2016-06-22 16:24:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ለኢጣሊያ ካቶሊካውያን ጋዜጠኞች ማኅበር


በኢጣሊያ ግሮታማረ የደን ሃብት እድገት መተረክ በሚል መሪ ሓሳብ ሥር በዚህ እየተኖረ ባለው ልዩ ቅዱስ የምኅረት ዓመት ተመርቶ ወደ ሚካሄደው የኢጣሊያ ብሔራዊ የካቶሊካውያን ጋዜጠኞች ማኅበር ሦስተኛው ጉባኤ ቀዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን  ባስተላለፉት መልእክት ለማኅበሩ ጉባኤውን ላዘጋጁት በሚካሄደው ጉባኤ ንግግር ለሚያስደምጡት ሁሉ ቅርበታቸውን በማረጋገጥ ያንን የቤተ ክርስቲያን የህልውናዋና ለምታከናወነው ተግባር ሁሉ መሠረት የሆነው ምኅረት ለማካፈል ለማስተላለፍ የተጠራች ነች። ወቅታዊው ሰው የእግዚአብሔር ፍጹም ምኅርት ትስብእት ወደ ሆነው ክርስቶስ እንዲያቀና ትመራለች። ይኽ ጥሪ ለወቅታዊው የመገናኛ ብዙኃን አቢይ ተጋርጦ ነው። ስለዚህ ሁሉም በተለይ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ባለ ሙያዎችና በዚህ መስክ የሚያገለግሉት በጠቅላላ ኃይል ከእምነት በማግኘት በዚህ መንፈስም ያ ለዘመናት በተዋረድ የተላለፈው እሴት ቀጣይነት እንዲኖረና በዚህ ነባሪ በሆነው እሴት ተነቃቅቶ መጻኢ በእውነት ቦግታ ቅርጻአካል እንዲይዝ በማድረጉ ረገድ የሚያገለግሉ መሆንቸው በማሳሰብ ከዚህ ጋር በማያያዝም ቅዱስነታቸው በዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ የተካይነት ሥልጣናቸው ስለ እሳቸው ሁሉም እንዲጸልዩ አደራ ብለው ሁሉም ተጋባእያን አስተምህሮ የሚሰጡት አክላላት ዓለማውያን ምእመናን ካህናትና ብፁዓን ጳጳሳት መንበረ ጥበብ ለሆነቸው ቅድስት ድንግል ማርያም አወክፈው ለሁሉም ሓውርያዊ ቡራኬ ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.