ወቅታዊው የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቀውስ መፍትሔ እንዲያገኝለት የኤውሮጳ አህጉራት ያንን ወንድማማችነትና ማኅበራዊ ፍትሕ የሚለው ክርስቲያናዊ ሥርወ መሰረት መርህ በማድረግ እንዲጋፈጡት ያስፈልጋል ብለው። የኤውሮጳ ሥልጣኔ ካለ ክርስትያናዊ ስርወ መሠረት መረዳቱ ያዳግታል። ከዚህ በመንደርደርም የኤውሮጳ መጻኢ አንድ ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል በኤኮኖሚ ላይ ብቻ የተገነባ ወይንም አክራሪ ኅብረተሰብ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ በክርስትያናዊ ባህል የተገነባ የትብብር ባህል በተራቀቀው የእደ ጥበብ እድገትና በዓለማዊነት ትሥሥር ብቻ ይከወናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው እንዳሉ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

የክርስቲያናዊ አድነት ሂደት የእውነት በፍቅር ላይ የጸና ውይይት መሠረት ያደረገ ነው

ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ባስተላለፉት መልእክት ለጋራ ጥቅም ታልሞ ሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ለአንድነት አልመው የሚያደርጉት የጋራው ጉዞ ያንን ማኅበራዊ ክፋት በፍትህና በሰላም መቃወም በሚል ጥረት ለሰብአዊ ጥቅምና ነጻነት ያነጣተረ መሆኑ ገልጠው። ስለ ክርስቶስ ቤተ ክስቲያን  የሚሰጠው አንድ የተዋጣለት ትክክለኛና መልካም ምስክርነት የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ወቅታዊው ተጋርጦ በሚገባ ለመጋፈጥ የሚያበቃቸው ያለባቸው የመንፈሳዊ ኃላፊነት መሠረት የሚያካሂዱት የጋራ ጥረት የሚያበረታ ነው ብለው፥ በኦርቶዶክስና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መካከል ለተሟላ ውህደት ታልሞ የሚደረገው የጋራው ውይይት ያንን የጋራ አርአያ የሚያረጋግጥ ወደ ቲዮሎጊያዊ እውቅና ወደ የጋራው ገጠመኝና የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መንፍሳዊነት ሃብታም የሚያደርግ እውነት በፍቅር የሚል ውይይት ነው እንዳሉ የገለጡት ኢዛበላ ፒሮ በማስከተል፥

ተፈጥሮና ፍጥረትን ለመንከባከብ ምኅዳራዊ ለውጥ

ብዙውን ጊዜ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ተፈጥሮንና ፍጥረትን መንከባከ ያለው አስፈላጊነት በማስመልከት በሚሰጡት ምዕዳንና በሚያቅርቡት ቀጣይ ጥሪ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባህ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በዋቢነት የሚገለገሉበት መሆኑ አስታውሰው ወቅታዊው የምኅዳር ቀውስ መንስኤ ከሆኑት ውስጥ መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ ቀውስ አንዱ መሆኑ አብራርተው ምኅዳራዊ ቀውስ ለመፍታት ተፈጥሮ ለመጠቀም የሚደረገው ስልት ሥር ነቃላዊ ለውጥ ያሻዋል እንዳሉ ያመለክታሉ።

የመላ ኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ፍሪያማነት መጸለይ

ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ያስተላለፉት መልእክት፥ ባለፈው እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጠቃለለው ካንድ ሺሕ ዓመት በኋላ የተካሄደው ቀዳሜ የመላ ኦርቶዶክሳዊያን አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በማስታወስ ለፍርያማነቱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዲጸልዩ ተማጥው። ጌታ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቤተ ክርስትያንና ለክርስቲያኖች አንድነት ጥቅምና በተለያየ ስቃይ እጅግ በመጎሳቆል ላይ ለሚገኘው ሁሉ እርባና ብርታቱንና ኃይሉን ይስጣቸው በሚል ጸሎት ያስተላልፉት መላክት እንዳተቃለሉ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.