2016-06-24 19:05:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በአርመን ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በኤስያ ክፍለ ዓለም በአርመን ለሶስት ቀናት የሚዘልቅ  ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማከናወን ዛሬ ጥዋት ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ተነስተዋል። ይህ ዛሬ በአርመን የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት 14ኛ ሀገራት አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ሲሆን ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የቅዱስ ወንጌል አገልጋይ እና የሰላም መልእክተኛ መንፈስ በመላበስ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሆነ ቅድስት መንበር አስታውቃለች።

በሮም ሰዓት አቁጠጠር  ከጥዋቲ  ዘጠኝ ሰዓት  ከለአኦናርዶ ዳ ቪንቺ   ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ተነስተው  ከአራት ሰዓት በረራ በኃላ  በየአርመን ሰዓት አቁጣጠር  ከቀትር በኃላ  ሶስት ሰዓተ ላይ  ዝቫርትኖትስ  ሀገራት  አቀፍ  አውሮፕላን ማረፍያ በሰለም ደርሰዋል። ቅድስነታቸው  በአርመን ርእሰ ከተማ   የረቫን  ከተማ እንደ ደረሱ  የአርመን  ሐዋርያዊ ካቶሊኮስ ብጹዕ ወቅዱስ  ካረኪን ዳግማዊ  የሀገሪቱ  መንግስት ፕረሲዳንት ሰርዚ ሳርግስያን  የቤተ ክርስትያን እና የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርግውላቸዋል። የቅድስት  መንበር እና የአርመን  ብሔራውያን መዝሙሮች ተደምጠዋል።

ቅድስነታቸው እና ከሸኝዋቸው ብጹዓን አበው ኤችሚያዝዲን ከተማ  ላይ  ወደ ሚገኘው  መንበረ ሐዋርያ ተጉዘው እዚያው  ወደ ሚገኘው  ካተድራል  ተጉዘው  የሥርዓተ ጸሎት ከፈጸሙ በኋላ፡  ርእሰ  ሊቃነ  ጳጳሳት  የሰላምታ የሚከተለውን ተናግረዋል።  “እጅግ የተከበሩ ከፍተኛ ፓትርያርክና የመላ ኣርመኖች ካቶሊኮስ! የተከበራችሁ በክርስቶስ ወንድሞችና እህቶች! የኣርመን ሕዝብ ታሪክ ምስክርና የመንፈሳውነቱ ኣሸብራቂ ታሪክ ማእከል የሆነ የዚሁ ቅዱስ ቦታ መድርክ ስሻገር በጥልቅ ስሜት ሲሆን ለኣርመንያ ለመጀመርያ የክርስቶስ ብርሃን የፈለቀበትን ቅዱስ ታቦት መቅረቤ እጅግ የከበረ የእግዚኣብሔር ስጦታ መሆኑን እገነዘባለሁ፣  ለመላ ኣርመኖች ካቶሊኮስ ቅዱስነታቸው ካረኪን ሁለትኛ ሰላምታ ሳቀርብ ቅድስት ኤትችምያድዚን ለመጎበኘት ላቀረቡልኝ ዕድሜ እያመሰገንኩ የኣርመንያ ሓዋርያዊት ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳትን ጳጳሳትንም ላደረጉልኝ ኣቀባበል ልባዊ ምስጋና ኣቀርባለሁ፣ ብዙ ቃላቶች ከሚገልጹት በላይ ጓደኝነትና የወንድማሞች ፍቅርን በሚገልጸው ተግባር ቅዱስነታቸው በቤታቸው ስለተቀበሉኝ ኣመሰግናለሁ።

በዚሁ የኣቀባበል ስርዓት መጀመርያ እግዚኣብሔር ለኣርመንያ ኣገራችሁ ለሰጠው የእምነት ብርሃን ምስጋና ኣቀርባለሁ። ይህ እምነት ኣርመንያ በኣገሮች መካከል የክርስቶስ መልእክተኛ እንድትሆን በማድረግ ልዩ ማንነት ኣለበሳት፣ ክብራችሁ ክርስቶስ ነው! እንዲሁም በብርሃኑ እንድምታሸብርቁ ኣድርጎ ኣዲስ ሕይወት በመስጠት በተለይ ደግሞ ታላላቅ ፈተናዎች ባጋጠብማችሁ ጊዜ የሚሸኛችሁና የሚደግፋችሁ ክርስቶስ ብርሃናችሁ ነው፣  ከጥንት ከ301 ዓም ጀምሮ ኣርመናያ የመጀመርያ የክርስትያን ኣገር እንድትሆን መልካም ፈቃዱ በሆነ የጌታ ምሕረት ራሴን ዝቅ ኣደርጋለሁ፣ ያኔ በሮማዊ ግዛት ክርስትያኖች በጨካኝ ስደት ሳሉ ይህች ኣገር ግን ክርስትናን የኣገሩ ሃይማኖት እንዲሆን ተቀበለች፣

