2016-06-22 16:28:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የኡክራይን ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው አጠናቀቁ


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅርበት ለኡክራይን ሕዝብ ለማረጋገጥ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በኡክራይን ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ማጠናቀቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ሲያመለክቱ፥ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በኡክራይን የግሪክ ሥርትዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባኅረ ሓሳብ መሠረት ለበዓለ ጰራቅሊጦንስ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ተሳትፈው ቃል ምዕዳን ለግሰው በኡክራይን ውሁዳኑ የላቲን ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያንና የዘረአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ጭምር ተገናኝተው ኪየቭ የሚገኘው የአርበኞች ሐውልት ጎብኝተውና እዛው የአበባ ጉንግኑ በማኖር የሕሊና ጸሎት አሳርገው ኪየቭ ከሚገኘው ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤ ጋር መገናኘታቸው ያታወሱት ደ ካሮሊስ ስለዚሁ ግኑኝንት በተመለከተም ባጠናቀሩት ዘገባ፥

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የኡክራይን ወቅታዊው ሁነት እግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች ሰላም እውን እንዲሆን በማድረጉ ጥረት አቢይ ሚና የሚጫወት ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሰብ በዚህ የተለያየ ዘርፈ ብዙ ቀውስ እየታየ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሁሉም ኃይማኖችት ማኅበረሰብ ከቀድሞ በበለጠ ሰላምና ሰውን ማእከል ያደርገ ባህል ለማረጋገጥ በሚደርገው ጥረት ተቀዳሚ ኃላፊነት አለባቸው፡ ስለዚህ ሁሉም ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ ወቅታዊው ሁነት በለጠ ያስገነዝባል። የፈጣሪ ሓዋርያት ታማኝ የሚያደርጋቸው ፖሊቲካ፡ ኃብት ወይንም የእርስ በእርስ መስማምት ሳይሆን በሚኖሩት የአገልግሎት መንፈስና ከዚያ ምንም ዓይነት የግል ጥቅም መሻት የሚል ኅቡእ ዓላማ የሌለው በነጻ ለሁሉም ከሚሰጡት ታማኝ አገልግሎት የመነጨ ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

ኡክራይን ከምትገኝብት አስቸጋሪው ሁኔታ ለማላቀቅ በቅድሚያ ውህድነት ዳግም መልሶ ማግኘት ያስፈልጋል። በዚያች አገርች ሥር የሰደደው ክርስቲያናዊ ባህል ቅንነት ለጋስነት ፍትህና ምግብረ ብልሽውና መዋጋት የሚል በውስጡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለሚያቀርበውና ለሚያብሰለስለው ለወጣቱ ትውልድ አስተንፍሶ እንዲሆናቸው መደገፍና መምራት ያስፈልጋል፡ ወጣቱ ትውልድ ቅንነት የቃልና ተግባር ጥምረት እርስ በእርስ መከባበር የሚሉትን እሴቶች ይሻል ስለዚህ ሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች ይኸንን የወጣቱን ጥያቄና መሻት ተገቢ መልስ ለመስጠት የተጠሩ ናችው። ባጠቃላይ ጊዜው ላለፈበት የተቃዋሚነት ርእዮተ ዓለም መመዘኛና ለምኖርበት ዓለም የተስተካከለ አድርጎ ማየት ስህተት ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በመጨረሻም ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መጻኢ የሚያድንና ክፍት የሚያደርግ አፍቃሪው ምህረት መሆኑ ከሚመሰክሩት ውስጥ አንዱ መስካሪያን በመሆን ለኡክራይን ሕዝብ ቅርብ መሆናቸው በማረጋገጥ ቅዱስነታቸው በኡክራይን ምስራቃዊ ክልል ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተጎዳው ለተፈናቀለው መርጃ እንዲውል ያነቃቁት በመላይቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምጽዋት የማሰባሰቡ መርሃ ግብር በመሳተፍ አስተዋጽኦ ለሰጡት ሁሉ አመስግነው ይኽ ተጨባጭ ግብረ ሠናይ ቅዱስ አባታችንና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ለሰው ልጅ ያላት አሳቢነት የሚያረጋግጥ ነው እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው ህዝብ እውነተኛ ነጻነትን ይሻል ወደዚሁ እውነተኛ ነጻነትም የሚሸኘው ያስፈልገዋል ስለዚህ ለዚህ ሕዝብ ለሚሻው እውነተኛ ነጻነት ለመለከት ለሚቀርበው የድጋፍ ጥያቄ  መልስ ለመስጠት የምንችል ሆነን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይርዳን በማለት ያስደመጡት ቃለ እንዳጠቃለሉ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.