2016-06-27 16:42:00

መለኮታዊ ሊጡርጊያ በኤትችሚያድዚን፥ ቅዱስ አባታችን ምሉእ ውህደት ተማጸኑ


በዚያ በሚምረውና በሚያስታርቀው ፍቅር ስም በብርቱ ጉጉት ለምንጠባበቀው ውህደት በጋራ መጓዝ፡ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአርመን ያካሄዱት 14ኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በኤትችሚያድዚን የምስራቅ ሥርዓት የአርመን  ሐዋያዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ  ካቶሊኮስ ካረኪን ዳማዊ የተመራ በኤትቺሚያድዚ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መንጠሊና በማጥለቅ መሳተፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዳሴው ሥነ ስርዓት ወቅት ባሰሙት ንግግር ለካቶሊኮስ ካረኪን ዳግማዊ ወንድማዊ ሰላምታቸው አቅርበው “በእነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ወንድሞች አብረው ሲጓዙ የሚሰጠው ደስታ ተመክሮ ለማጣጣም ችለናል። የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ተስፋ ያች አንድ መሆንዋ የምናምንባትና የምናስተውላትን የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አሳሳቢ የሆነው ጉዳይ ሁሉ በቱሁት መንፈስ ለመጋራት መቻሉን ሲገልጡ፥ “በተጠራችሁ ጊዜ ለአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ። እንዲሁም አንድ ጌታ አንድ እምነትና አንድ ጥምቀት አለ። ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነው በሁሉም የሚሠራው በሁሉም የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ” (ኤፌ. 4,4-6) ጠቅሰው በማብራራት፡ ቅዱስ በርጠለመዎስና ታደዮስ በዚህች በአርመን ምድር ወንጌልን ሲያበስሩ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስም በሮማ ሕይወታቸውን ለጌታ ሰውቷል፡ የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ተስፋና ጉጉት የሆነው ውህደት መንፈስ ቅዱስ የፍቅርና የአንድነቱን እሳት በማውረድ ያንን በክርቶስ ተከታዮች መካከል የሚታየው መሰናክል የሆነው መከፋፋል  ያቃጥል፡ አንድነቱን ይጸገውም ዘንድ ተማጽነው፡ በሁሉም ዘንድ የአንድነት ብርቱ ጉጉት አለ። ይኽ ምሉእ ውህደት ማለት ደግሞ አንዱ ለአንዱ መገዛት ወይንም መንበርከክ አንዱ በሌላው መጠቃለል መዋጥ ማለት ሳይሆን በመንፈስ ቅዱ አማካኝነት እግዚአብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተከወነው አቢይ የድህነት ምሥጢር ለዓለም ለማሳወቅ የሚበቃ ለእያንዳንዱ የሰጠው ጸጋ ማስተናገድ ማለት ነው እንዳሉላ ቨላ አስታወቁ።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓለም የሚታየው አመጽ ስቃይ ሁሉ በማሰብ፥ የቅዱሳኖች ጥሪ እናስተውል የትሁታንና የድኾችን የጥላቻ የቂም በቀል ሰለባ የሆኑትን እረሮ ስለ እምነታቸው ሕይወታቸውን የሚሰዉትን እንዳማጥም፡ ከባለፉት በታሪክ የሞገለጡት ልዩነቶች ሁሉ ነጻ የሆነ መጻኢ ለሚመኘው ወጣት ትውልድ የሚያዳጥ ጆሮ እንስጥ እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ላቨላ አያይዘው፥ ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን ዳግማዊ ባስደመጡት ስብከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓለም በሁሉም አገሮችና ሃይማኖቶች መካከል ሰላም እውን እንዲሆን በጋራ በሚያካሂዱት ጥረት የሁሉም ሰው ልጅ ብልጽግናና የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ እንዲቻል የሚሰጡት አስተዋጽኦ ያስታወሱም ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ለአገረ አርመንና ለአርመን ቤተ ክርስቲያን ጸልየው ከካቶሊኮስ ካረኪን ዳግማዊ ጋር በመተቃቀፍ ሰላምታ ከመለዋወጣቸው ቀደም በማድረግ የተሟላ ውህደትና ሱታፌ እንዲረጋገጥ ከልብ የመነጨ የጋራ ትጋት በማነጣጠር ካቶሎኮስ ካረኪን ዳግማዊ በእግዚአብሔ ስም እኔናና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በጋራ ለምሉእ ውህደት የሚደርገው ጥረት ይባርኩ” እንዳኡም ገልጠው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የመጨረሻውና ሦስተኛው ቀን የአርመን ሐዋያዊ ጉብኝታቸውን ጧት በኤትችምያድዚን በሚኘው  ጳጳሳዊ ሕንፃ በተተከለው ጸሎት ቤት በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ማረክ ሶልችዝይንስኪ ታጅበው የሓርዋያዊ ወኪል ቢሮ አባላት የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ከ 14 በአርመን ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳትና ከ112 ካህናት ጋር መገናኘታቸው  አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.