ለኣርመንያ የክርስቶስ እምነት እንደ ልብስ ከተቸመቸ የሚያጠልቁት ካልቸመቸ የሚጥሉት ሳይሆን ማንነታቸውና ዓላማቸው ኣድርገው በደስታ የተቀበሉትና ሕይወታቸው እስከመክፈል በመታገል ጸንተው ያኖሩት ታላቅ ስጦታ ነው፣ ለዚህም ነበር ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ‘በኣርመንያ ማህበረ ክስትያን ጥምቀት ሕዝቡን ያቆመና ኣርመናዊ ከመሆን የማይለይ ኣዲስ ማንነት ተወለደለት፣  ከክርስቶስ የተለየ የዚህ ሕዝብ ማንነት ለማሰብም ኣይቻልም’ ሲሉ የካቲት 2 2001ዓም ለ1700 ዝክር የጻፉት፣ ለዚሁ ምስክርነት እግዚኣብሔር ይባርካችሁ፣

በኣርመንያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንና በሓዋርያዊት የኣርመንያ ቤተ ክርስትያን መካከል በሚደረገው ወንድማማዊና ልበ ሙሉ ውይይት ስለምትሰጡት የውህደት ምስክርነትም ለእግዚኣብሔር ኣመሰግናለሁ፣ ይህ ውይይት በኣንድ የቅዱስ ቊርባን ማእድ የሚያደርስ ይሁን፣ መንፈስ ቅዱስ ጌታ የጸለየትን ኣንድነት ለመድረስ ይርዳን፣ ባለፉት ግዝያት ቅዱስነታቸው ቫስከን ቀዳማዊና ካረኪን ቀዳማዊ ከቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ከልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በቤተክርስትያኖቻችን መካከል ያለውን ግኑኝነትና ውይይት ለማጐልበት ያደረጉትን ጥረት በኣክብሮት ኣስታውሳለሁ፣ ከተደረጉት ኤኩመኒካዊ ተግባሮች መካከል በ2000 ዓም በታላቁ ኢየቤል ቅዱስነታቸው የኣርመናውያን ኣባትና ብርሃን የሆኑ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ቅዱሳን ቅርያቶች ለየረቫን ካተራል መስጠታቸው እንዲሁም በዚሁ ባለንበት ቦታ በቅድስት ኤትችምያድዚን በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና በቅዱስነታቸው መካከል የተደረገ የህብረት መግለጫ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በቫቲካን ያደረጉት ግቡኝንትና ሌሎችም መጥቀስ ይቻላል፣

ዛሬ ዓለማችን በሚያሳዝን ሁኔታ በመከፋፈልና በግጭት እንዲሁም ቁሳዊና መንፈሳዊ ድህነት የታወቀ ሲሆን ሕጻናትና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ከክርስትያኖች የወንድማማችነት መተባበር ምስክርነት ይጠባበቃሉ፣ ይህ ምስክርነት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ችሎታና የትንሳኤው እውነትን ያካተተ እንዲሆን ነው፣ በዚሁ የሌሊት ጨለማ በወረረው ዘመናችን ለሙሉ ኣንድነት የሚደረገው ትዕግስት የታከለበት የታደሰ የክርስትያኖች ኣንድነት ጥረትና በሁሉም የጌታ ተከታዮች መካከል የሚደረግ መተባበር እንደ ኣሸብራቂ ብርሃን ሊሆን ነው፣ የክርስትያን ኣንድነት እንቅሳቃሴ ከኣብያተ ክርስትያን ድንበር ውጭም በመሄድ ኣንድነት በሚፈጥሩ ጉዳዮች መወያየትና መተባበር ያስፈልጋል፣ ይህ ዓይነት ኣሰራር ሃይማኖትን ወደ ጽንፈኛ ኣስተሳሰብ ከመጠምዘዝ ሊያድን ይችላል፣ ምክንያቱም መሰረታዊ የሆኑ ዕሴቶችንና ስሮቻቸውን ኣፈላልጎ ለሌሎች ስለሚያካፍል እውነትን ለመከላከልን ለማስፋፋት ይረዳል፣ እንዲህ በማድረግም የእያንዳንዱ ሰው ክብርንና መብትን ለማክበርና ለመጠበቅ በመርዳት ያ በፍቅር ያገኘነውን ደህንነት ለሁሉ እንዲዳረስ ያደርጋል፣ ለዓለምም የሚያስተማምን ምስክርነት በመስጠት ጌታ ኢየሱስ ገና ሕያው መሆኑና ገና እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ኣዳዲስ የዕርቅ መንገዶች በመፍጠር በኣገሮች ስልጣኔዎችና ሃይማኖቶች መካክል ሰላም እንደሚፈጥር እንመሰክራለን፣ የእግዚኣብሔር ፍቅርንና ምሕረቱም ታማኝ በሆነ መንገድ እንገልጻለን፣

