2016-06-24 16:53:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ለአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


በአርጀንቲና ቱኩማና ሰበካ ባለፉት ቀናት “ኢየሱስ ክርስቶስ የታሪክ ጌታ፡ እንተ ታስፈልገናለህ” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ ወደ ተካሄደው የአርጀንቲና 11ኛው  ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት የተጋረጠባችሁ ችግርና ውጣ ውረድ ሁሉ ጠንቅቄ የማውቁት ጉዳይ መሆኑ ገልጠው ለዚያ አገር ህዝብና ቤተ ክርስቲያን ቅርበታቸው ኣንዳረጋገጡ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ሲቻል፡ ቅዱስነታቸው በዚህ በይድረስ ለአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ኾሴ ማሪያ አራንሰዶ በኩሉ ለአገሪቱ ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ባስተላለፉት አጭር መልእክት  አርጀቲና የተደቀነባት ችግር ሁሉ ከእምነት በሚገኘው ኃይል አማካኝነት በመጋፈጥ ፍትህ ፍቅር በሕዝባችና ምእመናንም መካከል እንዲሁም ድኾችን የማገልገል መንፈስ እንዲበረታ ጸሎቴ ነው ኣንዳ የገለጡት ጂሶቲ አያይዘው፥

የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ዝናብ ሁሉን ያረስርስ፡ በእርሱ ፍቅር ተመርቶ በፍቅር አገልግሎት መጠመድ ሊያስፈራን አይገባም

የአርጀንቲናው 11ኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ ሄደት አርጀንቲና ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ዝክረ ሁለት መቶኛው ዓመት ጋር ተያዞ የሚካሄድ በመሆኑ ያለው ድርብ ትርጉም በማስታወስ፡ ኩራ ብሮከሮን ጠቅሰውም የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ወንዝ ሁሉን ያረስርስ በጌታ ፍቅር ተመርቶ በፍቅሩና ስለ ፍቅሩ መጠመድ አደራ ሊያስፈራን አይገባም ብለው  በጸሎት እንተሳሰብ አደራ ስለ እኔም ጸልዩ በማለት ያስተላለፉት መልእክት ማጠቃለላቸው ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.