2016-06-22 20:11:00

ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ


ውድ ወንድሞችና እህቶች! እንደምን ኣደራችሁ!

‘ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ’ የሚለው ልመና ከኣንድ ለምጻም ወደ ኢየሱስ የቀረበ ነበር፣ ሰውየው ከሕመሙ መዳንን ብቻ ሳይሆን ሊነጻ ይጠይቃል፣ መላው ኣካሉና ልቡ በሕብረት እንዲነጻ ይጠይቃል፣ በዘመኑ ለምጽ የእግዚኣብሔር መርገም ሆኖ ጥልቅ ኣለመንጻትን ያመለክት ነበር፣ ለምጽ የያዘው ሰው ከህብረተሰቡ መራቅ ነበረበት፣ እንዲሁም በቤተመቅደስ ሊገባና በማንኛውም ስርዓተ ኣምልኮ ሊሳተፍ ኣይችልም ነበር፣ ከእግዚኣብሔር ከሕዝብ እጅግ የራቀ ነበር፣ የሚያሳዝን ሕይወት ነበር፣

ሁኔታው እንዲህ ቢሆንም ለምጻሙ ግን ለበሽታውም ይሁን ለህዝቡም ለመገለል ኣልበገርም ይላል፣ ኢየሱስን ለማግኘት ሕጉን ማፍረስ ኣላስፈራውም፣ ወደ ከተማም ገባ፣ በሕጉ መሰረት ከተማ መግባትስ ይቅር ከግለሰብም መቀላቀል ኣልነበረበትም፣ ኢየሱስን ባገኘው ግዜም እየሱስን ወደቀና ለመነው። ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ’ ኣለው፣ በሕዝቡ ንጹሕ እንዳልሆነ የሚታየው ይህ ሰው የሚያደርገው የሚናገረው የእምነቱ ብርቱነት መግለጫ ነበር፣ የኢየሱስ ችሎታን በማወቁ ደግሞ ሊያድነው እንድሚችልና ሁሉም በፍላጐቱ እንደሚወሰን ያውቃል፣ ይህ እምነት ነው ማንኛውን ውል ጥሶ ጌታ ኢየሱስን ለማግኘት የታገለው፣ ባገኘውም ግዜ ተንበርክኮ ‘ጌታ ሆይ’ ይለዋል፣ የለምጻሙ ልመና ጌታን ለመለመን በምንሄድበት ግዜ ረዥም ንግግር ማድረግ ኣስፈላጊ እንዳልሆነ ያስረደናል፣  በጌታ ኢየሱስ ሁሉም ቻይና በጎነት በሙሉ እምነትና መታመን  ይሁኑ እንጂ ጥቂት ቃላት ይበቃሉ! የእግዚኣብሔር ፍላጎት መተማመን ሁሉንም ወደር በሌለው ምሕረቱ መተው ነው፣ በግል ሕይወቴ ያጋጠመኝን ላካፍላችሁ፣ ማታ ልተኛ ስል ይህችን አጭር ጸሎት እደግማለሁ ‘ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ’ ካልኩ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በኣምስቱ ቊስሎቹ ስለኣነጻን ኣምስት ጊዜ በሰማይ የምትኖር ኣባታችንን እደግማለሁ፣ እናንተም በየቤቶቻችሁ ልትደግሙት ትችላላችሁ ‘ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ’ ካላችሁ በኋላ ኣምስቱን የጌታ ኢየሱስ ቁስሎችን በማስተንተን ለእያንዳንዱ ኣንድ በሰማይ የምትኖር ኣባታችን ሆይ መድገም ትችላላችሁ፣ ጌታ ኢየሱስ ሁሌ ይሰማናል፣