የተከበራችሁ ወንድሞች እያንዳንዱ ተግባራችን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ሃይል የተነሳሳና ሓይል ያገኘ እንደሆነ ኣንዱ ሌላውን የማወቃችንና የማክበራችን ባህል ይሰፋል፣ በኣንድነት መንፈስ ብዙ ፍሬ እያፈሩ እንዲጓዙም ያደርጋል፣ ይህ ነገር ለኣማኝም ይሁን ለባለበጎ ፈቃድ ተጨባጭ ምስክርነት ስለሆነ ያሉንን ግጭቶች በሰላም መፍትሔ ለማግኘት ይረዳል፣ የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኣባት የሆነ ሁሉ ቻይ እግዚኣብሔር በእመቤታችን ድንግል ማርያምን መራሔ ብርሃን ቅዱስ ጎርጎርዮስ እናንተን ሁላችሁምንና መላውን የኣርመንያ ሕዝብ ይባርክ! ከኣባቶቻችሁ በተቀበላችሁት እምነትም ጸንታችሁ እንድትኖሩ ይርድዋችሁ፣”

በመቀጠልም ርእሰ ሊቃነ  ጳጳሳት  ፍራንሲስ እና የአርመን ካቶሊኮስ  ከተከታዮቻቸው ጋር  ወደ  ኤችሚያዝዲን   መንበረ ሐዋርያ ተጉዘዋል። የኤችሚያዝዲን መንበረ  ሐዋርያ  ቅድስነታቸው በአርመን ቆይታቸው  የሚቆዩበት መካን  እንደሆን  ተመልክተዋል። 

ርእሰ ሊቃነ  ጳጳሳት ፍራንሲስ  በአርመን የተያዙት  ሐዋርያዊ ጉብኝት  በመቀጠል  በሀገሪቱ  ማለት በአርመን ሰዓት  አቆጣጠር   ከቀትር በኋላ  17 ተኩል  ለሀገሪቱ መራሄ መንግስት  የክብር ጉብኝት ለማደረግ  በርእሰ ከተማ የረቫን ወደ ሚገኘው  ቤተ መንግስት  ተጉዘዋል   ቤተ መንግስት   እንደደረሱም   ፕረሲዳንቱ  እና  የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት  ደማቅ አቀባበል   አድርጎውላቸዋል።

በዚሁ የተመንግስት አዳራሽ  የመንግስት ከፍተኛ  ባለስልጣናት  የበርካታሀገራት ዲፕሎማቶች  የሲቪል እና ባህል   ተወካዮች የተገኙ ሲሆን   የአረመን መራሄ   መንግስት ፕረሲዳንት ሰርጺይፕ

ሳርጊስያን  ለርእሰ ሊቃነ   ጳጳሳት   የእንኳን ደሃን መጡ   ንግግር   አሰምተዋል ።ቅድስነታቸውም ለተደረገላቸው  ደማቅ እቀባበል አመስግነ ንግግር አድርገዋል።

ቅድስነታቸው  በሀገሪቱ  ቤተ መንግስት  ያደረጉት ቆይታ  አጠቃልለው  ወደ  ሐዋርያዊ አዳራሽ  ተመልሰዋል።  በዚህም  ዛሬ  በኤስያ ክፍለ ዓለም  በአርመን   የጀመሩት  ሐዋርያዊ ጉብኝት  ተፈጽመዋል ።  ሐዋርያዊ ጉብኝቱ  እስከ  ፊታችን እሁድ  እንደሚቀጥል   ይታወቃል ።

ኣዲስ ኪዳን  አርመን  መጀመርያ  ክርስትና  ከተቀበሉ  ሀገራት  አንድዋ እና  አራራት  ምድረ   መሐፍ ቅዱስ   ብሎ  እንደሚጠራት  ተመልክተዋል።

የሀገሪቱ ህዝብ ሶስት ሚልዮን መሆኑ እና በ20 የተለያዩ የዓለም ሀገራት አራት ሚልዮን  አርመናውያነ  እንደሚኖሩ  ተገልጠዋል።  የአርመን  ካቶሊካውያን  ከሀግሪቱ ሶስት ሚልዮን ህዝብ በመቶ አስር  መሆናቸው  ይታወቃል፣ በአርመን  አዘርባጃን  እና ጆርጅያ  የቅድስት መንበር  ሐዋርያዊ እንደራሴ  ብፁዕ አቡነ  ማረክ ሶልስየንስኪ ሲሆኑ በቅድስት መንበር የአርመን አምባሳደር  ሚየል  ሚናስያን ናቸው።








All the contents on this site are copyrighted ©.