2016-06-20 16:50:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ከወንድሞቻችን ጋር ለመገናኘት መውጣት የመለወጥ ምልክት ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ በተገባው የምኅረት ዓመት ምክንያት ሁሌ ቅዳሜ የሚለግሱት ምኅረት ማእከል ያደረገ ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከውጭና ከውስጥ ለመጡት ምእመናን፥ ሰዎች ይለወጣሉ፡ ሕይወታቸው ይታደሳል ምክንያቱም በኢየሱስ መፈቀራቸው ስለ ሚሰማውቸውና ይኸንን ፍቅሩን ስለ ሚያስተውሉ ነው የሚል ሃሳብ ያሰመሩበት ስርየተ ኃጢኣት ማእከል በማድረግ በለገሱት አስተምህሮ፥ ገዛ እራስ ለጸጋ ክፍት ማድረግና ወደ ወንድሞ ማቅይና ከውንድሞቻን ጋር መገናኘት አንዱ የመለወጥ ምልክት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።

መለወጥ ማለት የምትከተለው መርሃ መንገድህን መቀየር ማለት ነው፡ ይኽ ሃሳብ በመጽሓፍ ቅዱስ በተደጋሚ የሚሰጥ ምክርና ጥሪም ነው፡ በተለይ ደግሞ በነቢያት አፍ ለሕዝበ እግዚኣብሔር የሚነገር በቀጣይነት የሚሰጥ ምዕዳን ነው፡ ወደ ጌታ መመለስ። ምኅረቱን መለመንና የሕይወት አገባብና ስልት መለወጥ ያስፈጋል፡ ኢየሱስ መለወጥ የሚለውን ቃል በመጀመሪያ ስብከት ሲጀምር የተጠቀመበት ቃል ነው፡ ተለወጡ በወንጌልም እመኑ እያለ ጠንካራ ምዕዳን ያቀርባል። ነቢያት ያቀርቡት ከነበረው ጥሪ ለየት የሚያደርገውም እርሱ የሚገልጠው መለወጥ ውስጣዊ መለወጥ የሚል ሲሆን፡ መላ ስብእናን የሚመለከት አዲስ ፍጥረት መሆን የሚል ትርጉም ያለው በመሆኑ ነው፡ አዲስ ሰውና አዲስ ፍጥረ መሆን፡  ኢየሱስ ተለውጥ ተለወጡ ብሎ ሲል እንደ ፈራጅ ዳኛ  በመቅረብ ሳሆን ተለወጥ ብሎ ጥሪ ለሚያቀርብለት ሰው ቅርብ በመሆን ከእርሱ ጋር አብሮ በመንገድ በመጓዝ አብሮ ወደ ቤቱ በመግባትና አብሮት በማእድ በመቀመጥ ነው፡ ለዚህም ነው ሕዝብ በኢየሱስ ላይ እማኔው ያኖረው። በ ፍቅር ምኅረቱን የሚገልጥ ጌታ ነው። እንዲህ ባለ ጠባይና ሁነት ኢየሱስ ይሰጠው  በነበረው የመለወጥ ጥሪ የሕዝብ ልብ በጥልቀት ይነካ ነበር፡ ሕዝቡም በዚህ አኳያ በእግዚአብሔር ፍቅር ተማርኮ ሕይወቱንም ለመለወጥ ጥልቅ ምክንያት ያገኝ ነበር። እውነተኛው መለወጥ የሚረጋገጠው ጸጋውን አሜን ብሎ ከመቀበልና የእውነተኛ መለወጥ ምልክቱን ወንድሞች እንደሚያስፈልጉንና እነርሱ ጋር ለመገናኘት ከእራስ መውጣት የሚለው ነው።

ብዙውን ጊዜ በሕይወት ጉዟችን ፍሬ አለ መስጠት ምድረ በዳነት መኖሩን ስለምናስተውል የጥልቅ ለውጥ አንገብጋቢነት በውስጣችን እንዳምጣለን። ስንት ጊዜ በሕይወታችን ኢየሱስ ና ወደ እኔ በማለት የሚያቀርብልንን ጥሪ እናዳምጣለን፡ የመለወጡን ሥራ ፈጻሚው እኔ ነኝ እኔ ደስተኛ አደርግሃለሁ። እንተ ናና ተከተለኝ ነው የሚለው፡ ኢየሱስ አብሮን ከእኛ ጋር ነው። ሕይወታችን እንለውጥም ዘንድ ይጠራናል። መለወጣችን እርሱ ከእኛ ጋር በመሆኑ ነው እንዳሉ ዶኒኒ ገለጡ።

ሕይወታችንን ለመለወጥ የመሻቱ ግፊትና በውስጣችን የአለማረፉ ሁኔታ ይታያል፡ እኛ ማድረግ የሚገባን ነገር ቢኖር በሮቻችንን በሙላት መክፈት ነው። የተቀረው ሁሉ እርሱ ይከውነዋል። እርሱ ይፈውሰናል ወደ ፊት እንራመድም ዘንድ ያበቃናል። እንዲህ ስናደድግ ደስተኞች እንደምንሆን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ በማለት ቅዱስ አባታችን በምኅረት ርእስ ዙሪያ የሰጡት ትምህርተ ክርስቶስ ማጠቃለላቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው፥ ቅዱስነታቸው እዛው ለተገኙት ከውጭና ከውስጥ ለመጡት የፈረንሳይ የብሮን የመከላከያ ኃይል ጤና ጥበቃ ትምህርት ቤት አባላት፡ በጀርመን የአይኽሽታት ዘርአ ክህነት ተማሪዎች፡ ከመካለኛው ምስራቅ የመጡት የዓአብኛ ቋንቋ ተናጋሪ መፈሳዊ ነጋድያን፡ በቶሪኖ የኮቶለንጎ ግብረ ሠናይ ማኅበር አባላት፡ በብፅዕ ካርዲናል ጁዘፐበቶሪ የተሸኙት የፊረንዘ ሰበካ ምእመናን እና የተለያዩ እዛው በትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የተገኙትን ማኅበራት ሁሉ ሰላምታ በማቅረብ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበት ማሰናበታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.