ጌታ ኢየሱስ በለምጻሙ ሁኔታ ልቡ እጅግ ተነካ፣ የማርቆስ ወንጌል ‘ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።’ (1.41)ይላል፣ የኢየሱስ እንቅስቃሴ ቃላቱን ሲሸኝ ትምህርቱን ግልጽ ያደርገዋል፣ በሙሴ ሕግ  መንካቱ ይቅርና ወደ ለምጽ የያዘው ሰው መቅረብ የተከለከለ ነበር (ዘሌ 13.45-46 ተመልከት)፣ ኢየሱስ ግን ከሕጉ ኣንጻር እጁን ዘርግቶ ዳሰሰው፣ ስንት ግዜ በመንገዳችን ድሆች ያጋጥሙናል! ልናዝንላቸው እንችላለን ልንለግስላቸውም እንችላለን  ነገር ግን አንጠጋቸውም ኣንነካቸውም፣ ላለመንካትና ላለመጠጋት ትንሽ ገንዘብ  ጣል እናደርግላቸዋለን፣ ያ ኣካል ግን የኢየሱስ ኣካል መሆኑን እንዘነጋለን፣ ኢየሱስ ግን ድሃንና የተገለለን ለመንካት እንዳንፈራ ያስተምረናል፣ ምክንያቱም እርሱ ከእነርሱ ጋር ነውና፣  ድሆችንና የተገለሉትን መርዳት የምንገኝበት ሁኔታና ያለንበትን  ሕይወት በበለጠ እንድንረዳ ይረዳናል። ዛሬ የምገኘው ከተገለሉ ወጣቶች ጋር ነው። ብዝዎች አገራቸው ቢቀሩ መልካም ነበር በማለት ቢያስቡም ግን አገራቸው ከዚህ የበለጠ ይሰቃዩ ነበር። እነዚህ ዛሬ የኛ ስደተኞች ቢሆኑም ቡዙዎች የሚመለከቷቸው በገለልተኝነት ነው። እባካችሁን እነዚህ ወንድሞቻችን ናቸው ክርስቲያን ማንንም አይነጥልም ለሁሉም ቦታ በመስጠት ሁሉንም ይጋብዛል።

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለምጻሙን ሰው ከፈወሰ በኋላ ለማንም ሰው እንዳይናገር ትእዛዝ ቢሰጠውም ግን ወደ ካህናቱ ሄዶ ራሱን እንዲያሳይና ለሕዝብም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻቱም ሙሴ ያዘዘውን መስዋእት እንዲያቀርብ ይነግረዋል።

እዚህ ላይ 3 የክርስቶስን ወዳጅነትን እንማራለን።  የመጀመሪያው በኛ ላይ ያለው የክርስቶስ ጸጋ በስሜታዊነት እንደማይሰራ  ነው- ረጋ ባለ መንፈስ በውስጣችን የተጎዳውን ክፍል በመንካት ሲያድነን እንዲሁም ወደ ቅድስና ሕይወት እያስተማረና እያሳደገ ልባችንንና ውስጣችንን በማሳደስ ወደ ክርስቶስ ልብ ያደርሳል።  ሁለተኛው  በኛ ላይ የተከሰተውን ፈውስ ለካህናት እንዲታይ በማድረግ ለዚህም መሥዋዕትን እንድናቀርብ ያስተምራል።  ለምጻሙ ሰው በመዳኑ ወደ ማህበራዊ ኑሮውና ከአማኖች ጋር አብሮ መኖር ይጀምራል።  የለምጻው ሰው መጽዳት እሱ ክርስቶስን እንደለመነው ሙሉ ፈውሱን  ማግኘቱን እናያለን። በመጨረሻም 3ኛው  ለምጻሙ ወደ ካህናቱ በመሄድ እራሱን ሲያሳይ የክርስቶስን ታላቅነትና መሲህነት ይመሰክራል። የክርስቶስን ምህረትና ርህራሄን ያስተምረናል። ለምጻሙ ሰው በክርስቶስ የነበረው እምነትም አዲስ የተልዕኮ በርን እንደ መክፈት ነው። ምክንያቱም ከሁሉም የተገለለ የነበር ሲሆን አሁን ግን በመዳኑ ከሁላችንም ጋር መቀላቀሉን ያስተምራል።

እስቲ አሁን በየግላችን ያሉንን ችግሮች እናስብ እስቲ በእውነት ውስጣችንን እንመልከት አንዳንዴ የግብዝነትን ልብስ በመልበስ እንደ መልካም ነገር በአስመሳይነት እንሸፍናለን  እንዲህ ሲሆን  ለብቻችን በመሆን በእግዚብሔር ፊት ተንበርክከን መጸለዩ መልካም ነው። ወደ መኝታ ከመሄዳችሁ በፊት ዘወትር ጌታ ሆይ አጽዳጅ ብሎ መጸለዩና መለመን መልካም ነው።   በመጨረሻም 3 ጊዜ ከምእመናኑ ጋር በሕብረት  ጌታ ሆይ፥ ብትወድስ፥ ልታነጻኝ ትችላለህ በማለት የሕብረት ጸሎት ካደረሱ በኋላ ሁሉንም በማመስገን የእለቱ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.