2016-06-27 16:44:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ እርቅ በአርመንና በቱርክ መካከል ሰላም በናጎርኖ ካራባክ


የዛሬ አንድ ዘመን በፊት በአርመን ላይ የተጣለው ጃምላዊ ቅትለትና እልቂት ፈጽሞ ዳግም እንዳይከሰት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በየርቫን የአርመን ረፓብሊክ ሕንፃ ተገኝተው ከ50 ሺሕ በላይ የሚገመቱ የአረን ዜጎች አቀባበል ተደርጎላቸው ባሰሙት ንግግር ጥሪ በማብቅረብ በዚህ ከካቶሊኮስ ካረኪን ዳግማዊ ጋር ባካሄዱት የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የጋራ ግኑኝነት ቅዱስነታቸው በአርመንና በቱርክ ህዝብ መካከል የእርቅ መንገድ እንዲነቃቃና በናጎርኖ ካራባክ ሰላም እንዲረጋገጥ እንዲሁም ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ወደ ምሉእ አንድነት አብረው በጋራ ኣንዲያቀኑ መጸለያቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።

ከሮማ የተነሱ መንፈሳዊ ነጋዲ ቅዱስ አባታችን ሁሉንም በያረቫን በሚገኘው በአርመን ረፓሊክ አደባባይ የተገኙትን ሁሉ በፍቅር አይን በመመልከት የአርመን ሕዝብ ጽኑ እምነቱንና ጥልቅ ስቃዩን አስታውሰው በወንጌል ምስክርነት ሃብታም በማለት እንደገለጡት የጠቀሱ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ፥

ዓለም ዳግም በተመሳሳይ የክፋት መንፈስ ሥር እንዳይወድቅ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የዛሬ 100 ዓመት በፊት በአርመ ሕዝብ ላይ በተጣለው እልቂት ሰለባ የሆኑትን አንድ ሚሊዮን ከግማሽ አርመናውያንን በማሰብ፥ በዚህ በጋራው ጉዞ ብዙ ምስክርነ የሰጡ በተለይ ደግሞ በዚያ አንድ በሚያደርገን በክርስቶ ላይ ባለን እምነት ምክንያት የደም ሰማዕትነ የከፈሉት በሰማይ ከዋክብቶቻን በመሆን በእኛ ላይ የብርሃን ነጸብራቅ በማውረድ በዚህ በምድራዊ ሕይወታቸው ለሙሉ ውህደት ታልሞ በሚደረገው ጉዞ ልንከተለው የሚገባንን መንገድ ያመላክትሉናል። ስለዚህ በአርመን ህዝብ የተሞከረው መራራው ገጠመኝ ማስታወስ ያስፈጋል። የዛሬ 100 ዓመት በፊት በአርመን ህዝብ ላይ ያ የክፋት መንፈስ ያወረደው ዓቢይ ዕልቂት በሰው ልጅ አእምሮ የታተመና ልብን የሚያቃጥል ታሪክ ነው። ስቃያቸውም የክርስቶስ አካል ላይ የወረደው የስቃይ ምስጢር ሱታፌ ነው፡ ስለዚህ የደረሰው አሰቃቂው ዕልቂት ማስታወሱ አስፈላጊና ግዴታ ቢሆንም ቅሉ በዓለም ተመሳሳይ አስከፊ ዕልቂት ዳግም እንዳይከሰት ማስጠንቀቂያ ጭምር ነው፡ ያ መራራው ስቃይ የጥላቻና የቂም በቀል ምክንያት ማድረግ ሳይሆን አለ የብቀላ መንፈስ ለመጻኢ የሰላም ዘር እመሆኑ እውቅና በሚሰጥ ተግባር ማስታወስ ነው እንዳሉ ዶኒኒ አስታወቁ።

በአርመንና በቱርክ ህዝቦች መካከል እርቅ

ሁሉም በጋራ የግኑኝነት ባህል እንዲገነቡ በሚደረገው ጥረት እንዲረባረብ በማሳሰብ መጻኢያችሁ ጌታ ይባርክ እርመንና ቱርክን ወደ የእርቅ መንገድ ይምራ። በናጎርኖ ካራባክ ሰላም ይስፈን፡

