2016-06-24 17:02:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግኑኝነቶች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በፊት የቅዱስ ኤጂዲዮ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ መሥራች ፕሮፍፈሰር አንድረያ ሪካርዲ፡ ቀጥለውም የማልታ ሉኣላዊ ወታደራዊ ደንብ ልዑልና አቢይ መምህር ክቡርነታቸው ወንድም ማቲዩ ፈስቲንግ፡ በተባበሩት መንግስታት የምግብና እና የእርሻ ድርጅት ጠቅላይ አስተዳዳሪ ኾሴ ግራዚያኖ ዳ ሲልቫ ጋር መገናኘታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስ አባታችን  በቅድስት መንበር ለኵባ ልኡከ መንግሥት እንዲሆኑ ከመንግሥታቸው ለተላኩት ክቡርነታቸው ኾርገ ከሳዳ ኮንሰፕሲዮን  እንዲሁም በቅድስት መንበር ለፈረንሳይ ልኡከ መንግሥት ሆነው እንዲያገለግሉ ከመንግሥታቸው ለተላኩት ክቡርነታቸው ፊሊፐ ዘለር ቀጥለውም የፖላንድ ልኡከ መንግሥት በቅድስት መንበር እንዲሆኑ የተላኩት ክቡርነታቸው ያኑች ካታኒስኪ ያቀረቡትን የሹመት ደብዳቤዎች መረከባቸውንም በማሳወቅ፡ በመጨረሻም በቅድስት መንበር የታላቅዋ ብሪጣንያ ልኡከ መንግሥት በመሆን ያገለገሉት ያገልግሎት ዘመናቸው አጠናቀው ወደ አገራቸው የሚመለሱትን  ክቡርነታቸው ኒገል ማርኩስ ባከር ያቀረቡት የሥንብት ደብደቤ ተቀብለው ማነጋገራቸው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.