2016-06-24 17:08:00

ኢዮበልዩ ቅዱስ የምኅረት ዓመታት ታሪክ


ኢዮቤልዩ፡ መፈሳዊነት ታሪክና ባህል በሚል ርእስ ሥር 450 ገጾች አዘል ፕሮፈሰር ሉካ ማሲዳ ያጠንቀሩት የኢዮቤሊዩ የምኅረት ዓመታት ታሪክ የሚያወሳ መጽሓፍ በኡተት ማተሚያ ቤት የታተመው  እ.ኤ.አ. ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የኢጣልያ ልኡከ መንግሥት ሕንፃ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር እየተኖረ ያለው የምኅረ ዓመት አቀነባባሪ ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በመሩት ዓውደ ጉባኤ ለንባብ መብቃቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ ገለጡ።

መጽሓፉን ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ንግግር ያስደመጡት በኡቴት ማተሚያ ቤት አበይት የድርሰት ሥራዎች ጉዳይ ለሚከታተለው የኅትመ ክፍል ሊቀ መንበር ፋቢዮ ላዛሪ፥ በተለያዩ ዘመናት የተከበሩት ኢዮቤሊዮ ቅዱስ የምኅረት ዓመት ከተኖረባቸው ወቅትና ታሪክ ጋር ጥምረት ያላቸው ቢሆንም አንድ የሚያደርጋቸው ቲዮሎጊያዊ ሂደት መኖሩ ገልጠው። የባህሎች የሕዝቦችና የቋንቋዎች መገናኘት የሚታይበት ሰብአዊ ኤኦኖኢያዊ መስኅባዊ ገጽታ ያለውና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ መቃብር ሥፍራ ለመሳለምን በቅዱስ በር ለመግባት የሚጎርፍበት ቅዱስ ሁነት ነው ሲሉ፥ ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በበኵላቸውም፥ ምኅረት በኅብረተሰብና በቤተ ክርስቲያን ዳግም ማእከላዊነቱ እየተረጋገጠ ነው ብለው። የምኅረት ሥራ በማከወን ረገድ ስናድግ እውነተኛ ባህላዊ አቢዮት እንሠራለን ብለው፡ ክርስትና የእግዚአብሔር ምኅረት መግለጫ ነው እንዳሉ ጓራሺ ያመለክታሉ።

በቅድስት መንበር ለኢጣሊያ መንግስት ልኡክ ዳኔለ ማንቺኒ በበኵላቸውም፥ በዚህ በአሁኑ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉት ከሚያገናኝ ድልድይ ይልቅ የሚለያይ የግንብ አጥር እየተስፋፋ ባለው ዓለም ባንድ ጎኑ ዓለማዊነ ትስስር ተብሎ ይሰበካል በሌላው ረገድ ደግሞ ለያዩ የግንብ አጥር ከፍ እያለ ነው፡ ስለዚህ ይኽ የምኅረት ዓመት የሕዝቦች የባህሎች ግኑኝነት የሚያነቃቃ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረድዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጓራሺ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.