ወደ ምሉእ ውህደት ማቅናት

ቅዱስ አባታችን ባሰደመጡት ንግግር ወደ ምሉእ ውህደት ያቀና የሚደረገው የጋራው ጉዞ በማሰብ ይኽ ግኑኝነት በመጨረሻዎች ዓመታት በተካሄዱት ግኑንነቶች እየተጠናከረ መምጣቱንም ገልጠው በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ሐዋርያዊ ሱታፌ ለማጎልበት ሁሉም በዚህ እንደሚገኙና ቀደሜ የክርስትና እምነት የተቀበለው የአርመን ህዝብ ለተቀበለው እምንት ታማኝና መስዋዕት ጭምር የከፈለ መሆኑም እስታውሰው እዚህ በጋራ መገናኘቱ ጽንሰ ሃሳብ ለመለዋወጥ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለመለዋወጥ ያንን ምሉእ ውህደት እርሱም ቅዱስ ቁርባናዊ ውህድት እውን የሚሆንበትን ቀን በማሰብ መሆኑ ያብራሩት ቅዱስነታቸው አክለውም በዚህ ለአንድነት በሚደረገው ጉዞ በ 12ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩ ቅዱስ ካቶሊኮስ ነርሰስ ሽኖርሃሊን ውህደተ እንዲረጋገጥ የሰጡት አስተዋጽኦ በማስታወስም ለውህደት  ጸሎትና እርስ በእርስ መፈቃቃር አስፍላጊ ነው፡ ፍቅር ብቻ ነው ቅድመ ፍርዶችን የሚሰርዘው። ግትር ያለ ርእሰ እማኔና የግል ጥቅም በትሑት ፍቅር ስም ወደ ጎን እናድርግ እንዳሉ ዶኒኒ አስታወቁ።

የራስ ጥቅም ለማካበት የግል ርባና  የመመልከቱ ዘመምነት አግሎ የእግዚአብሔ ምህረት የኢየሱስ ቡራኬና የመንፈስ ቅዱስ የተትረፈረፈ ቡራኬ  በሚማርክ በትሁት ፍቅርና በለጋስነት መንፈስ መኖር። በእውነተኛ ልብ እርስ በእርስ በእውነት በመዋደድ በትህትና ጸጋ የሆነው ምሉእ ውህደት ለመቀበል ገዛ እራሳችንን ክፍት እናድርግ። በቁርጠኝነት በዚህ ለምሉእ ውህደት ታልሞ የሚደረገው ጉዞ እንቀጥልበት።

መካከለኛው ምስራቅ እያደማ ያለው አመጽ

ኢየሱስ ሰላሙን ይሰጣል። ይኸንን ሰላም ላለ መቀበል በሰላም ጎዳና ላለ መጓዝ የሚዳርጉ መሰናክሎች ጦርነቶችና የጦርነት መዘዞች በዓለማችን እጅግ ብዙ ናቸው ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ በማሰብ የጥላቻና የቂም በቀል የግጭቶ መንስኤ ግጭት ጦርነት ሁከት የሚያባብሰው የጦር መሣሪያ ንግድ እና የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር በተለይ ደግሞ የድኾች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት መሆኑም አብራርተው፥

አርመናውያን የሰላም መልእክተኞች ይሁኑ

ሌላው ታላቁ የሰላም መስካሪ አርመናዊው ቅዱስ ጐርጐሪዮስ ዘናረቅ ቅዱስ አባታችን የቤተ ክርስትያን ሊቅ በማለት የሰየሙዋቸውን አስታውሰው እኚህ ቅዱስ የሚወጉኝን እንዲለወጡ አድርግ እንጂ አታጥፋቸው በማለት ለሚጠሉዋቸውና ለሚያሳድዱዋቸው ሁሉ ይቅርታንና ምኅረትን የለመኑ ለሁሉም ምኅረት የተማጸኑ የሰላም ሊቅ ሊባሉ ይገባቸዋል ብለው፥ በተለያዩ አገሮች ተሰደው የሚኖሩት የአምረን ተወላጆችን ሁሉ በመንፈስ በማሰብ በምትገኙበት ሁሉ የሱታፌና የውህደት መስካሪያን ሁኑ። ዓለም የእናንተ ምስክርነት ይሻል። ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው፥

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ንግግር ከማደመጣቸው ቀደም ብለው ካቶሊኮስ ካረኪን ባሰሙት ንግግር ሰላም ያለው አስፈላጊነት ጠቅሰው በአርመናውያን ላይ የደረሰው እልቂት ቅዱስነታቸው በማስታወሳቸው አመስግነው ሁሉም ፍትህ ለማረጋገጥ የሚተጉ  ሁሉ የተመስገኑ ናቸው። ከቱርክ ጋር ግኑኝነት በናጎርኖ ካራባክ ሰላም እንዲሁም ከአዘርበጃን ጋር ያለው ውጥረት እንዲረግብ ሰላም ተማጥነው ስለ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ውህደት በመጸለይ የዚህ ትእምርት ናቸው የሚባሉት ተግባሮችም በጋራ መከወናቸ እንዳስታወሱም  አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.